Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide
This is the Amharic edition of Capstone Module 5 Mentor Guide
ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ
THE URBAN MINISTRY INSTITUTE የWORLD IMPACT, INC. አገልግሎት ነው
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
የመምህሩ መምሪያ
ሞጁል 5 ስነመለኮት እና ስነምግባር
AMHARIC
የመምህሩ መመሪያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
ሞጁል 5
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥናቶች
መጽሐፍ ቅዱሳዊ እስትንፋሰ እግዚአብሔር፦
የመጽሐፍ ቅዱስ አመጣጥና ሥልጣን
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት፦
የሶስት-ደረጃ ሞዴል
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስነ ጽሑፍ:-
የመጽሐፍ ቅዱስ ዘውጎችን መተርጎም
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች:-
ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አጋዥ መሣሪያዎችን መጠቀም
ይህ ሥርዓተ-ትምህርት የThe Urban Ministry Institute (TUMI) የሺዎች ሰዓታት የሥራ ውጤት በመሆኑ ያለ ፈቃድ ማባዛት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ TUMI እነዚህን መማሪያዎች ለእግዚአብሔር መንግሥት እድገት ለመጠቀም ለሚፈልጉ ሁሉ ድጋፍ ያደርጋል፤ በተጨማሪም ለማባዛት በተመጣጣኝ ዋጋ ፈቃድ ይሰጣል ፡፡ እባክህ ይህ መጽሐፍ በትክክል ፈቃድ ያገኘ መሆኑን ከመምህርህ ጋር በመሆን አረጋግጥ፡ ፡ በ TUMI እና በፈቃድ አሰጣጥ ፕሮግራማችን ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት Www.site.org እና Www.tumi.org/license ን ጎብኝ፡፡
ካፕስቶን ሞጁል 5: - የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት የመምህሩ መመሪያ ISBN: 978-1-62932-087-8
© 2005, 2011, 2013, 2015. The Urban Ministry Institute. መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው. የመጀመሪያ እትም 2005 ፣ ሁለተኛ እትም 2011 ፣ ሦስተኛው እትም 2013 ፣ አራተኛ እትም 2015 ፡፡ © 2017 Amharic Translated by Amanuel Abera
በ 1976 የቅጂ መብት ሕግ ወይም ከአሳታሚው በፅሁፍ ከሚፈቀደው በስተቀር የእነዚህን መማሪያ ቁሳቁሶች መቅዳት፣ እንደገና ማሰራጨት እና / ወይም መሸጥ ወይም በማንኛውንም ያልተፈቀደ መንገድ ማስተላለፍ የተከለከለ ነው ፡፡ የፍቃድ ጥያቄዎች በሚከተለው አድራሻ መቅረብ አለባቸው፥ The Urban Ministry Institute ፣ 3701 E. 13th Street, Wichita, KS 67208. The Urban Ministry Institute የWorld Impact አገልግሎት ነው በዚህ ሞጁል ውስጥ የተጠቀሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በሙሉ በአዲሱ መደበኛ ትርጉም ላይ የተመሰረተ ነው፡ ፡
ይዘት
የኮርሱ አጠቃላይ እይታ
3 5 7
ስለ ጸሐፊው
የሞጁሉ (የትምህርቱ) መግቢያ
የኮርሱ መስፈርቶች
13 ትምህርት 1
1
መጽሐፍ ቅዱሳዊ እስትንፋሰ እግዚአብሔር:- የመጽሐፍ ቅዱስ አመጣጥና ሥልጣን
57 ትምህርት 2
2
የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ትምህርት:- የሦስት ደረጃ ሞዴል
107 ትምህርት 3
3
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥነ ጽሑፍ፦ የመጽሐፍ ቅዱስን ዘውጎች መተርጎም
159 ትምህርት 4
4
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች፦ ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማመሳከሪያዎችን መጠቀም
207
አባሪዎች
283 የካፕስቶን ሥርዓተ-ትምህርት ማስተማሪያ
291
የትምህርት 1 የመምህሩ ማስታወሻዎች
297
የትምህርት 2 የመምህሩ ማስታወሻዎች
301
የትምህርት 3 የመምህሩ ማስታወሻዎች
305
የትምህርት 4 የመምህሩ ማስታወሻዎች
/ 3
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
ስለ ጸሐፊው
ቄስ ዶ/ር ዶን ኤል ዴቪስ የዘ አርባን ሚኒስትሪ ኢንስቲትዩት ሥራ አስፈፃሚ እና የዎርልድ ኢምፓክት ከፍተኛ ምክትል ፕሬዚዳንት ናቸው ፡፡ ትምህርታቸውን በዊተን ኮሌጅ እና በዊተን ድህረ ምረቃ ትምህርት ቤት የተከታተሉ ሲሆን በቢብሊካል ስተዲስ የቢ.ኤ. (1988) እና በሲስተማቲክ ቲዎሎጂ የኤም.ኤ (1989) ዲግሪዎችን በቅደም ተከተል ማግኘት ችለዋል ፡፡ በተጨማሪም ከአዮዋ ስኩል ኦፍ ሪሊጅን በሃይማኖት ጥናት (ሥነ-መለኮት እና ሥነ-ምግባር) ፒኤችዲ አግኝተዋል ፡፡ የተቋሙ ሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር እና የዎርልድ ኢምፓክት ዋና ሥራ አስፈፃሚ እንደመሆናቸው መጠን የከተማ ሚስዮናውያንን ፣ የቤተ ክርስቲያን ተካዮችን እና የከተማ መጋቢያን ሥልጠናን በበላይነት የሚቆጣጠሩና የሚመሩ ሲሆን ለከተሞች ክርስቲያን ሠራተኞች በስብከተ ወንጌል ፣ በቤተ ክርስቲያን እድገት እና በተቀዳሚ ተልእኮዎች የሥልጠና ዕድሎችን ያስተባብራሉ ፡፡ በተጨማሪም የተቋሙን ሰፊ የርቀት ትምህርት መርሃግብሮች ይመራሉ እንዲሁም እንደ ፕሪዝን ፌሎውሺፕ ፣ ኢቫንጀሊካል ፍሪ ቸርች ኦፍ አሜሪካ ላሉት ድርጅቶች እና ቤተ እምነቶች የአመራር ልማት ኢድሎችን ያመቻቻሉ ፡፡ የበርካታ የማስተማር እና የአካዳሚክ ሽልማቶች ባለቤቱ ዶ/ር ዴቪስ በበርካታ ዕውቅ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሮፌሰር እና የፋኩልቲ አባል ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በሃይማኖት ትምህርቶች፣ ሥነ መለኮት ፣ ፍልስፍና እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥናቶች (ቢብሊካል ስተዲስ ) እንደ ዊተን ኮሌጅ ፣ ሴንት አምብሮስ ዩኒቨርሲቲ ፣ ሂዩስተን ድህረ ምረቃ የሥነ-መለኮት ትምህርት ቤት ፣ በአዮዋ ዩኒቨርሲቲ ስኩል ኦፍ ሪሊጅን ፣ በሮበርት ኢ ዌበር ኢንስቲትዩት ኦፍ ዎርሺፕ ስተዲስ ባሉ የትምህርት ተቋማት ሲያስተምሩ ቆይተዋል፡፡ የከተማ መሪዎችን ለማስታጠቅ በርካታ መጻሕፍትን ፣ ሥርዓተ-ትምህርቶችን እና የጥናት ጽሑፎችን አዘጋጅተዋል ፣ ከነዚህም ውስጥ የ ‹ካፕስቶን› ሥርዓተ ትምህርት ፣ የ TUMI ፕሪሚየር ሲክስቲን ሞጁል ዲስታንስ ኤጁኬሽን ሴሚናሪ ኢንስትራክሽን፥ የከተሞች አብያተ ክርስቲያናት ታሪካዊቷን የኦርቶዶክስ እምነት እንደገና በማደስ ራሳቸው እንዴት ሊታደሱ እንደሚችሉ የሚያትተው ሴክርድ ሩትስ፡ ኤ ፕሪሚየር ኦን ሪትራይቪንግ ዘ ግሬት ትራዲሽን እና ብላክ ኤንድ ሂዩማን፡ ሪዲስከቨሪንግ ኪንግ አስ ኤ ሪሶርስ ፎር ብላክ ትዎሎጂ ኤንድ ኤቲክስ ተጠቃሾች ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ዶ/ር ዴቪስ እንደ ስታሊ ሌክቸር ሲሪስ ባሉ ትምህርታዊ ጉባኤዎች፣ እንደ ፕሮሚስ ኪፐርስ ራሊስ ባሉ የተሃድሶ ኮንፈረንሶች እና እንደ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቨርጂኒያ ሊቭድ ቲዎሎጂ ፕሮጄክት ሲሪስ ባሉ ሥነ-መለኮታዊ ጥምረቶች ተሳትፈዋል ፡፡ ዶ/ር ዴቪስ በ 2009 ከአዮዋ ዩኒቨርስቲ የሊበራል አርትስ እና ሳይንስ ኮሌጅ የአልሙናይ የክብር ሽልማት ያገኙ ሲሆን በተጨማሪም የዘ ሶሳይቲ ኦፍ ቢብሊካል ሊትሬቸር እና ዘ አሜሪካን አካዳሚ ኦፍ ሪሊጅን አባል ናቸው ፡፡
/ 5
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
የትምህርቱ/የሞጁሉ መግቢያ
ኃያል በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም ላንተ ይሁን!
በቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነት መሰረት እግዚአብሔር በመንፈሰ-እስትንፋስ በተሞላው የእግዚአብሔር ቃል አማካኝነት ወኪሎቹን ያስታጥቃቸዋል። እግዚአብሔር ወደ አገልግሎት የጠራው ማንኛውም ሰው የቃሉን ይዘት ጠንቅቆ ለማጥናት፣ ለትእዛዛቱ ለመገዛት እና እውነቱን ለማስተማር ራሱን ለማስገዛት የወሰነ መሆን አለበት። እንደ ትጉህ ሰራተኛ የእውነትን ቃል በቅንነት ለመናገር እና በትምህርቱም በጌታ ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት መጣር አለበት (2ጢሞ. 2.15)። ይህ ሞጁል መጽሐፍ ቅዱስን ለመተርጎም የሚያስፈልጉትን እውነታዎች፣ መሠረታዊ ሥርዓቶችና ውጤቶች ያብራራል። የመጽሐፍ ቅዱስ እስትንፋሰ እግዚአብሔር: የመጽሐፍ ቅዱስ አመጣጥና ሥልጣን በተሰኘው የመጀመሪያ ትምህርታችን ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ አስፈላጊነትና ለዚህ ታላቅ ተግባር ለመዘጋጀት ምን ማድረግ እንዳለብን እንመለከታለን። የመጽሐፍ ቅዱስን መለኮታዊም ሆነ ሰዋዊ ገጽታ እንመረምራለን፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ዓላማ ምን እንደሆነ እንመለከታለን፤ እንዲሁም ቅዱሳት መጻሕፍት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያላቸውን ከፍተኛ ቦታ በተመለከተ የሥነ መለኮታዊ አስተሳሰባችንን በግልጽ እናቀርባለን። የእግዚአብሔርን ቃል በትክክል ለመተርጎም የሚያስፈልገውን የአኗኗር ዘይቤና የልብ ዝግጅት በተመለከተ ይበልጥ ትኩረት እንሰጣለን። በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር መንፈስ አነሳሽነት እንደተጻፈ የሚገልጸውን ሐሳብ እንዲሁም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለውን ሥልጣንና ቦታ እንመለከታለን። የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን በከፍተኛ ደረጃ እየጨመሩ ባሉበት በዚህ ዘመን ዘመናዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትችቶችን በአጭሩ እንመለከታለን፤ እንዲሁም ከቅዱሳት መጻሕፍት ጥናታችን ጋር በተያያዘ የሚነሱትን ጥያቄዎች እንመረምራለን። የመጽሐፍ ቅዱስ ስነ-አፈታት: የሶስት ደረጃ ሞዴል በተሰኘው በሁለተኛው ትምህርታችን ደግሞ በጥንታዊ እና በዘመናዊ ዓለማችን መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ወደ ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናትህ እንድትቀርብ ለማገዝ የተነደፈውን ውጤታማ የመጽሐፍ ቅዱስ ስነ አፈታት ዘዴ እናስተዋውቃለን። የሶስት ደረጃ ሞዴል ብለን እንጠራዋለን: የመጀመሪያውን ተደራሲያን መረዳት፣ አጠቃላይ መርሆችን ማስቀመጥ እና በህይወትህ መተግበር። በዚህ ትምህርት ውስጥም ይህንን ሞዴል በመጠቀም የቅዱሳት መጻሕፍትን ክፍሎች እንመረምራለን፣ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በጻፈው ደብዳቤ ውስጥ ያለውን ክፍል እንመለከታለን፣ በመጀመሪያው መልእክቱ 9.1-14 የመጽሐፍ ቅዱስ ስነአፈታት ቁልፎች በተባለው ተጨማሪ ክፍል ውስጥ የሚገኘውን ማዕቀፍ በመጠቀም ይህን ታላቅ የቅዱሳት መጻሕፍት ምንባብ በጥንቃቄና በጸሎት በመመርመር የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቃል በመጠቀም ፈቃዱን ለመረዳት ስንጥር እንዴት ታላቅ መረዳትና መነሳሳት ማግኘት እንደምንችል እንመረምራለን። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስነ ጽሑፍ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘውጎችን መተርጎም በተሰኘው ሦስተኛው ትምህርት ላይ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን ጽሑፎችና እንዴት መተርጎም እንደሚቻል እንመለከታለን። የመጽሐፍ ቅዱስ ስነ አፈታት ውስጥ የዘውግ ፅንሰ-ሀሳብን (ዣንራ ተብሎ የሚጠራውን) እንመለከታለን፣ ስለ ሀሳቡ አጠቃላይ እይታ እናቀርባለን ፣ እንዲሁም ስለዚህ ዓይነቱ ልዩ የስነ አፈታት ዘዴ ጥቂት መሠረታዊ ግምቶችን እንሰጣለን። በመቀጠልም የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘውጎችን
6 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
እንመለከታለን፣ ነገር ግን የመጽሐፍ ቅዱስን እውነተኛ ይዘት በአብዛኛው ለሚወክሉት ሁለት የስነ ጽሑፍ ዓይነቶች ልዩ ትኩረት እንሰጣለን - ትረካዊ እና ትንቢታዊ። ስለ ትረካ ጥናት (ማለትም ፣ ስለ ታሪክ ሥነ-መለኮት) እንዲሁም ስለ ትንቢታዊ እና አፖካሊፕቲክ ሥነ-ጽሑፍ አጭር ግን ጥልቅ ውይይቶችን እናደርጋለን፣ ለተለያዩ ዘውጎች ትኩረት መስጠታችን ቅዱሳት መጻሕፍትን በተሻለ ለመተርጎም እንዴት እንደሚረዳን ያሳያል። በመጨረሻም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች:- ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማመሳከሪያዎችን መጠቀም በተሰኘው አራተኛው ትምህርታችን እንጨርሳለን። አንድን የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ ትርጉም ለመረዳት ስንሞክር ምን ዓይነት አስተማማኝ የማመሳከሪያ መሣሪያዎች እንዳሉ እንመለከታለን። ዛሬ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ የቃሉን እውቀት ለማግኘት የሚረዱትን በጽሑፍም ሆነ በሶፍትዌር መልክ ማመሳከሪያዎችን ማግኘት ይችላል። በመጀመሪያ ለጠንካራ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጓሜ መሠረታዊ መሳሪያዎች፡ ጥሩ የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጉም፣ የዕብራይስጥ እና የግሪክ መርጃዎች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ ኮንኮርዳንስ እና የኤክሲጀሲስ ማጣቀሻዎች ላይ እናተኩራለን። በተጨማሪም የቅዱሳት መጻሕፍት ጥናታችንን ሊያዳብሩ የሚችሉ ተጨማሪ መርጃዎችንም እንመለከታለን። እነዚህም የማመሳከሪያ መርጃዎች፣ ርዕስ መር መጽሐፍ ቅዱሶች፣ ማጣቀሻ መጽሐፍ ቅዱሶች እና ርዕስ መር ኮንኮርዳንስን ያካትታሉ። በተጨማሪም በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክና ልማዶች ላይ የሚያተኩሩትን መርጃዎች፡ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ኢንሳይክሎፔዲያዎች፣ አትላስ እና ሌሎች ተዛማጅ የማመሳከሪያ ጽሑፎችን እንጠቀማለን። በመጨረሻም፣ መጽሐፍ ቅዱስን ለአምልኮ፣ ለስብከት እና ለማስተማር በምትተረጉሙበት ወቅት የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎችን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያዎችን፣ የጥናት መጽሐፍ ቅዱሶችን፣ እና በአጠቃላይ ማመሳከሪያዎች ስለሚኖራቸው ሚና በመመልከት እናጠቃልላለን። መጽሐፍ ቅዱስ የራሱ የመለወጥ ኃይል እንዳለው የሚገልጸው አስደናቂ ሐሳብ የእግዚአብሔርን ቃል ጠንቅቀን እንድንማር ሊገፋፋን ይገባል። “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።” 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥16-17። በሰዎች ቃል ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር እስትንፋስ ያለው የእግዚአብሔር ቃል እኛን ለማጎልበት፣ ለማነጽ እና ለበጎ ስራ ሁሉ ብቁ እና የታጠቀን እንድንሆን በቂ ነው። በእርግጥ የእግዚአብሔር ቃል ሊሰበር አይችልም፣ አላማውን ሁል ጊዜ ይፈጽማል፣ የእግዚአብሔርም ልጆች የትም ቢሆኑ የእግዚአብሔርን መንግስት ለማስፋት በሚያደርጉት ሁሉ መልካም ስኬት እንደሚያገኙ ያረጋግጣል (ዮሐ. 10.35፣ ኢሳ. 55.8-11፤ ኢያሱ 1.8)። የእኔም ልባዊ ጸሎት መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ እና ዘላለማዊ ቃሉን የመተርጎም መርሆችን እና ልምምዶችን እንድትመረምር ይረዳህ ዘንድ፣ እነዚህ ሁሉ እና ሌሎችም በረከቶች ያንተ ይሆኑ ዘንድ ነው።
ለመታነጽ ይሆንህ ዘንድ በከፍተኛ ጉጉት፣
- ቄስ ዶ/ር ዶን ኤል ዴቪስ
/ 7
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
የኮርሱ መስፈርቶች
• መጽሐፍ ቅዱስ (ለዚህ ትምህርት ዓላማ ሲባል የአንተ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም መሆን አለበት [ለምሳሌ NIV, NASB, RSV, KJV, NKJV, ወዘተ] እና የትርጓሜ ሐረግ መሆን የለበትም [ለምሳሌ The Living Bible, The Message] • እያንዳንዱ የካፕስቶን ሞጁል በሙሉ ትምህርቱ የሚነበቡ እና የሚያወያዩ የመማሪያ መጽሀፎችን አካትቷል ፡፡ እነዚህን ከመምህርህ እና አብረው ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር በመሆን እንድታነብ፣ እንድታሰላስል እና እንድትመልስ እናበረታታሃለን ፡፡ እነዚህ ጽሑፎች በበቂ ሁነታ መገኘት ባለመቻላቸው ምክንያት (ለምሳሌ ፣ በቂ የመጻሕፍቱ ሕትመት ካለመኖሩ የተነሳ) የካፕስቶን አስፈላጊ የመማሪያ መጽሐፍ ዝርዝራችንን በድረ-ገፃችን ላይ እናስቀምጣለን። የዚህን መጽሐፍ (ሞጁል) ጽሑፎች ወቅታዊ ዝርዝር ለማግኘት እባክህን www.tumi.org/booksን ጎብኝ። • የክፍል ውስጥ ሥራዎችን ለመስራት እና ማስታወሻዎችን ለመውሰድ ወረቀት እና ብዕር ፡፡ • Douglas, J. D., N. Hillyer, and D. R. W. Wood, eds. New Bible Dictionary , 3rd ed. Downers Grove: InterVarsity Press (IVP), 2000. • Strong, James. Strong’s Exhaustive Concordance of the Bible . Iowa Falls: World Bible Publishers, 1986. • Vine, W. E. Vine’s Complete Expository Dictionary of Old and New Testament Words . Merrill F. Unger and William White, Jr., revision eds. Nashville: Thomas Nelson, 1996. • Wenham, G. J., J. A. Motyer, D. A. Carson, and R. T. France, eds. New Bible Commentary . 21st Century ed. Downers Grove: IVP, 2000. • Kuhatschek, Jack. Applying the Bible . Grand Rapids: Zondervan, 1990. • Montgomery, J. W. ed. God’s Inerrant Word . Minneapolis: Bethany, 1974. • Packer, J. I. “Fundamentalism” and the Word of God . London: IVP, 1958. • ------. God Has Spoken: Revelation and the Bible . Grand Rapids: Baker, 1979. • Sproul, R. C. Knowing Scripture . Downers Grove: IVP, 1977.
አስፈላጊ መጻሕፍት እና ቁሳቁሶች
ሊገዙ የሚገቡ ማጣቀሻ መጻሕፍት
እባክህ ልብ በል:- እነዚህ የማጣቀሻ ምንጮች ለግል የመጻሕፍት ስብስብህ እንድትገዛቸው ትመከራለህ። የዚህን ትምህርት ስራዎች ለማጠናቀቅ እንደነዚህ አይነት ማጣቀሻዎችን ማግኘት ይኖርብሃል።
የተጠቆሙ ንባቦች
8 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
የግምገማዎች እና የምዘናዎች ድምር ውጤት በክፍል መገኘት እና የክፍል ውስጥ ተሳትፎ
የኮርሱ መስፈርቶች
30% 90 ነጥቦች
ፈተናዎች
10% 30 ነጥቦች
የቃል ጥናት ጥቅሶች
15% 45 ነጥቦች
የእክሴጀሲስ ፕሮጀክት
15% 45 ነጥቦች
የሚኒስትሪ ፕሮጀክት
10% 30 ነጥቦች
ንባቦች እና የቤት ስራዎች
10% 30 ነጥቦች
የማጠቃለያ ፈተና
10% 30 ነጥቦች
ጠቅላላ ድምር: 100% 300 ነጥቦች
አጠቃላይ ውጤት መመዘኛ መስፈርቶች በእያንዳንዱ የትምህርት ክፍለ ጊዜ መገኘት የኮርሱ ቅድመ ሁኔታ ነው ፡፡ መቅረት በውጤትህ ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል። በአስገዳጅ ምክንያት መቅረት ግድ በሚሆንበት ጊዜ እባክህ አስቀድመህ ለመምህርህ አሳውቅ ፡፡ ያመለጠህ ክፍለ ጊዜ ሲያጋጥም ያመለጠህን የቤት ሥራ መስራት እና ስለዘገየህበት ሁኔታ ከመምህሩ ጋር መነጋገር የአንተ ኃላፊነት ነው። ይህ ኮርስ ባብዛኛው በውይይት መልክ የሚካሄድ እንደመሆኑ መጠን የአንተ ንቁ ተሳትፎ በእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ ውስጥ የሚፈለግና የሚጠበቅ ይሆናል። እያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ የሚጀምረው ካለፈው ትምህርት መሠረታዊ በሆኑት ሀሳቦች ላይ በተመሰረተ በአጭር ፈተና ይሆናል። ለፈተናው ለመዘጋጀት ደግሞ የተሻለው መንገድ ባለፈው ትምህርት ወቅት የተወሰዱ የተማሪውን መልመጃ (Student Workbook) እና የክፍል ማስታወሻዎችን መከለስ ነው ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ አማኝ እና መሪ እንደመሆንህ መጠን በቃልህ ያጠናኸው ጥቅስ(ቃል) ለህይወትህ እና ለአገልግሎትህ መሰረት ነው ፡፡ በአንጻራዊነት ጥቅሶቹ ከቁጥር አንጻር ጥቂት ቢሆኑም በይዘታቸው ግን ጠቀሜታቸው የጎላ ነው፡፡ በእያንዳንዱ የትምህርት ክፍለ ጊዜ የተሰጡትን ጥቅሶች (በቃል ወይም በፅሁፍ) ለመምህርህ እንድትናገር ወይም እንድታነብብ ይጠበቅብሃል ፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር ወንድ እና ሴት ልጆች ለተጠሩበት የአገልግሎት ድርሻ ሁሉ ለማስታጠቅ የእግዚአብሔር ልዩ መሳሪያ ናቸው (2 ጢሞ. 3.16-17) ፡፡ ለዚህ ኮርስ የሚያስፈልጉትን መመዘኛዎች ለማጠናቀቅ አንድ መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በመምረጥ በንባቡ ላይ ተግባራዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት (ማለትም ፣ የትርጓሜ ጥናት) ማድረግ አለብህ ፡፡ ጥናቱ አምስት ገጾች ርዝመት ሊኖረው ይገባል (በድርብ የተከፋፈለ ፣ ታይፕ የተደረገ ወይም በጥሩ ሁኔታ በእጅ የተፃፈ) እና በዚህ ትምህርት ውስጥ ጎላ ብለው ከተነሱት የክርስቲያን ሚሽን መሠረተ-ትምህርቶች እና መርሆዎች
በክፍል መገኘት እና የክፍል ውስጥ ተሳትፎ
ፈተናዎች
የቃል ጥናት ጥቅስ
የእክሴጀሲስ ፕሮጀክት
/ 9
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
ውስጥ አንዱ ላይ ያተኮረ መሆን ይኖርበታል፡፡ ፍላጎታችን እና ተስፋችን ቅዱሳት መጻሕፍት የአንተን እና የምታገለግላቸውን ሰዎች ሕይወት በተጨባጭ ለመለወጥ ያላቸውን አቅም እንዲረዱ ነው። ኮርሱን በምትወስድበት ጊዜ የበለጠ ለማጥናት በምትፈልገው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ የንባብ ክፍል (በግምት ከ4-9 ቁጥሮች) ለማጥናት አታመንታ፡፡ የፕሮጀክቱ ዝርዝሮች በገጽ 10-11 ላይ የተካተቱ ሲሆን በዚህ ትምህርት መግቢያ ክፍል ውስጥ ይብራራሉ ፡፡ እኛ የምንጠብቀው ሁሉም ተማሪዎች ትምህርታቸውን በሕይወታቸው ውስጥ እና በአገልግሎት ድርሻቸው ላይ በተጨባጭ እንዲተገብሩት ነው ፡፡ ተማሪው የተማራቸውን መርሆዎች ከተግባራዊ አገልግሎት ጋር አጣምሮ የሚኒስትሪ ኘሮጀክት የማዘጋጀት ኃላፊነት አለበት ፡፡ የዚህ ፕሮጀክት ዝርዝሮች በገጽ 12 ላይ የተሸፈኑ ሲሆን በትምህርቱ መግቢያ ክፍል ውስጥ ይብራራሉ ፡፡ የክፍል ሥራ እና የተለያዩ ዓይነት የቤት ሥራዎች በክፍል ትምህርት ወቅት በመምህርህ ሊሰጡህ ወይም በተማሪው መልመጃ (Student Workbook) ውስጥ ሊጻፉ ይችላሉ፡፡ ስለሚፈለገው ነገርም ሆነ የቤት ስራ ስለ ማስረከቢያው ጊዜ ጥያቄ ካለህ መምህርህን ጠይቅ። ለክፍል ውይይት ለመዘጋጀት ተማሪው የተመደበውን ንባብ ከጽሑፉ እና ከቅዱሳት መጻሕፍት ማንበቡ አስፈላጊ ነው ፡፡ እባክህ በየሳምንቱ ከአንተ የተማሪው የመልመጃ መጽሐፍ ውስጥ “የንባብ ማጠናቀቂያ ቅጽ” ን ተመልከት። ለሚደረጉ ተጨማሪ ንባቦች ተጨማሪ ዋጋ/ነጥብ የማግኘት እድል ይኖራል ፡፡ በትምህርቱ መጨረሻ ላይ መምህርህ በቤት ውስጥ የሚጠናቀቅ የመጨረሻ ፈተና (የተዘጋ መጽሐፍ) ይሰጥሃል። በትምህርቱ ውስጥ የተማርከውን እና በአገልግሎትህ ላይ ያለህን አስተሳሰብ ወይም አሠራር እንዴት እንደሚነካው እንድታንጸባርቅ የሚረዳ ጥያቄ ትጠየቃለህ፡፡ ስለ መጨረሻው ፈተና እና ሌሎች ጉዳዮች መምህርህ አስፈላጊውን መረጃዎች ይሰጥሃል።
የሚኒስትሪ ፕሮጀክት
የክፍል እና የቤት ሥራ ምደባዎች
ንባቦች
ከቤት-የሚሰራ የማጠቃለያ ፈተና
ውጤት አሰጥጥ የሚከተሉት ውጤቶች በክፍለ-ጊዜው መጨረሻ ላይ በዚህ ክፍል ውስጥ ይሰጣሉ እናም በእያንዳንዱ ተማሪ መዝገብ ላይ ይቀመጣሉ።
A - የላቀ ሥራ
D - የማለፊያ ሥራ
B - በጣም ጥሩ ሥራ
F - አጥጋቢ ያልሆነ ሥራ
C - አጥጋቢ ሥራ
I - ያልተሟላ
ለእያንዳንዱ የመጨረሻ ክፍል አግባብነት ያላቸው ውጤቶች ይሰጣቸዋል ፣ ለእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ የሚሰጠው የክፍል ነጥብ በጠቅላላው አማካይነት ውጤት ላይ የሚታሰብ ይሆናል። ያልተፈቀደ የስራ መዘግየት ወይም ሥራዎችን አለማስረከብ በውጤትህ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ፣ ስለሆነም እባክህ አስቀድመህ አቅደህ ከመምህርህ ጋር ተነጋገር።
1 0 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
የኤክሴጄሲስ ፕሮጀክት በካፕስቶን ፋውንዴሽን የክርስቲያናዊ ሚሽን የጥናት ሞጁል ተሳታፊ እንደመሆንህ መጠን ከሚከተሉት ንባቦች በአንዱ ላይ የክርስቲያን ሚሽን እና የከተማ አገልግሎት ምንነት ላይ ኤክሴጄሲስ (ኢንደክቲቭ ጥናት) እንድትሰራ ትጠየቃለህ። መዝሙር 19: 7-11 2 ጢሞቴዎስ 3:14-17 1 ቆሮንቶስ 2.9-16 መዝሙር 1: 1-3 ማቴዎስ 22፡34-40 ያዕቆብ 1: 22-25 ኢሳይያስ 55: 8-11 2 ጴጥሮስ 1: 19-21 ምሳሌ 2: 1-5 የዚህ የትርጓሜ ፕሮጀክት (እክሴጀሲስ) ዓላማ ስለ ክርስቲያናዊ ሚሽን ምንነት እና አሠራር የዋና ምንባብ ዝርዝር ጥናት ለማካሄድ እድል ለመስጠት ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚሽን አምላክ መሆኑን ማየት ለእያንዳንዱ የከተማ አገልግሎት ደረጃ መሠረታዊ ነው፡፡ ሚሽን ሰዎች ለተወሰነ ጊዜ ወደ ባህር ማዶ ሄደው ለተወሰነ ወቅት ብቻ የሚሰሩት ሥራ አይደለም፡፡ ይልቁንም ሚሽን እግዚአብሔር በዚህ ምድር ላይ የሚሰራው ስራ እስትንፋስና የአይሁድ-ክርስቲያናዊ የዓለም ምልከታ መሰረት ነው። በአንድ በኩል ጠቅላላው የክርስትና ታሪክ እግዚአብሔር የርሱ የሆኑትን ከአለም ወደራሱ ለመሳብ ያደረገውን መመልከት እንችላለን፤ ሚሽን የኛ ስራ የመሆኑን ያህል የእግዚአብሔርም ስራና የልቡ ፈቃድ ነው። የዚህ ጥናት ዓላማ አንተ ከላይ ከተጠቀሱት ፅሁፎች አንዱን በመምረጥ ስለ ሚሽን - መሠረቱን ፣ አሰራሩን እና ለከተሞች ክርስቲያናዊ አመራር ያለውን ጠቀሜታ በጥልቀት ለመመልከት እንደ መነፅር እንድትጠቀምበት ነው፡፡ ከእነዚህ ንባቦች ውስጥ አንዱን ስታጠና (ወይም አንተ እና የአንተ መምህር የተስማማችሁበትን) ለክርስቲያናዊ ሚሽን መሠረት የሆነውን ቁልፍ ገጽታ እንደምትገነዘብ ተስፋ በማድረግ ነው፡፡ እንግዲህ ይሄን ከራስህ የግል የደቀመዝሙርነት ጉዞ ጋር እንዲሁም እግዚአብሔር በቤተክርስቲያንህ እና በአገልግሎትህ ውስጥ ከሰጠህ የመሪነት ሚና ጋር በቀጥታ እንዴት እንደምታዛምደው መንፈስ ቅዱስ ጥልቅ መረዳት እንዲሰጥህ እንመኛለን ፡፡ ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮጀክት እንደመሆኑ የትርጓሜ ጥናት (ኤክሴጄሲስ) ለመስራት የጥናት ክፍሉን በአውዱ ውስጥ መረዳት ያስፈልጋል። በመቀጠልም ዋናውን ትርጉም ከተረዳህ በኋላ ለሁላችንም ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል መርህ ማውጣትና ይህንም በተጨባጭ ከህይወት ጋር ማዛመድ ይኖርብሃል። ይህን የግል የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጥናት በምታደርግበት ወቅት እነዚህ ሶስት ደረጃዎች ሊያግዙህ ይችላሉ:- 1. በተሰጠው ምንባብ ውስጥ ለተጠቀሱት ዋና አድማጮች እግዚአብሔር መናገር የፈለገው ምንድነው? 2. ከዚህ ምንባብ ልንማረው የምንችለውና ለሁሉም ዘመንና በየትኛውም ቦታ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ ልንወስደው የምንችለው መርህ ምንድነው? 3. ዛሬም መንፈስ ቅዱስ እኔን ከተማርኩት መርህ በመነሳት ምን እንዳደርግ ነው የሚፈልግብኝ? እንግዲህ እነዚህን ጥያቄዎች በተገቢው መንገድ ከመለስክ በቀጣይ ለወረቀት ስራህ የግልህን መረዳት ለማቅረብ ዝግጁ ነህ ማለት ነው። ለወረቀት ስራህ ይህን ቅደም ተከተል ተከትሎ መስራት ይረዳሃል፥
ዓላማ
ዝርዝር መግለጫ እና አወቃቀር
1. የመረጥከው የንባብ ክፍል ዋና ጭብጥ ወይም ሃሳብ ምን እንደሆነ ለይተህ አስቀምጥ።
/ 1 1
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
2. የምንባቡን ዋና ትርጉም በአጭሩ ግለጽ (ይህን በሁለት ወይም በሶስት አንቀጽ ልታስቀምጠው ትችላለህ ወይም ደግሞ በእያንዳንዱ ቁጥር አጫጭር ማጣቀሻ ወይም ማመሳከሪያ እየተጠቀምክ መሄድ ትችላለህ።) 3. ይህ የምንባብ ክፍል ሊሰጠን የሚችሉ ከአንድ እስከ ሶስት የሚደርሱ የክርስቲያን ሚሽን መርሆዎችን ዘርዝር። 4. ከመርሆዎቹ ውስጥ አንዱ፣ የተወሰኑት ወይም በጠቅላላው ከሚከተሉት ነጥቦች ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ አሳይ፥ ሀ. ከአንተ የግል መንፈሳዊ ህይወት እና ከጌታ ጋር ካለህ ጉዞ ጋር ሐ. ባለህበት ማህበረሰብም ሆነ በጠቅላላው ህብረተሰብ ውስጥ ከሚንጸባረቁ ሁኔታዎችና ችግሮች ጋር የዚህን ትምህርት (ሞጁል) መጽሐፍ እና ማጣቀሻዎችን እንደ መመሪያና እንደ መርጃ ለመጠቀም ነጻነት ይኑርህ፤ ይህን በምታደርግበት ወቅት ግን የሌላን ሰው ምልከታ ከተዋስክ ወይም በዛ ምልከታ ላይ የራስህን ከመሰረትክ ለባለሃሳቡ ዕውቅና መስጠትን መዘንጋት የለብህም። ለዚህም የጽሁፍ ውስጥ ማጣቀሻዎችን፣ የግርጌ ማስታወሻዎችን፣ ወይም የመጨረሻ ማስታወሻዎችን ተጠቀም። የተጠቀምከው የማስታወሻ ዘዴ ተቀባይነት የሚኖረው 1) በጠቅላላው የጽሁፍ ስራህ ውስጥ ወጥነት ያለው ሲሆንና 2) የተጠቀምከውን የሌላን ሰው ሃሳብ በትክክል የሚያመለክት ሲሆንና ተገቢውን እውቅና ሲሰጥ ብቻ ነው ፡፡(ለተጨማሪ መረጃ ከአባሪዎች ገጽ ላይ Documenting Your Work : A guide to Help You Give Credit Where Credit is Due ተመልከት ፡፡) የትርጓሜ ጥናቱ (ኤክሴጄቲካል ፕሮጀክቱ) የሚከተሉትን መመዘኛዎች የሚያሟላ መሆኑን አረጋግጥ:- • በአግባቡ መጻፉን(ታይፕ መደረጉን) • ከላይ ከተሰጡት ምንባቦች የአንዱ ጥናት መሆኑን • ሳይዘገይ በቀኑና በሰኣቱ ገቢ መደረጉን • ርዘመቱ 5 ገጽ መሆኑን • ከላይ የተሰጠውን መመሪያ ተከትሎ መሰራቱንና አንባቢው በቀላሉ ተከትሎ ሊረዳው የሚችል መሆኑን • ምንባቡ ከህይወትና ከአገልግሎት ጋር ያላቸውን ዝምድና የሚያሳይ መሆኑን እነዚህን መመሪያዎች አይተህ አትደናገጥ፤ ይህ የመጽሀፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮጀክት ነው፤ ማድረግ የሚያስፈልግህ ምንባቡን በደንብ ማጥናት፤ ከምንባቡ ውስጥ ትርጉም መፈለግ፤ ከዚያም ቁልፍ የሆኑ መርሆዎችን ከምነባቡ ማውጣት እና መርሆዎቹንም ከህይወትና ከአገልግሎት ጋር ማዛመድ ናቸው፡፡ ይህ የትርጓሜ ጥናት (ኤክሴጄቲካል ፕሮጀክት) የ45 ነጥቦች ዋጋ ያለው ሲሆን ከጠቅላላው የዚህ ኮርስ ውጤት 15% ይይዛል፡፡ ስለዚህ በተቻለህ መጠን ስራህን የላቀና አስተማሪ አድርገሀ ለማቅረብ ሞክር፡፡ ለ. በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ካለህ አገልግሎት ጋር
ምዘና
1 2 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
የሚኒስትሪ ፕሮጀክት የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤” (ዕብራውያን 4፡12)፡፡ ሐዋሪያው ያዕቆብ ሰሚዎች ብቻ ሳይሆን አድራጊዎችም ጭምር እንድንሆን አጽንኦት ሰጥቶ ይናገራል፡፡ ቃሉን በተግባር ላይ እንድናውለውም ይመክረናል፡ ፡ ይህን ልምምድ መዘንጋት የተፈጥሮ ፊታችንን በመስታውት ውስጥ ተመልክተን ወዲያው ማንነታችንን ከመርሳት ጋር ያመሳስለዋል፡፡ በማንኛውም ሁኔታ የእግዚአብሔርን ቃል የሚያደርግ ሰው በነገር ሁሉ ይባረካል (ያዕቆብ 1፡22-25)፡፡ እኛም መሻታችን የምንቀስመውን ትምህርት በግል ህይወትህ፣ በአገልግሎትህና በቤተክርስቲያንህ ውስት ካሉ ተጨባጭ ሁኔታዎችና ፍላጎቶች ጋር በማዛመድ በተግባር ስታውለው መመልከት ነው፡ ፡ በመሆኑም የዚህ ትምህርት (ኮርስ) ዋና ዓላማ ከዚህ ኮርስ የተማርካቸውን ነገሮች ከሌሎች ጋር ልትከፋፈልበት የምትችልበት የሚኒስትሪ ፕሮጀክት መቅረጽ እንድትችል ነው፡፡ የዚህን ጥናት መመዘኛዎች ለማሟላት ብዙ አማራጮች አሉህ፡፡ ከሰንበት ትምህርት ቤት የወጣቶች ወይም አዋቂዎች የመጽሀፍ ቅዱስ ጥናት ወይም ማንኛውም አገልግሎት ዘርፍ ላይ ተመስርተህ አጠር ያለ ጥናት ማካሄድ ትችላለህ፡፡ እዚህ ጋር የግድ ማድረግ የሚኖርብህ ነገር ቢኖር ከነበረህ የትምህርት ክፍለ ጊዜ የተማርካቸውን ነጥቦች ከአድማጭህ ጋር መወያየት ነው፡፡ (በእርግጥ የምታካፍላቸውን ነጥቦች ከትርጓሜ ጥናትህም መውሰድ ትችላለህ፡፡) በእያንዳንዱ የፕሮጀክት ስራህ ነጻነትህን ተጠቅመህ ሳቢና ግልፅ ለማድረግ ሞክር፡፡ በዚህ ኮርስ መጀመሪያ ሀሳብህን የምታካፍልበትን ሁኔታ (አውድ) በመወሰን ለመምህርህ ማሳወቅ ይኖርብሃል፡፡ ለዚህም ፕሮጀክትህ ይህን ዝርዝርና ቅደም ተከተል በመጠቀም ሊዘጋጅ ይችላል፡፡
ዓላማ
እቅድ እና ማጠቃለያ
1. ሙሉ ስም 2. የት እና ከማን ጋር የመከፋፈል ጊዜ እንደነበረህ 3. ስለነበራቹ ጊዜ ምን እንደተሰማህና ስለነሱ ምላሽ አጠር ያለ ማብራሪያ 4. ከነበራቹ ጊዜ ስለተማርከው ነገር
ይህ የሚኒስትሪ ፕሮጀክት የ30 ነጥቦች ዋጋ ያለው ሲሆን ከጠቅላላው የዚህ ኮርስ ውጤት 10% ይይዛል፡፡ ስለዚህ ሃሳብህን በልበ ሙሉነት ማካፈልህንና ግልጽ የሆነ ማብራሪያ ማቅረብህን እርግጠኛ መሆን ይኖርብሃል፡፡
ምዘና
/ 1 3
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
መጽሐፍ ቅዱሳዊ እስትንፋሰ እግዚአብሔር የመጽሐፍ ቅዱስ አመጣጥና ሥልጣን
ትምህርት 1
ገጽ 291 1
ሃያል በሆነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን ! የዚህን ትምህርት መጽሐፍ ካነበብክ፥ ካጠናህ፥ ውይይት ካካሄድክና ወደ ተግባር ከቀየርከው በኋላ የሚከተሉትን ማድረግ ትችላለህ:- • ስነ አፈታትን እንደ አንድ በትርጓሜ ላይ፣ በተለይም በምንባቦች ትርጓሜ ላይ እንደሚያተኩር የጥናት እና የእውቀት ዘርፍ መግለጽ ትችላለህ፣ ። • የመጽሐፍ ቅዱስን ምንነት ለመገንዘብና ሙሉ በሙሉ ለመረዳት መጽሐፍ ቅዱስ መለኮታዊና ሰዋዊ መጽሐፍ እንደሆነ ተደርጎ መተርጎም እንዳለበት ማስረጃ ትሰጣለህ። • ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት መለኮታዊ መምጫቸው፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን መተርጎም፣ ሂደታዊ የመገለጥ ሀሳብ፣ በክርስቶስ ላይ ያተኮረ የመጽሐፍ ቅዱስ ተፈጥሮ እና የእግዚአብሔርን ቃል ለመረዳት የመንፈስ ቅዱስ አስፈላጊነት ጨምሮ በታሪካዊ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያኖች ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት ተፈጥሮ ያመኑትን ወሳኝ ቅድመ-ሁኔታዎች ማብራራት ትችላለህ። • የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜን የሶስት ደረጃ ሞዴል አጠቃላይ እይታ ትሰጣለህ፣ ይህም የቀደመውን ሁኔታ መረዳትን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ መርሆችን መመርመርን እና የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጉም በሕይወታችን ላይ ተግባራዊ ማድረግን ያካትታል። • ለመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ልብን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉትን የተለያዩ ነገሮች ማለትም ትሕትናንና ጸሎትን፣ ትጋትንና ቁርጠኝነትን እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስን እንደ ትጉህ ሰራተኛ በጥንቃቄ ማጥናት አስፈላጊ መሆኑን መግለጽ ትችላለህ። • አእምሯችንን ለትልቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ስናዘጋጅ ሊኖረን ስለሚገባው ሚና ግንዛቤ እንዳለህ ማሳየት ትችላለህ፤ ይህ ሚና ደግሞ ቃሉን በትጋት መፈለግ፣ ፍንጮችን በመከተል እንዲሁም ማስረጃዎቹን በጥንቃቄ በመመዘን ውሳኔ ከማስተላለፍህ በፊት የመመርመርን ሚና ይጨምራል። • መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር መንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ ከመሆኑም በላይ በሰዎች የተጻፈ መሆኑን ከቅዱሳት ጽሑፎች በመነሳት ማስረዳት ትችላለህ። • ቅዱሳት መጻሕፍት በመንፈስ ቅዱስ እንዴትና በምን መንገድ እንደተጻፉ እንዲሁም እንዴት በጸሐፊዎቹ ሰዎች ተጽዕኖ እንደተደረገባቸው ለመግለጽ የሚጥሩትን የተለያዩ የመንፈስ አነሳሽነት ንድፈ ሐሳቦች መግለጽ ትችላለህ። • ምክንያታዊ እና ታሪካዊ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትችት በጥንቃቄ ማቅረብ ትችላለህ፤ እንዲሁም ይህ ዘመናዊው ትችት እንዴት የመጽሐፍ ቅዱስን አመጣጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጠቀሱት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች አንስቶ በመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖናዊ መጻሕፍት ውስጥ እስከተዘገቡት ክስተቶች ድረስ በመከታተል እንደሚያዛምድ ማሳየት ትችላለህ።
የትምህርቱ አላማ
ገጽ 293 2
1
1 4 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
• በዘመናዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትችት ዋና ዋና ንዑስ ክፍሎች ማለትም ቅርጽ፣ ምንጭ፣ ስነ ቋንቋ፣ የጽሑፍ፣ የሥነ ጽሑፍ፣ ቀኖና፣ ቅነሳዊ የትርጉም ጥናቶችን ጨምሮ ጥቅሞቹንና ችግሮቹን በአጭሩ መግለጽ ትችላለህ።
መተማመኛ መሰረታችን ኢሳ. 55.6-11 - “እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፥ ቀርቦም ሳለ ጥሩት፤ ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን ይተው፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ እርሱም ይምረዋል፥ ይቅርታውም ብዙ ነውና ወደ አምላካችን ይመለስ። አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና፥ ይላል እግዚአብሔር። ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው። ዝናብና በረዶ ከሰማይ እንደሚወርድ፥ ምድርን እንደሚያረካት፥ ታበቅልና ታፈራም ዘንድ እንደሚያደርጋት፥ ዘርንም ለሚዘራ እንጀራንም ለሚበላ እንደሚሰጥ እንጂ ወደ ሰማይ እንደማይመለስ፥ ከአፌ የሚወጣ ቃሌ እንዲሁ ይሆናል፤ የምሻውን ያደርጋል የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም።” እግዚአብሔር ፍጹም ጽኑ አቋሙንና እውነቱን ሲናገር አያመቻምችም። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት የታመነና ታማኝ አምላክ ነው፣ ፈጽሞ የማይዋሽ ወይም የማያሳስት፣ ቃሉ ፍጹም እውነት የሆነ፣ ሉዓላዊነቱና እውነቱ ለሕዝቡ ታላቅ መተማመንን የሚሰጥ አምላክ ነው። ስለ እግዚአብሔር ታማኝነት አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ስንመለከት እንኳን፣ እግዚአብሔር የቅዱሳት መጻህፍትንና የተስፋ ቃሉን የማድረግ ኃይል በድፍረት ያወጀ ታማኝ የቃል ኪዳን ቃል አምላክ ነው። የዚህ በእግዚአብሔር ቃል ላይ የመተማመን ምሳሌ እነሆ፡- መዝ. 19፡7-10 - “የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ነፍስን ይመልሳል፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል። የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው፥ ልብንም ደስ ያሰኛል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፥ ዓይንንም ያበራል። የእግዚአብሔር ፍርሃት ንጹሕ ነው፤ ለዘላለም ይኖራል፤ የእግዚአብሔር ፍርድ እውነትና ቅንነት በአንድነት ነው። ከወርቅና ከክቡር ዕንቍ ይልቅ ይወደዳል፤ ከማርና ከማር ወለላም ይጣፍጣል።” ዘዳ. 32.4 – “እርሱ አምላክ ነው፤ ሥራውም ፍጹም ነው፤ መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፤ የታመነ አምላክ፥ ክፋትም የሌለበት፥ እርሱ እውነተኛና ቅን ነው።” ዘጸ. 34.6 – “እግዚአብሔርም በፊቱ አልፎ፦ እግዚአብሔር፥ እግዚአብሔር መሐሪ፥ ሞገስ ያለው፥ ታጋሽም፥ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት፥” መዝ. 98.3 – “ለያዕቆብ ምሕረቱን ለእስራኤልም ቤት እውነቱን አሰበ፤ የምድር ዳርቻዎች ሁሉ የአምላካችንን ማዳን አዩ።”
ጥሞና
ገጽ 293 3
1
መዝ. 100.5 - “እግዚአብሔር ቸር፥ ምሕረቱም ለዘላለም፥ እውነቱም ለልጅ ልጅ ነውና።”
ኢሳ. 25.1 – “አቤቱ፥ አንተ አምላኬ ነህ፤ ድንቅን ነገር የዱሮ ምክርን በታማኝነትና በእውነት አድርገሃልና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ ስምህንም አመሰግናለሁ።” ዮሐንስ 6፡63 - “ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።”
/ 1 5
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
1 ጴጥ. 1.23-25 - “ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ። ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤ የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል። በወንጌልም የተሰበከላችሁ ቃል ይህ ነው። በዚህ መጠነኛ ዝርዝር ውስጥ ስለ እግዚአብሔር ታማኝነት ተጨማሪ ቅዱሳት መጻሕፍትን ጨምር እና በኢሳይያስ 55 ሃሳብ ላይ ሙሉ ወደሆነ ግንዛቤ ትደርሳለህ። እግዚአብሔር የቃሉን ፍጻሜ እርግጠኝነት በትንቢቱም ሆነ በተስፋው መሠረት ከዘርና ከምድር ጋር ተደባልቆ ብዙ ፍሬ ከሚያፈራው ከሰማይ ዝናብ ተፈጥሯዊ ኃይል ጋር ያነፃፅራል። ዝናብ ከምድር ንጥረ ነገሮች ጋር እንደሚደባለቅ ሁሉ እግዚአብሔር ቃሉም ፍሬያማ፣ እርግጠኛ፣ የተሳካ እና ኃያል እንደሆነ ተናግሯል። ይህን ከእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ቃል ጋር የተያያዘ የፍሬያማነት እና የብልጽግና ተስፋ፣ የውጤት እርግጠኝነት በምን እንቆጥረዋለን? በባሕርይው፣ በማንነቱ፣ በእውነተኛነቱ እንደ ታማኝ አምላክ፣ የማይዋሽ አምላክ (ቲቶ 1.2)፣ ቃሉ የተረጋገጠና የታመነ፣ ለዘላለም በሰማያት የተቀመጠ ነው። ዳዊት በመዝሙር 89 ላይ ስለ እግዚአብሔር ታማኝነት እና ስለ ቃሉ ታማኝነት ዘምሯል፡- “አቤቱ፥ ምሕረትህን ለዘላለም እዘምራለሁ፥ እውነትህንም በአፌ ለልጅ ልጅ እናገራለሁ። እንዲህ ብለሃልና፦ ምሕረት ለዘላለም ይመሠረታል፥ እውነትህም በሰማይ ይጸናል።” (መዝ. 89፡1-2)። በዚህ ጽሑፍ ውስጥ እግዚአብሔር ቃሉ እውነት መሆኑን አረጋግጦልናል። እግዚአብሔር ታማኝ አምላክ ስለሆነ ቃሉ እርሱ የወሰነውን ይፈጽማል፣ እርሱም ያደርገው ዘንድ በሾመው ነገር ላይ ይፈጸማል። ልጠይቅህ፡ እግዚአብሔር የገባልን ቃል ሁሉ በእርግጥም እንደሚፈጸም የመተማመኛ መሰረታችን ምንድን ነው - በምን ምክንያት፣ በምን መሰረት፣ በኢየሱስ ክርስቶስ የተገባልንን ህይወት በእምነት እንደምናጭድ እንዴት እናምናለን? መልሱ እውነተኝነት ለህዝቡ እውነትን የተናገረው የህያው አምላክ እውነተኛ ባህሪ መሆኑ ነው። አምላካችን የእውነት አምላክ ነው፤ ስለዚህም የገባውን ቃል እንደሚፈጽም አውቀን የተስፋ ቃሉን እንጠባበቃለን። ይህ እና ይህ ብቻ መተማመኛ መሠረታችን ነው። የኒቂያን የእምነት መግለጫ (በአባሪው ውስጥ ይገኛል) ካነበብክ እና/ወይም ከዘመርክ በኋላ የሚከተለውን ጸሎት ጸልይ፥ ቅዱሳት መጻሕፍትን ሁሉ ለትምህርታችን እንዲጻፉ ያደረግህ ብሩክ ጌታ፡ አንተ የሰጠኸንን የተባረከውን የዘላለም ሕይወት ተስፋ እንድንሰማ፣ እንድናነብብ፣ እንድንቀበል፣ እንድንማር፣ እና እንድናሰላስላቸው፣ አጥብቀንም እንይዛቸው ዘንድ ከአንተ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በሚኖርና በሚነግሥ አንድ አምላክ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስጠን፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም። አሜን። ~ Episcopal Church. The Book of Common Prayer and Administrations of the Sacraments and Other Rites and Ceremonies of the Church, Together with the Psalter or Psalms of David. New York: The Church Hymnal Corporation, 1979. p. 236
1
የኒቂያ የእምነት መግለጫ እና ጸሎት
1 6 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
ይህ ትምህርት ፈተና የለውም
ፈተና
የቃል ጥናት ጥቅስ ምዘና
ይህን ትምህርት የቃል ጥናት ጥቅስ የለውም
የቤት ስራ/መልመጃ ማስረከቢያ
ይህ ትምህርት የቤት ስራ/መልመጃ የለውም
1
እውቂያ
ለምን ግድ ሊለን ይገባል?
በዛሬው ጊዜ ያሉ ብዙ ሰዎች ሳይንስ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነተኛነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዳከሸፈ ያምናሉ፤ ቢያንስ ቢያንስ ከታሪክና ከተፈጥሮ በላይ ካሉት ኃይሎች ጋር በተያያዘ። መጽሐፍ ቅዱስን በቅንነት የሚያጠኑ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ቅን የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪካዊ ትክክለኛነት እና እውነት ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምንነት ለሚጠራጠሩ ሰዎች ማረጋገጥ ግዴታቸው እንደሆነ ያምናሉ። ቅዱሳት መጻሕፍት በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የተጻፉ መሆናቸውን የሚያረጋግጡ የትንቢት ፍጻሜዎች፣ የትንበያዎቹ ትክክለኛነት፣ እርስበርሳቸው ያላቸው ተያያዥነት እና ተጠብቀው መቆየታቸውን እንደማስረጃ ያነሳሉ። በሌላ በኩል ደግሞ እንዲሁ ቅን ነገር ግን ድምጻቸው አናሳ የሆነ የክርስቲያን ቡድኖች ቅዱሳት መጻሕፍትን ለማያምኑት ታሪካዊ እና መንፈሳዊ ትክክለኛነትን በማስረጃ በማቅረብ ማሳመን እንደማይችሉ በእርግጠኝነት ይሞግታሉ። ያለ መንፈስ ቅዱስ እርዳታ ማንም ሰው ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ታማኝነት ከማያምኑት ጋር በመሟገት እርግጠኛ መሆን ይቅርና እግዚአብሔር በክርስቶስ ያሰጠውን የተስፋ ቃል መቼም አያምንም በማለት ይከራከራሉ። እንግዲህ እነዚህን አመለካከቶች ስትመረምር የመጽሐፍ ቅዱስ አመጣጥ፣ ሥልጣንና በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ መሆን አለመሆኑ ሊያሳስበን ይገባል ብለህ የምታስበው ለምንድን ነው? ቅዱሳት መጻሕፍት እና መንፈስ ቅዱስ የወንጌላውያን እምነት ተከታዮች መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት ጥሩ ዘዴዎችንና መሠረታዊ ሥርዓቶችን መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን የሚገልጹ በሺዎች የሚቆጠሩ መጻሕፍትን ጽፈዋል። አንድ ሰው ወደ የትኛውም የክርስትና የመጽሐፍት መደብር ወይም ቤተ መጻሕፍት ቢሄድ የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጉም ‘በግልጽና ቃል በቃል’ ለመረዳት ሊወስዷቸው የሚገቡትን እርምጃዎች በተመለከተ ዝርዝር መመሪያ የሚሰጡ በርካታ ጥቅሶችን ያገኛል። እነዚህ ሁሉ መጻሕፍት ቢኖሩም አሁንም ቢሆን ብዙ አብያተ ክርስቲያናት የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት እንደሌላቸው የሚያሳዩ ሲሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን እንዴት ማካሄድ እንደሚቻል ጥሩ ዘዴዎች ቢኖሩም መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ከሌሎች የበለጠ የሚወዱ ወይም የሚያነቡ አይመስሉም። አንዳንዶች የመንፈስ ቅዱስ አመራርና ሙላት ከሌለ አንዳንድ ዘዴዎችና አቀራረቦች ትርጉም እንደሌላቸው ይናገራሉ። እነዚህ ሰዎች የትርጓሜ ዘዴዎችን ሙሉ በሙሉ ያጣጥሉና አዕምሯዊ ልኬቶችን ሳይሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ መንፈሳዊ ልኬቶችን ደግሞ
1
ገጽ 295 4
2
/ 1 7
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
ያጎላሉ። የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ውስጥ በመጽሐፍ ቅዱስ የአተረጓጎም ዘዴ እና የመጽሐፍ ቅዱስ ባለቤት በሆነው የመንፈስ ቅዱስ ሥራ መካከል ያለው ግንኙነት ምንድን ነው? ምንም እንኳን ጥሩ የስነ አፈታት ዘዴዎች ቢኖሩንም ያለ መንፈስ ቅዱስ ብርሃን መጽሐፍ ቅዱስን ትርጉም ባለውና ሕይወትን በሚቀይር መንገድ መረዳት ይቻላልን?
ሥነ ጽሑፍ ወይስ ሕያው የእግዚአብሔር ቃል ወይስ ሁለቱም? ባለፉት ጥቂት አሥርት ዓመታት ውስጥ የተወሰኑ ምሁራን መጽሐፍ ቅዱስን እንደ ሥነ ጽሑፍ መረዳት ለሕይወታችን ያለውን ትርጉም ለማወቅ እንደሚያስፈልግ አበክረው ተናግረዋል። የሥነ ጽሑፍ ሥራ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሆነም አልሆነ የሚከናወነው በተመሰረቱ ህጎችና ቅርጾች እንደሆነ ይሞግታሉ። እነዚህ ምሁራን መጽሐፍ ቅዱስን እንደ ሰዋዊ መጽሐፍ ባለው ቅርጽና ህጎች መሰረት ከማንበብ ይልቅ መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ትንንሽ ክፍሎች ቆርጠን እንደወሰድነው፣ የሥነ ጽሑፍ ዓይነቶችን ችላ እንዳልን፣ እና መጽሐፍ ቅዱስን በዋናነት እንደ ማስረጃ ተጠቅመን አንድን ወይም ሌላን ሥነ-መለኮታዊ ርዕሰ ጉዳይ ለመሞገት እንደሞከርን ይናገራሉ። አንዳንዶች ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት ሰዎች ቢሆኑም ጽሑፎቹ ከሥነ ጽሑፍ ደንቦችና ቅርጾች ያለፉ እንደሆኑ ይናገራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ስላገኘነው ድነት እና እምነትን በተመለከተ ትርጓሜን ሊሰጠን የሚችል የሕያው የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ ይሞግታሉ። ለእንደዚህ አይነቱ ሙግት የአንተ ምላሽ ምን ሊሆን ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ የሥነ ጽሑፍ መጽሐፍ ነው ወይስ የሕያው የእግዚአብሔር ቃል? ወይስ ሁለቱንም?
3
1
የመጽሐፍ ቅዱስ እስትንፋሰ እግዚአብሔር፡ የመጽሐፍ ቅዱስ አመጣጥ እና ሥልጣን ክፍል 1፡ ጠጠር ላለ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጓሜ መዘጋጀት
ይዘት
ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ
ስነ አፈታት በትርጓሜ ላይ፣ በተለይም በምንባቦች ትርጓሜ ላይ የሚያተኩር የጥናት እና የእውቀት ዘርፍ ነው። ሂርሜኔዩቲክስ እንደ ስነ አፈታት ዘዴ መጽሐፍ ቅዱስን እንደ መለኮታዊ እና እንደ ሰዋዊ መጽሐፍ ለመተርጎም መሄድ ስላለበት መንገድ ለመረዳት ይፈልጋል፣ የቅዱሳት መጻሕፍትን ተፈጥሮ ለመገንዘብ እና ሙሉ በሙሉ ለመረዳት ሁለቱም ልኬቶች ያስፈልጋሉ። ታሪካዊ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ከመጀመሪያው ጀምሮ በቅዱሳት መጻሕፍት ተነሳሽነት፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን በቅዱሳት መጻሕፍት የመተርጎም አስፈላጊነት እና በክርስቶስ መገለጥ ስለሚጠናቀቅ ሂደታዊ የመገለጥ ሀሳብ ያምናሉ። ቅዱሳት መጻሕፍትን መረዳት የሚቻለው በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ብቻ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ የሶስት ደረጃ ሞዴል የመጀመሪያውን ሁኔታ መረዳትን፣ የመጽሐፍ ቅዱስን መርሆች መመርመርን እና የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጉም በሕይወታችን ውስጥ ተግባራዊ ማድረግን ያካትታል። የእግዚአብሔርን ቃል በትክክል ለመተርጎም ልባችንን፣ አእምሯችንንና ፈቃዳችንን በማዘጋጀት በትሕትናና በጥንቃቄ ማጥናት፣ በጥንቃቄ መመርመርና ከልብ መታዘዝ ይኖርብናል፤ ይህም ለእግዚአብሔር ክብርን ያመጣል።
የክፍል 1 አጭር ማብራሪያ
1 8 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
የዚህ ክፍል ዓላማችን ጠጣር ስለሆነው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጓሜ መዘጋጀትን በተመለከተ የሚከተሉትን ነጥቦች እንድትገነዘብ ማስቻል ነው፦ • ስነ አፈታት በትርጓሜ ላይ፣ በተለይም በምንባቦች ትርጓሜ ላይ የሚያተኩር የጥናት እና የእውቀት ዘርፍ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜዎች በተለይ መጽሐፍ ቅዱስን ለመተርጎም በሚያስችሉ ዘዴዎችና ሳይንስ ላይ ያተኩራሉ። • መጽሐፍ ቅዱስን እንደ መለኮታዊም ሆነ እንደ ሰዋዊ መጽሐፍ መተርጎም ያስፈልጋል፤ እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስን ምንነት ሙሉ በሙሉ ለመረዳት መለኮታዊም ሆነ ሰዋዊ ባሕርያትን መገንዘብ ያስፈልጋል። • ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት መለኮታዊ አመጣጥ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ስለመተርጎም፣ ሂደታዊ የመገለጥ ሀሳብ፣ በክርስቶስ ላይ ያተኮረ የመጽሐፍ ቅዱስ ተፈጥሮ እና የእግዚአብሔርን ቃል ለመረዳት የመንፈስ ቅዱስ አስፈላጊነት ጨምሮ ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት ተፈጥሮ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያኖች ከመጀመሪያው አንስቶ ያመኑባቸውን ወሳኝ ቅድመ-ሁኔታዎችን አስቀምጠዋል። • የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜን የሶስት ደረጃ ሞዴል አጠቃላይ እይታ ትሰጣለህ፣ ይህም የቀደመውን ሁኔታ መረዳትን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ መርሆችን መመርመርን እና የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጉም በሕይወታችን ላይ ተግባራዊ ማድረግን • የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ የሦስት ደረጃ ሞዴል በሥነ ጽሑፉ ዓለም እና በዘመናዊው ዓለም መካከል ያለውን ታሪካዊ እና የቋንቋ ልዩነት በቁም ነገር ለመውሰድ የሚፈልግ ሲሆን መልእክቱን ከመጀመሪያው ሁኔታ አንጻር ለመረዳት ፣ ከመጽሐፉ የመጽሐፍ ቅዱስ መርሆችን ለማግኘት እና በመጨረሻም የቅዱሳት መጻሕፍትን ትርጉም በሕይወታችን ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ ጥረቶችን ማድረግን ያካትታል ። • የእግዚአብሔርን ቃል በትክክል ለመተርጎም ልባችንን፣ አእምሯችንንና ፈቃዳችንን በማዘጋጀት በትሕትናና በጥንቃቄ ማጥናት፣ በጥንቃቄ መመርመርና ከልብ መታዘዝ ይኖርብናል፤ ይህም ለእግዚአብሔር ክብርን ያመጣል። • ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር እንደ ትጉ ሰራተኛ በትህትና እና በጸሎት፣ በትጋት እና በቆራጥነት እና ጥብቅ ተሳትፎ ልባችንን ማዘጋጀት አለብን። መጽሐፍ ቅዱስን በጥንቃቄ በመመርመርና ማስረጃዎችን በጥንቃቄ በመመዘን ቃሉን በመስማት ብቻ ሳይሆን በመታዘዝ ፈቃዳችንን ማዘጋጀት፣ እንዲሁም ጥበብ የሚገኘው ቃሉን በማሰላሰል ብቻ ሳይሆን ለእሱ ምላሽ በመስጠት እንደሆነ የሚገልጸውን እውነት መቀበል ይኖርብናል።
1
/ 1 9
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
I. የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ አስፈላጊነት
የቪዲዮ ሴግመንት 1 መግለጫ
ሀ. የመግቢያ ቃላት
1. “ሔርሜነቲክስ” - በስነ ትርጓሜ ላይ፣ በተለይም በጽሁፎች ትርጓሜ ላይ የሚያተኩር የእውቀት ዘርፍ ነው
2. “ትርጓሜ” - የመተርጎም ወይም የማብራራት ድርጊት ነው፤ የአንድን ነገር፣ ሂደት፣ መልእክት፣ ወይም ጽሑፍ ስሜት እና ትርጉም መስጠት
1
ለ. መጽሐፍ ቅዱስ ለምን የግድ መተርጎም አለበት?
1. መጽሐፍ ቅዱስ መለኮታዊ መጽሐፍ ነው፤ ከእግዚአብሔር በቀር የእግዚአብሔርን አሳብ የሚያውቅ የለም፣ 1ኛ ቆሮ. 2.10-11.
ሀ. እግዚአብሔር በግልጽ ተናግሯል፣ ዘዳ. 30፡11-14።
ለ. እግዚአብሔር የተናገረው እርሱን ፈላጊ አእምሮ ያስተውል ዘንድ ነው፣ ኢሳ. 45.19.
ሐ. እግዚአብሔር በሰፊው ተናግሯል (ማለትም፣ እርሱን ለማመን እና ለመታዘዝ ማወቅ ያለብንን ነገሮች ሰጥቶናል)፣ ዘዳ. 29.29.
2. መጽሐፍ ቅዱስ የሰው መጽሐፍ ነው፣ 2ጴጥ. 3፡15-16።
ሀ. የቋንቋ፣ የባህል እና የልምምድ ልዩነቶች አሉ።
2 0 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
ለ. ቅዱሳት መጻሕፍት ከ1,600 ዓመታት በላይ በወሰደ ጊዜ ውስጥ የተጻፉት በ40 የተለያዩ ጸሐፊያን ነው፣ ልምዳቸውና ግንዛቤያቸው ከእኛ በእጅጉ የተለየ ነው።
3. እግዚአብሔር ቅዱሳት መጻሕፍትን በትክክል እንድንይዝ ይጠይቀናል፤ ያም ማለት እንድንቀበለው ያሰበውን ትርጓሜ ለማግኘት በሚያስችል መንገድ እንድናነብ ነው።
ሀ. 2 ጢሞ. 2.15
1
ለ. 1 ቆሮ. 2.6
ሐ. 2 ቆሮ. 4.2
ሐ. የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ግብ፡ ትርጉሙን ግልጽ እና ቀላል ማድረግ
1. የእውነትን ቃል “በትክክል ለመያዝ”፣ 2ጢሞ. 2.15
2. ትርጓሜ ለመስጠት እና ግልጽ ለማድረግ፣ ነህምያ 8.1-3፣ 7-8
3. እውነትን ለማወቅ እና እግዚአብሔራዊ ነፃነት ለመለማመድ፣ ዮሐ 8፡31-32
4. ለእግዚአብሔር ቃል ካለን ታማኝነት የተነሳ መንፈሳዊ ትርፍ ለማግኘት፣ መዝ. 19፡ 7-11
/ 2 1
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
መ. ወሳኝ ቅድመ-ግምቶች (ቅዱሳት መጻሕፍትን መተርጎም ከመጀመራችን በፊት እንደ እውነት የምንቀበላቸው ነገሮች)
1. ቅዱሳት መጻሕፍት መለኮታዊ እና ሰብዓዊ ደራሲዎች አሏቸው።
2. የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ስለ ኤክሴጄሲስ እንጂ ኢሴሲስ አይደለም።
ሀ. ኤክሴጄሲስ - ከአንድ ጽሑፍ ውስጥ ትርጉሙን ለማብራራት፣ ግልጽ ለማድረግ እና ለመተርጎም መሞከር (ማለትም ከጽሑፉ ውስጥ ማንበብ/ማውጣት)
1
ለ. ኢሴጄሲስ - አንድን ጽሑፍ በተለይም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፍን የራስን ሃሳቦች በመጠቀም ማብራራት እና መተርጎም (ማለትም ወደ ውስጥ ማንበብ)
3. ቅዱሳት መጻሕፍትን ቅዱሳት መጻሕፍት መተርጎም አለባቸው።
ሀ. 1 ቆሮ. 2.13
ለ. ማቴ. 22.29
ሐ. ሉቃ 24፡44-47
4. ሂደታዊ መገለጥ፡ መገለጡ የሚቀጥለው በኢየሱስ ክርስቶስ እስኪጠናቀቅ ድረስ ነው (ማለትም፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የሁሉም ቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜዎች መለኪያ ነው)።
ሀ. ዕብ. 1.1-2
2 2 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
ለ. ማቴ. 17.5
ሐ. ዮሐንስ 1፡17-18
መ. 2 ቆሮ. 4.3-6
5. ቅዱሳት መጻሕፍት በመንፈስ አብርሆት መነበብ አለባቸው።
1
ሀ. 2 ጴጥ. 1.20-21
ለ. ማርቆስ 12፡36
ሐ. የሐዋርያት ሥራ 1፡16
መ. የሐዋርያት ሥራ 3፡18
ሠ. የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ “የሦስት ደረጃ ሞዴል” አጠቃላይ ምልከታ
1. ዋናውን አውድ እና ሁኔታ መረዳት፡ አንድ ጽሑፍ በጭራሽ ማለት ያልፈለገውን ነገር ሊያመለክት አይችልም።
2. አጠቃላይ መርሆችን መፈለግ፡ መንፈስ ከአእምሮ፣ ህሊና እና ፈቃድ ጋር የተያያዙትን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ያሉትን ሁለንተናዊ እውነቶች ይገልጣል።
3. ግንኙነትን መፍጠር እና ተግባራዊ ማድረግ፡- የእግዚአብሔር ቃል የሚመረመርና የሚጠና ብቻ ሳይሆን ሊታመንና ሊጠበቅ የሚገባው ነው።
/ 2 3
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
II. በመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ የልብ ዝግጅት አስፈላጊነት፡ ርኅሩኆች ሁኑ 2ኛ ዜና. 16፡9 ሀ - “እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዓይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና።”
ሀ. ወደ እግዚአብሔር ቃል በትሕትና እና በጸሎት እንቀርባለን፡ የጸሎት አስፈላጊነት፣ መዝ. 119.18.
1. ለእግዚአብሔር መንፈስ ምሪት ጸልይ፣ 1 ዮሐንስ 2፡20-21።
1
2. ለእግዚአብሔር መመሪያ ክፍት እንድትሆን ጸልይ፣ መዝ. 32፡8-9።
3. ለመታመን እና ለመታዘዝ የእግዚአብሔርን ኃይል እንዲሰጥህ ጸልይ
ሀ. ዕብ. 11.6
ለ. ያዕቆብ 1፡22-25
4. ቃሉን ለሌሎች ለማካፈል ለእግዚአብሔር ምሪት ጸልይ፣ ዕዝራ 7፡10.
ለ. ለቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት መልካም አመለካከት ይኑርህ
1. ትጉና ቆራጥ ሰራተኛ ሁን፣ ምሳ. 2.1-9; ዝ. ምሳ. 2.2-5; 2 ጢሞ. 2.15.
2. ትሑት እና ጭምት ሁን፣ ኢሳ. 57.15.
2 4 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
3. የሚማር እና የሚቀበል ሁን፣ መዝ. 25.4-5.
ሐ. “ጥጋታችሁንም እረሱ”፡ የእግዚአብሔርን ቃል በማያቋርጥ እና በጥብቅ በማንበብ እና በማሰላሰል መተዋወቅ፣ ሆሴ. 10.12.
1. መጽሐፍ ቅዱስን አንብብ፣ ነህ. 8.8.
2. መጽሐፍ ቅዱስን በቃልህ ሸምድድ፣ መዝ. 119.11.
1
3. በመጽሐፍ ቅዱስን አሰላስል፣ መዝ. 1.1-3.
4. መጽሐፍ ቅዱስ ሲሰበክ ስማ፣ ሐዋ 17፡11.
III. በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጓሜ የአዕምሮ ዝግጅት አስፈላጊነት፡ በአዕምሮ የበሰለ ሁን 1 ቆሮ. 14፡20 - “ወንድሞች ሆይ፥ በአእምሮ ሕፃናት አትሁኑ፤ ለክፋት ነገር ሕፃናት ሁኑ እንጂ በአእምሮ የበሰሉ ሁኑ።”
ሀ. ወደ እግዚአብሔር ቃል እንደ አጥኚ ቅረብ (ሃብቱን ለማግኘት እንደወሰነ ፈላጊ)፣ ማቴ. 13.52.
1. የመጽሐፍ ቅዱስ ዓለም ከእኛ አለም እንደሚለይ ግን ደግሞም በጣም እንደሚመሳሰል ተገንዘብ።
2. የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሁሉ የመጀመሪያው እንቅስቃሴ ‘ከእነርሱ ዓለም’ ጋር መተዋወቅ ነው።
/ 2 5
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
3. ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አንዳንድ “የጊዜ ሂደትን” ያካትታል።
4. እመለከት ዘንድ ዓይኖቼን ክፈት፡ መመልከት፣ መሳተፍ እና ማግኘት።
ለ. ወደ እግዚአብሔር ቃል እንደ መርማሪ ቅረብ (ዋናውን ትርጉም እና ግንኙነቶቹን ለመረዳት ፍንጭ መፈለግ)።
1. የእውነት ኃይሉ በjots እና በtittles ውስጥ ነው; ፍንጮችን ለመፈለግ ራስን የማሰልጠን አስፈላጊነት፣ ማቴ. 5፡17-18።
1
2. አንድም ዝርዝር ነገር እንዳያመልጥህ በጥንቃቄ ፈልግ፡ Agassiz እና ምን ታያለህ?፣ ሉቃ 16፡16-17።
3. ሁሉንም ሊሆኑ የሚችሉ መመሪያዎችን ተከተል፣ ለእያንዳንዱ የቅዱሳት መጻሕፍት ምስክር ጠይቅ።
4. እያንዳንዱን ታሪክ እና alibiን ይመልከቱ።
5. የእግዚአብሔር ቃል አያልፍም፥ ሉቃ 21፡33.
ሐ. እንደ ሳይንቲስት ወደ እግዚአብሔር ቃል መቅረብ (ሁሉንም ሃሳቦች ለመፈተሽ እና ሁሉንም ነገር በእውነታው መሠረት ለማረጋገጥ እንደቆረጠ)፣ ሐዋ 17፡11.
1. ሁሉንም ሃሳቦች ለእግዚአብሔር ቃል ተገዢ በማድረግ እያንዳንዱን ጽንሰ ሃሳብ እና መላምት በቃሉ መሰረት ፈትን።
ሀ. 1ኛ ዮሐንስ 4፡1
2 6 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
ለ. ኢሳ. 34.16
ሐ. 1 ተሰ. 5.21
መ. ኢሳ. 8.20
ሠ. ሮሜ. 12.2
1
ረ. ኤፌ. 5.10
ሰ. ፊል. 1.10
2. በእግዚአብሔር ቃል ያልተደገፈ ማብራሪያን አትቀበል።
ሀ. 1ኛ ዮሐንስ 4፡5-6
ለ. 1 ጴጥ. 1.10-12
3. ሁሉንም የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጉም ከመሲሑ ሰው ጋር ለማገናኘት ጥረት አድርግ።
ሀ. 2 ጢሞ. 3፡15-16
ለ. ዮሐንስ 5፡39
/ 2 7
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
4. በአስተሳሰብህ ሙሉ በሙሉ የበሰለ ሁን።
ሀ. እውነታዎችህን ቀጥተኛ ይሁኑ፥ ፈጣን እና ጥቅልል ያሉ ድምዳሜዎችን አታድርግ፣ ዮሐንስ 7፡24.
ለ. ትክክለኛ መከራከሪያዎችን አቅርብ፡ አመክንዮ እና የአስተሳሰብ ህግጋት። (1) የማንነት ህግ (“ሀ” “ሀ” ነው)
(2) የኢ- ተቃርኖ ህግ (“ሀ” “ሀ” አይደለም)
1
(3) የተገለለው መካከለኛ ህግ (“መ” ወይ “ሀ” ወይም “ለ” ነው)
ሐ. በንግግር ማሰብን ተማር፡ ሀ እና ለ ሁለቱም እውነት ናቸው (ሀለ)። (1) የእግዚአብሔር እውነት ሀ፡ ኢየሱስ ፍፁም አምላክ ነው።
(2) የእግዚአብሔር እውነት ለ፡ ኢየሱስ ፍፁም ሰው ነው።
(3) የእግዚአብሔር እውነት ሀ እና ለ ሁለቱም ናቸው (እኩል፣ የተለያዩ፣ የተዋሃዱ)
መ. “በራስህ ማስተዋል አትደገፍ፣” ምሳ. 3.5-6.
1. ሁሉንም እውነታዎች እስክታገኝ ድረስ ድምዳሜ ላይ አለመድረስን ተማር።
2. ቶሎ ድምዳሜ ላይ እንዳትደርስ ራስህን አስለምድ።
3. ግኝቶቼ ናቸው ብለህ የምታስበውን ሁሉ ደጋግመህ አረጋግጥ።
4. ስለ ጥናትህ ፍሬ ሌሎች ፍርድ ይስጡ።
2 8 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
IV. በመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ የፈቃዱ ዝግጅት አስፈላጊነት፡ የእግዚአብሔርን ቃል ለመለማመድ ራስህን ዝግጁ አድርግ።
ሀ. የቃሉ አድራጊ ሁን፣ ያዕ 1፡22-25፣ ዝከ. ዕዝራ 7፡10
1. የእግዚአብሔርን ቃል በምታጠናበት ጊዜ የጌታን ድምፅ ስማ፣ ዕብ. 3.7-13.
2. የእግዚአብሔርን ማነሳሳት ወዲያውኑ አድርግ።
1
3. ለሌሎች የማንበብ ልማድ አይንርህ፣ እና እግዚአብሔር ለራስህ ሲናገር ለመስማት አንብብ
4. የእግዚአብሔር ቃል በጥናት ልማድህ ላይ ብቻ ሳይሆን በሕይወትህም ላይ ተጽዕኖ እንዲያሳድር ጠብቅ።
ለ. ጥበብ የሚገኘው የእግዚአብሔርን ቃል በመታዘዝ እንጂ በመተርጎም ብቻ አይደለም፣ መዝ. 111.10.
1. ጠንካራ የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ቃሉን ለማጥናት አይኖሩም ይልቁንም ለመኖር ይማራሉ ።
ሀ. ዘዳ. 4.6
ለ. ኢያሱ 1፡7-8
2. ማስተዋል የሚከሰተው የእግዚአብሔርን ቃል በማሰላሰላችን እንጂ ማስታወሻዎች እና ማብራሪያዎችን በመስጠታችን ብቻ አይደለም፣ መዝ. 119.98-101.
/ 2 9
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
3. ያለማቋረጥ ለእግዚአብሔር ቃል በመታዘዝ ከሕፃንነት ወደ ልጅነት ብሎም ወደ ጉልምስና እናድጋለን።
ሀ. 1 ጴጥ. 2.2
ለ. ዕብ. 5.12-6.1
ማጠቃለያ
1
» ቅዱሳት መጻሕፍትን በትክክል ለመተርጎም ልባችንን፣ አእምሯችንን እና ፈቃዳችንን ለሕያው እግዚአብሔርን ዘላለማዊ ቃል ማዘጋጀት አለብን። » እንደ መለኮታዊ እና ሰዋዊ መጽሐፍ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ለመረዳት በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ላይ መደገፍ እና ቃሉን ከመተግበራችን በፊት ህይወታችንን እንዲለውጥ ለመፍቀድ ዝግጁ መሆን አለብን።
እባክህ በነዚህና በሌሎችም በዚህ ቪዲዮ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች በቂ ጊዜ ወስደህ ምላሽ ለመስጠት ሞክር፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ስነ አፈታትን ርእሰ ጉዳይ የከበሩ የቅዱሳት መጻሕፍት ግንዛቤዎችን ብቻ የሚያስገኙ ሕጎችና ዘዴዎች ጥርቅም ብቻ አድርገን ልንመለከተው አይገባም። ይልቁንም፣ አጠቃላይ ርዕሰ ጉዳዩ መንፈሳዊ ጉዳይ ነው፤ ትክክለኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜም ሁል ጊዜ መንፈሳዊ ዝግጅትን ይጠይቃል፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለመረዳት ብቻ ሳይሆን በሁሉም የሕይወታችን ዘርፎች ለማሟላት የሚፈልግ መሠረት ነው። ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡትን የመጀመርያውን ሴግመንት ቁልፍ ጽንሰ ሐሳቦች ማጠቃለያ ጥያቄዎች ከእነዚህ እውነቶች አንጻር ተመልከታቸው፤ መልሶችህን በቅዱሳት መጻሕፍት አስደግፍ። 1. የስነ አፈታት ሳይንስ ምንድነው፣ ስለምንስ ጉዳይ ያጠናል? የመጽሐፍ ቅዱስ ስነ አፈታት ጥናት የሚያመጣው ልዩ ተግዳሮት እና ግብ ምንድን ነው? 2. መጽሐፍ ቅዱስ እንደ መለኮታዊም ሆነ እንደ ሰብዓዊ መጽሐፍ ተደርጎ መወሰድ አለበት ሲባል ምን ማለት ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ሰዋዊ መጽሐፍ ነው ብሎ መናገር መጽሐፍ ቅዱስ ከእግዚአብሔር የመነጨ ነው የሚለውን ሐሳብ ያቃልለዋል? አብራራ። 3. የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ዓላማ ምንድን ነው? በሌላ አነጋገር መጽሐፍ ቅዱስን ስናጠና ምን ለማድረግ መጣር አለብን? ‘የእውነትን ቃል በቅንነት መያዝ’ ሲባል ምን ማለት ነው? (2 ጢሞ. 2.15)?
መሸጋገሪያ 1
የተማሪ ጥያቄዎች እና ምላሾች
ገጽ 295 5
3 0 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
4. ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን በትክክል ለመተርጎም ሲጥሩ ምንጊዜም እውነት አድርገው የያዙት “ወሳኝ የሆኑ ቅድመ አመለካከቶች” ምንድን ናቸው? ቅዱሳት መጻሕፍትን ለመረዳት የተለያዩ ዘዴዎችን ከመጠቀምህ በፊት እነዚህን ቅድመ ግምቶች ማወቅ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? 5. መጽሐፍ ቅዱስን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ምልዓቱን እንደሚያገኝ ሂደታዊ መገለጥ አድርገን መመልከታችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? በተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል እና የእግዚአብሔር የራሱ ቃል በሆነው በጌታችን በኢየሱስ መካከል ያለው ግንኙነት ምን ይመስልሃል? እርስ በርሳቸው እንዴት ይዛመዳሉ? 6. በቅዱሳት መጻሕፍት እስትንፋሰ እግዚአብሔርነት እና ቅዱሳት መጻሕፍትን በመተርጎም ረገድ መንፈስ ቅዱስ ያለውን ሚና ግለጽ። 7. የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ የሶስት ደረጃ ሞዴል ምንድን ነው? ይህ ዘዴ ጽሑፉ በተጻፈበት ዓለም እና በዘመናዊው ዓለም መካከል ያለውን ታሪካዊ እና ቋንቋዊ ልዩነቶች ከግምት ለማስገባት የሚሞክረው እንዴት ነው? 8. የእግዚአብሔርን ቃል መረዳት የሚቻለው እንዴት ነው? የአምላክን ቃል ስናነብ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜዎችን ለመረዳት የሚያስችል ጠንካራ ዘዴ መከተል አስፈላጊ መሆኑን ችላ ማለት ይኖርብናል? ያለ ልብ፣ አእምሮ እና ፈቃድ ዝግጅት የእግዚአብሔርን ቃል እግዚአብሔር በወሰነው መሠረት በቀላሉ መተርጎም የማይቻለው ለምንድነው? ይህ ማለት የእግዚአብሔርን ቃል ስናነብ ጠንካራ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ስነ አፈታት ዘዴን አስፈላጊነት ችላ ማለት አለብን ማለት ነው? 9. መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት ሂደት ውስጥ አእምሯችንን በሙሉ ልባችን ለመጠቀም ስንጥር ልንወስዳቸው የሚገቡ አንዳንድ እርምጃዎች ምንድን ናቸው? የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጓሜ ሙሉ በሙሉ ለመረዳት መታዘዝ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው፣ ማጥናትና ማሰላሰል ብቻውን በቂ ያልሆነው ለምንድን ነው?
1
/ 3 1
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
የመጽሐፍ ቅዱስ እስትንፋሰ እግዚአብሔር፡ የመጽሐፍ ቅዱስ አመጣጥ እና ሥልጣን ክፍል 2፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እስትንፋሰ እግዚአብሔር እና ዘመናዊ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንተና
ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ
መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ እንደሚናገረው መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር መንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ ሲሆን የእግዚአብሔርና የሰዎች ባሕርይም የመጽሐፉ ምንጭ እንደሆነና ሕያው የሆነው አምላክ ቃል መሆኑን ያረጋግጣል። ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር ቃል በእግዚአብሔር መንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ ስለሆነ፣ በመጀመሪያዎቹ ቅጂዎች ውስጥ ምንም ዓይነት ስህተት እንደሌለበት፣ በዚህም ምክንያት በእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ምን ማመንና ምን ማድረግ እንዳለብን የሚወስን ፍጹም ሥልጣን እንዳለው ያምናሉ። በዘመናችን ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኞች የመጽሐፍ ቅዱስን አመጣጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጠቀሱት የመጀመሪያዎቹ ክንውኖች በመነሳት በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ከተመዘገቡት ክንውኖች ጋር ለማዛመድ ይጥራሉ። እነዚህ ዋና ዋና ክፍሎች ቅርጽ፣ ምንጭ፣ የስነ ቋንቋ፣ የጽሑፍ፣ ሥነ-ጽሑፋዊ ፣ ቀኖናዊ እና ታሪካዊ ትንተናዎችን እንዲሁም የትርጉም ጥናቶችን ያካትታሉ። በዛሬው ጊዜ ያሉ ብዙ ምሁራን የሚይዙት አቋም ምንም ይሁን ምን ቅዱሳት መጻሕፍት በእርግጥ የሕያውና ለዘላለማዊው አምላክ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ እርግጠኞች መሆን እንችላለን። የዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እስትንፋሰ እግዚአብሔር እና ዘመናዊ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንተና የተሰኘ ሴግመንት ዓላማ የሚከተሉትን እንድትገነዘብ ማስቻል ነው፦ • ቅዱሳት መጻሕፍት በግልጽ እና በድፍረት መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እና አሠራር በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት “እስትንፋሰ እግዚአብሔር” እንደሆነ ይናገራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ በሰዎች ደራሲነት እና በመለኮታዊ አነሳሽነት የተጻፈ መጽሐፍ ነው፣ ነገር ግን የትኛውም ቅዱስ መጽሐፍ በግለሰብ ፈቃድ የተተረጎመ አይደለም፣ ነገር ግን ደራሲዎቹ በመንፈስ ቅዱስ “ተነድተዋል”። • ቅዱሳት ጽሑፎችን የጻፉት ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው የተጻፉ መሆናቸውን የሚያረጋግጡት አምስት ዋና ዋና የመንፈስ አነሳሽነት ንድፈ ሐሳቦች ናቸው። እነዚህም ሜካኒካል ወይም ዲክቴሽን ቲዎሪ፣ ኢንቱይሽን ወይም ናቹራል ቲዎሪ፣ የኢሉሚኔሽን ቲዎሪ፣ ዘ ዲግሪስ ኦፍ ኢንስፓየሬሽን ቲዎሪ እና ቨርባል/ፕሌነሪ ቲዎሪ ይገኙበታል። ቨርባል/ ፕሌነሪ ቲዎሪ፣ ጸሐፊው የመረጣቸውን ቃላት ጨምሮ የቅዱሳት መጻሕፍቱ ሙሉ ጽሑፍ የእግዚአብሔር መሪነትና ምርጫ ውጤት ነው የሚል ነው። • በዘመናችን ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኞች የመጽሐፍ ቅዱስን አመጣጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጠቀሱት የመጀመሪያዎቹ ክስተቶች በመነሳት በመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ውስጥ ከተመዘገቡት ክስተቶች ጋር ለማገናኘት ይጥራሉ። ከቁጥጥር ክስተት ጀምሮ የእግዚአብሔርን መልእክት ከድርጊቱ ክዋኔ አንስቶ ዛሬ እስካለን የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጉም ድረስ ለመከታተል ይሞክራል ።
የሴግመንት 2 ማጠቃለያ [የጎን ማስታወሻ]
1
3 2 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
• የዘመናዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ትችት ዋና ዋና ክፍሎች የቅርጽ ትችት (የቃል ወግ መከታተል)፣ የመነሻ ትችት (የመጀመሪያውን የጽሑፍ ምንጮች መፈለግ) ፣ የቋንቋ ትችት (ቋንቋ ፣ ቃላት እና ሰዋስው) ፣ ጽሑፋዊ ትችት (የጽሑፎች ቅጂዎች) ፣ የሥነ-ጽሑፍ ትችት (የሥነ-ጽሑፍ ህጎች) ፣ ቀኖናዊ ትችት (መጽሐፎች እንዴት እንደተመረጡ)፣ የአርትዖት ትችት (የደራሲዎቹ ዓላማዎች) ፣ ታሪካዊ ትችት (ታሪክ እና ባህል) ፣ እንዲሁም የትርጉም ጥናቶችን ያካትታል። • በዛሬው ጊዜ ያሉ ብዙ ምሁራን የሚይዙት አቋም ምንም ይሁን ምን ቅዱሳት መጻሕፍት በእርግጥ የሕያውና ለዘላለማዊው አምላክ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ እርግጠኞች መሆን እንችላለን።
1
I. ምንም እንኳን መጽሐፍ ቅዱስ በሰዎች ደራሲነት የተጻፈ ቢሆንም ግን በእግዚአብሔር ነው።
የቪዲዮ ሴግመንት 2 መመሪያ
ሀ. ስሞች እና ርዕሶች
1. “መጽሐፍ ቅዱስ” የሚለው ቃል ቢብሎስ (ማቴ. 1.1) እና መጽሐፍ ቅዱስ (ሉቃስ 4.17) “መጽሐፍ” ከሚለው የግሪክኛ ቃል የመጣ ነው።
2. በቢብሉስ ወይም በፓፒረስ ሸምበቆ ላይ የተጻፉ ጥንታዊ መጻሕፍት፣ ከዚህም ቢብሎስ መጡ እና በመጨረሻም ከቅዱሳት መጻሕፍት ጋር ተቆራኝተዋል (ማርቆስ 12.26፤ ሉቃስ 3.4፤ 20.42፤ የሐዋርያት ሥራ 1.20፤ 7.42)
3. “ቅዱስ መጽሐፍ” ወይም “ቅዱሳት መጻሕፍት” (ማለትም፣ ቅዱሳን ጽሑፎች) (ማርቆስ 12.10፤ 15.28፤ ዮሐንስ 2.22፤ 10.35፤ ሉቃስ 24.27፤ የሐዋርያት ሥራ 17፡ 11፤ 2 ጢሞ. 3.15፤ 2 ጴጥ. 3፡16)
4. የእግዚአብሔር ቃል (ማር. 7፡13፤ ሮሜ. 10፡17፤ 2ኛ ቆሮ. 2፡17፤ ዕብ. 12፤ 1 ተሰ. 2፡13)
/ 3 3
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
ለ. መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በሰዎች ደራሲነት ነው።
1. ኢሳያስ፣ ኢሳ. 1.1-2
2. ጳውሎስ፣ ገላ. 1.1-5
3. ሙሴ፣ መዝ. 90.1-2
1
4. ዳዊት፣ መዝ. 19.1
ሐ. ቅዱሳት መጻሕፍት በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የተጻፉ ናቸው።
1. በእግዚአብሔር በራሱ “አነሳሽነት”፣ 2ጢሞ. 3፡16-17።
2. ደራሲዎች ምንም ዓይነት የግል ትርጉም የለውም፣ 2ጴጥ. 1.19-20.
3. ደራሲዎቹ በመንፈስ ቅዱስን ተነድተው ነው የጻፉት፣ 2 ጴጥ. 1.21.
መ. የቅዱሳት መጻሕፍት መለኮታዊ ተነሳሽነት አንድምታ
1. ቅዱሳት መጻሕፍት በእግዚአብሔር መንፈስ አነሳሽነት የተጻፉ በመሆናቸው፣ በትምህርታቸው ወይም በእውነት ማረጋገጫዎቻቸው ምንም ዓይነት ስህተት እንደሌላቸው እናረጋግጣለን።
3 4 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
2. ቅዱሳት መጻሕፍት በእግዚአብሔር መንፈስ አነሳሽነት የተጻፉ በመሆናቸው፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ ማመንና ማድረግ ስላሉብን ነገሮች ቅዱሳት መጻሕፍት ብቻ የመጨረሻው እና ፍፁም ባለሥልጣን መሆናቸውን እናረጋግጣለን።
II. የእስትንፋሰ እግዚአብሔር ጽንሰ-ሀሳቦች፡ መንፈስ ቅዱስ እንዴት ደራሲ ሰዎችን በትክክል መራ? እነዚህ ንድፈ ሐሳቦች ጌታ፣ መንፈስ እንዴት ደራሲዎቹን እንዳነሳሳቸው፣ ያመጡት ውጤት “በእግዚአብሔር አነሳሽነት” የመጣ ነው እንዴት ሊባል ይችላል የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ይፈልጋሉ።
በዚህ ክፍል ውስጥ ያለው የክርክር አወቃቀር ከ H. Wayne House, “Theories of Inspiration.” Charts of Christian Theology. Grand Rapids: Zondervan, 1992 የተወሰደ ነው።
1
ሀ. መካኒካል ወይም ዲክቴሽን ቲዎሪ፡ ተሳትፎ አልባ የሰው ደራሲነት
1. ደራሲው ሰው በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ተሳትፎ አልባ መሳሪያ ነበር።
2. ፀሐፊው እያንዳንዱን ቃል እግዚአብሔር እንደተናገረው ጻፈ (በቃል ዘገባ፣ እንደ ጸሐፊ)።
3. ይህ አጻጻፍ ቅዱሳት መጻሕፍትን ከስህተት ይጠብቃል።
4. ለሜካኒካል ወይም ለዲክቴሽን ቲዎሪ ምላሽ
ሀ. ይህ እውነት እንዳይሆ የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት በጣም ብዙ የአጻጻፍ ስልት፣ የቋንቋ እና የአገላለጽ ስልት ልዩነቶችን ያሳያሉ።
ለ. ታዲያ ለምን እግዚአብሔር መጽሐፉን ሙሉውን አልሰጠንም?
/ 3 5
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
ለ. ኢንቲዩሽን ወይም ናቹራል ቲዎሪ፡ ባለ ተሰጥኦ የሰው ደራሲነት
1. መጽሐፍ ቅዱስን እንዲጽፉ መንፈስ ቅዱስ ጥልቅ መንፈሳዊ ጥበብ ያላቸውን ሰዎች መረጠ።
2. ደራሲዎቹ መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት በራሳቸው ልምድና ግንዛቤ ነው።
3. ለኢንቲዩሽን ወይም ናቹራል ቲዎሪ ምላሽ፡- በቅዱሳት መጻሕፍት መሰረት የቅዱሳት መጻሕፍት ደራሲ የእግዚአብሔር መንፈስ እንጂ ሰው አይደለም፣ ነገር ግን እንደመረጠ ወይም ስጦታን እንደሰጠ ይናገራሉ፣ 2 ጴጥ. 1.20-21.
1
ሐ. ኢሉሚኔሽን ቲዎሪ፡ ከፍ ያለ የሰው ደራሲነት
1. መንፈስ ቅዱስ የጸሃፊ ሰዎችን መደበኛ አቅም ከፍ አድርጓል።
2. ይህ የላቀ ችሎታ ደራሲዎቹ ስለ መንፈሳዊ እውነት ልዩ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና እንዲገልጹ አስችሏቸዋል።
3. ለኢሉሚኔሽን ቲዎሪ ምላሽ፡- ቅዱሳት መጻሕፍት በተጨማሪ ስጦታዎች አማካኝነት የጻፉትን ደራሲ ሰዎች ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩትንም ይገልጻሉ (ሮሜ 3.2)።
መ. ዲግሪስ ኦፍ ኢንስፓየሬሽን ቲዎሪ፡- የበለጠ እና-ያነሰ ተነሳሽነት ያለው የሰው ደራሲነት
1. አንዳንድ የቅዱሳት መጻሕፍት ክፍሎች ከሌሎቹ በበለጠ ተነሳሽነት የተጻፉ ናቸው።
3 6 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
2. ከቁልፍ አስተምህሮ ወይም ከሥነ ምግባር እውነቶች ጋር የተያያዙ ክፍሎች ከታሪክ፣ ኢኮኖሚክስ፣ ባህል፣ ወዘተ ጋር ከተያያዙት የበለጠ ተነሳሽነት አላቸው።
3. አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በመንፈስ አነሳሽነት ያልተጻፉ ሊሆኑ ይችላሉ።
4. ለዲግሪ ኦፍ ኢንስፓየሬሽን ቲዎሪ ምላሽ
ሀ. ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ በእስትንፋሰ እግዚአብሔር መሪነት የተጻፉ ናቸው፣ 2ጢሞ. 3፡16-17።
1
ለ. የኢንስፓየሬሽን ቲዎሪ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ቃል በተመለከተ ካስተማረው ሁሉ ፊት ይሄዳል፣ ማቴ. 5.17-18; ዮሐንስ 3፡34-35; ዮሐንስ 10፡35
ሐ. የትኞቹ ክፍሎች ብዙ ወይም ጥቂት ተነሳሽነት እንዳለባቸው የሚወስነው ማን ነው?
ሠ. ቨርባል-ፕሌነሪ ቲዎሪ፡ ተሳትፎ አልባ የሰው ደራሲነት
1. ቅዱሳት መጻሕፍት በጽሑፎቻቸው መለኮታዊም ሆነ ሰዋዊ አካላትን ያይዛሉ።
2. ደራሲው የመረጣቸውን የቃላት ምርጫን ጨምሮ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶች በሙሉ የእግዚአብሔር ውጤቶች ናቸው።
ሀ. እነዚህም በሰዎች እና ሁኔታዎች ውስጥ ተገልጸዋል.
ለ. በሰው ቋንቋ እና ፈሊጥ ነው የሚገለጹት።
/ 3 7
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
3. ደራሲዎቹ አስቀድሞ በእግዚአብሔር የታወቁ እና የተመረጡ ናቸው፤ እርሱም በጽሁፋቸው ውስጥ መርቷቸዋል (ለምሳሌ ኤርምያስ፣ ኤር. 1.5)።
4. ለቨርባል-ፕሌነሪ ቲዎሪ ምላሽ፡
ሀ. ስለ ሰው እና መለኮታዊ ደራሲነት ጉዳይ መልስ ይሰጣል
ለ. ቃላቶቹን ጨምሮ በሙሉው ጽሑፍ ላይ ያተኩራል።
1
ሐ. ውሱን እና ከባህል ጋር የተቆራኙ ሰዋዊ አካላት እንዴት የማይለወጥ እና ዘላለማዊ የእግዚአብሔር ቃል ተብለው ሊገለጹ ቻሉ?
ረ. የመጨረሻ ጉዳዮች
1. መንፈስ ቅዱስ ደራሲዎቹን ነዳቸው፣ 2 ጴጥ. 1.20-21.
2. ሁሉም ቅዱሳት መጻሕፍት (የእግዚአብሔር መንፈስ መነዳትውጤት) ናቸው፣ ስለዚህም በእግዚአብሔር “የተተነፈሱ” ናቸው፣ 2ጢሞ. 3፡16-17።
III. የመጽሐፍ ቅዱስ ትንታኔ እና የመጽሐፍ ቅዱስ አመጣጥ፡ ከክስተት ወደ ታሪክ ከዚያም ወደ ጽሑፍ
ሀ. ጉዳዩ፡ የጽሑፉ ዝግመተ ለውጥ
1. መጽሐፍ ቅዱስ እኛ ጋር የደረሰው እንዴት ነው? አሁን ያሉንን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች እንድናገኝ ያደረጉን እርምጃዎች ምን ምን ነበሩ?
3 8 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
2. የመጽሐፍ ቅዱስን አመጣጥ ከተፈጸሙት ክንውኖች አንጻር በራሳችን የአፍ መፍቻ ቋንቋ መረዳት እንችላለን?
3. ዘመናዊ ታሪካዊ ትንታኔ የቅዱሳት መጻሕፍትን አመጣጥ ከመጀመሪያዎቹ ክንውኖች አንስቶ ወደ ትክክለኛው ታሪኮች በመመልከት ስለእነሱም ለቅዱሳት መጻሕፍት ጽሑፎች እና በመጨረሻም ዛሬ በምናገኛቸው ትርጉሞች ላይ ነው።
ሀ. ኦሪጅናል ክስተቶች፡ ገላጭ ክስተቶች (ለምሳሌ፡ የክርስቶስ ክስተት)
1
ለ. ስለእነሱ ትክክለኛ ታሪኮች እና ዘገባዎች (ታሪኮቹ ከመጻፋቸው በፊት ይሰራጩ የነበሩት የቃል ወጎች)
ሐ. ወደ ቅዱሳት መጻሕፍት ጽሑፎች (የመጻሕፍቱ ትክክለኛ አወቃቀር)
መ. ወደ ትርጉሞቹ (አሁን ያሉን ትርጉሞች)
ለ. መጽሐፍ ቅዱሳዊ የትችት ምሳሌ፡- ሉቃስ
1. የሉቃስ ምስክርነት፣ ሉቃስ 1፡1-4
ሀ. የታሪክ እውነታዎችን ትረካ ማጠናቀር
ለ. ያመኑትን የዓይን ምስክሮች መሰረት በማድረግ
ሐ. ሥርዓት ያለው ታሪክ ለቴዎፍሎስ
/ 3 9
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
መ. የተማርካቸውን ነገሮች በተመለከተ እርግጠኛ ለመሆን
2. የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ሲከፈት፣ የሐዋርያት ሥራ 1.1-2
ሀ. የኢየሱስን ማንነትና ሥራ በተመለከተ የሉቃስ ዘገባ “ጥራዝ II” ሆኖ አገልግሏል።
ለ. ታሪካዊ ትክክለኛነት
1
3. የሉቃስ ትችት መሠረታዊ መነሻ፡ በኢየሱስ ሕይወትና ሥራ ዙሪያ ስላሉት ታሪካዊ እውነታዎች ትክክለኛ ዘገባ ማቅረብ።
4. ዘመናዊ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትችት፡- ጽሑፉን ከመጀመሪያው ክስተት ለመፈለግ፣ ከክስተቱ ከራሱ፣ ከቃል ወጎች፣ ከዚያም ወደ ጽሑፋዊ ቅጂዎች፣ ወደ መደበኛ ትርጉሞች መሸጋገር።
ሐ. የመገለጡ ክስተት፡ እግዚአብሔር በአለም ውስጥ እና በእግዚአብሔር ወንድና ሴት ልጆች ይሰራል
1. ቆራጥ (በመገለጥ ረገድ)
2. ባለሥልጣን (ከሐዋርያዊ ትውፊት አንፃር፣ ለምሳሌ ትንሣኤ፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 15)
3. የማይደገም (በታሪክ ውስጥ ከእግዚአብሔር ድርጊት ጋር የተሳሰረ)፣ ለምሳሌ፣ 2ቆሮ. 5.19
4 0 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
4. በመለኮት የተገለጠው (ትርጉሙ የሚተረጎመው ከራሳችን አስተሳሰብ ወይም ትንታኔ ሳይሆን ከራሱ በእግዚአብሔር ብቻ ነው)
ማሳሰቢያ፡- መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥናቶች አንድ ማህበረሰብ የተገለጠን ክስተት የተረዳበት፣ ያስተላለፈበት፣ የመዘገበበት እና በነገረ መለኮት እንደተረዳው በማህበረሰቡ አውድ ውስጥ የጽሑፉን ትርጉም እንደገና ለመያዝ የሚያደርገው ሙከራ ነው።
መ. ቅፅ ትችት፡ ከክስተቶች እና ከጽሁፎቹ ጋር የተያያዙ የቃል ወጎችን (ታሪኮችን፣ ዘገባዎችን፣ ምስክርነቶችን) መፈለግ።
1. የእግዚአብሔርን ሰዎች እና የቀደመችው ቤተክርስቲያንን የቃል ወጎች ያጠናል
1
2. መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎች ወግ ውጤት እንደሆነ አድርጎ ይመለከተዋል።
3. በጣም ዝቅተኛ የማረጋገጫ ደረጃ አለው
4. ጥንካሬ፡- ቅዱሳን ጽሑፎች ምናልባት ከተጻፉት ውጤቶች በፊት የቃል ጅምር እንደነበራቸው አበክሮ ይናገራል
5. ድክመት፡- ማህበረሰቡ ታሪኩን እንዴት እንዳካፈለው ብዙ ይገምታል።
ሠ. ምንጭ ትችት፡- በመጻሕፍቱ አፈጣጠር ውስጥ ጥቅም ላይ የዋሉ የጽሑፍ ምንጮችን ማግኘት
1. መመሳሰሎችን እና ንፅፅሮችን ለማየት በተለያዩ መጽሃፎች ውስጥ ያሉትን ጽሑፎች ያወዳድራል።
2. መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎች ወግ ውጤት እንደሆነ አድርጎ ይመለከተዋል።
3. በጣም ዝቅተኛ የማረጋገጫ ደረጃ አለው
/ 4 1
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
4. ጥንካሬ፡- ቅዱሳን ጽሑፎች ቁልፍ ምንጮችን የመለየት ችሎታን ያጎላል
5. ድክመት፡ መከራከሪያዎቹን ማረጋገጥ አይቻልም
ረ. የቋንቋ ትችት፡ የጥንት ቋንቋዎችን፣ ቃላትን እና ሰዋሰውን ማጥናት
1. የጥንት ዕብራይስጥ፣ ኮይነ ግሪክ እና አራማይክ አጥንቷል።
1
2. መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎች ባህል ውጤት እንደሆነ አድርጎ ይመለከተዋል።
3. የመካከለኛ ደረጃ ማረጋገጫ አለው።
4. ጥንካሬ፡ የጥንት ቋንቋዎች ጥልቅ ትርጉም
5. ድክመት፡ ከቋንቋው በጣም የራቀ ነው።
ሰ. ጽሑፋዊ ትችት፡ ምርጡን ንባብ ለማግኘት ልዩ ልዩ የእጅ ጽሑፎችን ማወዳደር
1. በተለያዩ የእጅ ጽሑፎች ላይ ያተኩራል።
2. መጽሐፍ ቅዱስን የጽሑፍ ምርምር ውጤት አድርጎ ይመለከተዋል።
3. በጣም ከፍተኛ ደረጃ የማረጋገጫ አለው
4. ጥንካሬ፡- በርካታ አስተማማኝ የእጅ ጽሑፎች አሉት
4 2 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
5. ድክመት፡ እጅግ በጣም ሰፊ ቁጥር
ሸ. ስነ-ጽሑፋዊ ትችት፡- ደራሲውን፣ ዘይቤውን፣ ተቀባዩን እና ዘውጉን መወሰን
1. የተለያዩ የስነ-ጽሑፍ ዓይነቶችን ያጠናል፣ ስለመጻሕፍቱ የጀርባ ጥናት
2. መጽሐፍ ቅዱስን የሥነ ጽሑፍ የጥበብ ውጤት አድርጎ ይመለከተዋል።
1
3. በጣም ከፍተኛ ደረጃ የማረጋገጫ አለው
4. ጥንካሬ፡- የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥነ-ጽሑፍ ዓይነቶች (ዘውጎች) ምን ማለት እንደሆኑ እና እነሱን በትክክል ለመተርጎም እንዴት መያዝ እንዳለባቸው ያውቃል።
5. ድክመት፡- ለራሳቸው እንዲናገሩ ባለመፍቀድ ወደ ጽሑፉ ብዙ የማንበብ ዝንባሌን ይፈጥራል
ቀ. ቀኖናዊ ትችት፡ የቤተክርስቲያንን ተቀባይነት፣ የጽሑፉን እይታ እና አጠቃቀም ይተነትናል።
1. በጥንቷ እስራኤል እና በጥንቷ ቤተክርስቲያን (ምክክሮች፣ ስብሰባዎች) የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ላይ ያተኩራል።
2. መጽሐፍ ቅዱስን የሃይማኖት ማኅበረሰብ ውጤት አድርጎ ይመለከተዋል።
3. በጣም ከፍተኛ ደረጃ የማረጋገጫ አለው
4. ጥንካሬ፡- ማህበረሰቡ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ያለውን አመለካከት በቁም ነገር ይመለከታል
/ 4 3
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
5. ድክመት፡- የቅዱሳት መጻሕፍትን ትርጉም በሙሉ ወደ አማኝ ማኅበረሰብ ወደ ምንነት የመቀየር ዝንባሌ አለው እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው አይደለም።
በ. ማሻሻያ ትችት፡ በጻፈው ሰው ሥነ-መለኮት ላይ ያተኩራል።
1. የጸሐፊውን ጭብጥ እና አመለካከቶች ትርጉም ለመረዳት የግለሰብ መጻሕፍትን በጥልቀት ማጥናት
1
2. መጽሐፍ ቅዱስን የመፍጠር ባሕርይ ውጤት እንደሆነ አድርጎ ይመለከተዋል።
3. መካከለኛ ደረጃ ማረጋገጫ አለው።
4. ጥንካሬ፡ ስለ ደራሲው አጠቃላይ የጽሁፎች ስብስብ እና ፍላጎቶቻቸው ጥልቅ ትንተና
5. ድክመት፡- መጽሐፍ ቅዱስን ከሌሎች መጻሕፍት ጋር አይዛመድም።
ተ. ታሪካዊ ትችት፡ ታሪካዊ መቼቱን፣ ባህሉን እና ዳራውን መመርመር
1. ጥንታዊ ባህሎችን፣ ልማዶቻቸውን እና ታሪካቸውን ይመረምራል።
2. መጽሐፍ ቅዱስን የታሪክ ኃይሎች ውጤት አድርጎ ይመለከተዋል።
3. የመካከለኛ ደረጃ ማረጋገጫ አለው።
4 4 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
4. ጥንካሬ፡ የጽሑፉን ታሪካዊ ጉዳዮች ጠንቅቆ ያውቃል
5. ድክመት፡ ከታሪክ በጣም የራቀ ነው።
ቸ. የትርጉም ጥናቶች፡ በምርጥ የእጅ ጽሑፎች ላይ የተመሠረተ ግልጽ፣ ሊነበብ የሚችል ትርጉም ይሰጣል
1. ስለ ተቀባዩ ባህል ቋንቋ ከጽሑፉ ትርጉም ጋር ለተሻለ ትርጉም ግንዛቤ በማግኘት ላይ ያተኩራል።
1
2. መጽሐፍ ቅዱስን እንደ ተለዋዋጭ የትርጓሜ ውጤት ነው የሚመለከተው
3. የመካከለኛ ደረጃ ማረጋገጫ አለው።
4. ጥንካሬ፡ በራስ አንደበት እና የአስተሳሰብ ዓለም የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂን ይከታተላል
5. ድክመት፡ ስለ ጽሑፉ ትርጉም የራስን አስተያየት ያንፀባርቃል
IV. የዘመናዊው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትችት ማጠቃለያ
ሀ. የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪክ እና ልማዶች በዙሪያው ያለውን ሁኔታ ለመረዳት ይጠቅማል
ለ. የመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋዎችን ጥልቅ እውቀት በመስጠት ጠቃሚ ነው።
/ 4 5
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
ሐ. መጽሐፍ ቅዱሳችን ወደ እኛ የመጣባቸውን መንገዶች በመጠቆም ጠቃሚ ነው።
መ. ጥልቅ ችግሮች
1. እውነትን የሚከተለው ከኢየሱስና ከሐዋርያት ቃል ሳይሆን ከሃይማኖት ሳይንሳዊ ጥናት ነው።
2. መጽሐፍ ቅዱስን ትርጉም ያለው እና ሊሆን ይችላል ብለው በሚያምኑት ገደብ መሰረት ለመተርጎም ይፈልጋል
1
3. መጽሐፍ ቅዱስን እንደ መገለጥ ያለመመልከት ዝንባሌ አለው ይልቁንም በዋናነት እንደ አንድ ሃይማኖታዊ ማኅበረሰብ መዝገብ ይቆጥረዋል።
ቃሉ እውነት ይሁን፣ ሰውም ሁሉ ውሸታም ይሁን!
ኢሳ. 40.8 - “ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፥ የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።”
ማጠቃለያ
» የእግዚአብሔር ቃል በእግዚአብሔር መንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ ነው፣ ምክንያቱም ደራሲዎቹ በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው የጻፏቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ናቸው፣ ስለዚህም የሕያው እግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው ቃላት ናቸው። » በዘመናችን ያሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትችቶች በብዙ መልኩ መጽሐፍ ቅዱስን እንድንገነዘብ የሚረዱን ቢሆኑም፣ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እስትንፋሰ እግዚአብሔርነት ካለው ጥርጣሬ አንጻር ስለሚሏቸው ነገሮች ግን መጠንቀቅ እንዳለብን ይጠቁማል።
4 6 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
የሚከተሉት ጥያቄዎች በሁለተኛው የቪዲዮ ክፍል ውስጥ ያለውን ሐሳብ እንድትገመግም ለመርዳት ታስበው የተዘጋጁ ናቸው። የመጽሐፍ ቅዱስን አመጣጥ፣ ሥልጣንና መንፈስ አነሳሽነት በተመለከተ የሚነሱ ጥያቄዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜዎች ሁሉ ዋነኛ ክፍል ናቸው። የመጽሐፍ ቅዱስን መለኮታዊ አመጣጥና ሰዋዊ ደራሲነት በተመለከተ ያለውን ጥያቄ እስካልፈታነው ድረስ የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጓሜ በተመለከተ ያለንን አተረጓጎም መግለጽ አንችልም። ዘመናዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ትችት መለኮታዊና ሰዋዊ ናቸው በሚሉት መካከል ያለውን ትክክለኛ ግንኙነት ለመግለጽ ይጥራል። ከታች ባሉት ጥያቄዎች ላይ አብራችሁ ስትወያዩ በጽሑፉ ላይ የተጠቀሱትን ዋና ዋና ሐሳቦች ስትገመግሙ የራስህን አመለካከት ግልጽ ለማድረግ ሞክር። የሚከተሉትን ጥያቄዎች በጥንቃቄ አንብብ፤ እና ቅዱሳት መጻሕፍት ከሚያስተምሩት ትምህርት አንጻር ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ሞክር። 1. ቅዱሳት መጻህፍት በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የተጻፉ ናቸው የሚሉ ቢያንስ ሦስት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ዘርዝር። መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው ሲባል ምን ማለት ነው? በ2ኛ ጴጥሮስ ላይ የሚገኘውን የቅዱሳት መጻሕፍት ጥቅሶች የግል ትርጓሜ እንዳላቸው የሚገልጸውን ነገር እንዴት ትረዳዋለህ? (2 ጴጥ. 1.19-21)? 2. ሜካኒካል ወይም ዲክቴሽን ቲዎሪ ምንድን ነው? ምንስ ይዟል? 3. የመጽሐፍ ቅዱስን እስትንፋሰ እግዚአብሔርነት የሚገልጸውን ኢንቲዩሽን ወይም ናቹራል ቲዎሪ አብራራ። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ራሱ ከሚናገረው ነገር አንጻር ይህን ቲዎሪ እንዴት ልንረዳው ይገባል? 4. የመጽሐፍ ቅዱስ እስትንፋሰ እግዚአብሔርነት ኢሉሚኔሽን ቲዎሪ ዋና ዋና ገጽታዎች ምንድን ናቸው? ቅዱሳት መጻሕፍት ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች ስጦታ እና ስለ መጽሐፍ ቅዱስ መለኮታዊነት ለሚነሳው ጥያቄ መልስ የሚሰጡት እንዴት ነው? 5. ዲግሪስ ኦፍ ኢንስፓየር ቲዎሪ ስለ እግዚአብሔር ቃል ተፈጥሮ ከሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር እንዴት ይስማማል? 6. ቨርባል/ፕሌነሪ ቲዎሪ ከተሰኘው የመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጐም ጋር የተያያዙ ዋና ዋና ፅንሰ ሀሳቦችን ዘርዝር። ይህ ቲዎሪ ከሌሎቹ በላቀ ሁኔታ በመጽሐፍ ቅዱስ አመጣጥና ሥልጣን ውስጥ ስላለው መለኮታዊና ሰዋዊ ግንኙነት ግልጽ መልስ የሚሰጠን ለምንድን ነው? 7. የዘመናዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ትችት ዓላማ ምንድን ነው? ይህስ አላማ ተጨባጭ ነው? መልስህን አብራራ። 8. ከመለኮታዊ ክስተት አንስቶ እስከ ቅዱሳን ጽሑፎች ቅጂዎች ድረስ ያለውን ሂደት የሚከታተሉትን የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትችት ንዑስ ክፍሎችን ጠቅለል አድርገህ ግለጽ። “ከፍተኛ” ትችትና “ዝቅተኛ” ትችት የሚለያዩት እንዴት ነው? ከእነዚህ ዘርፎች ጋር የተያያዙት ችግሮችና ጠቀሜታዎች ምንድናቸው?
መሸጋገሪያ 2
የተማሪዎች ጥያቄዎችና መልሶች
1
/ 4 7
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
9. ከሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ትችት ዘዴዎች መካከል የቅዱሳት መጻህፍትን ጥናት በሚያካሂዱ ሰዎች መካከል ቃሉን በትክክል ለመተርጎም ለሚያደርጉት ጥረት የተሻለውንና በጣም ጠቃሚውን ድጋፍ የሚሰጠው የትኛው ነው? 10. በዛሬው ጊዜ ያሉ ብዙ ምሁራን ስለ እግዚአብሔር ቃል ሥልጣንና እስትንፋሰ እግዚአብሔርነት ጥርጣሬ ቢኖራቸውም እንኳ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉማችን አስተማማኝና ትክክለኛ መሆኑን እርግጠኞች መሆን የምንችለው ለምንድን ነው?
የናዝሬቱ ኢየሱስ የኦሪት መጻሕፍትን የተረዳበትና የተጠቀመበት መንገድ እንዲሁም በሐዋርያቱ አማካኝነት መጪውን አዲስ ኪዳን አስቀድሞ የተመለከተው እንዴት እንደሆነ ለማወቅ በፖል ኤንስ የተጻፈውን ተጨማሪ ክፍል “Christ’s View of the Bible”ን አንብብ።
1
ግንኙነት
የቁልፍ ጽንሰ ሐሳቦች ማጠቃለያ
የዘመናዊው መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውቀት ተፈጥሮ በአሁኑ ጊዜ ለመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጓሜዎች የሚገኙት በርካታ ዘዴዎች ግራ የሚያጋቡ ቢሆኑም ተርጓሚው በግንዛቤ ሂደት ተለዋዋጭነት ላይ ሳይሆን ዘዴዎች ላይ እንዲያተኩር ሊያደርግ ይችላል ። የችግሩን ሙሉ ስፋት (የ ‹ኦንቶሎጂያዊ› ልኬቶቹን ጨምሮ) እንደ መነሻ ነጥብ ሲወሰድ ፣ የሚመለከቷቸውን ልዩ ገጽታዎች በተመለከተ ዘዴዎችን ለመመደብ እና ለእያንዳንዱ ጉዳይ በጣም ተስማሚ የሆነውን ዘዴ ለመምረጥ ይቻላል ። የችግሩ ታሪካዊ ገጽታ በዋነኝነት በላኪው እና በመልእክቱ መካከል ካለው ግንኙነት ጋር የተያያዘ ነው። ከዚህ አስፈላጊ የምርምር ዘርፍ በርካታ ልዩ ቴክኒኮች ተሻሽለዋል። የጀርባ ታሪክ ጥናቶች (Zeitgeschichte) ጽሑፉ የተገኘበት ታሪካዊ ዳራ ላይ ያተኩራሉ። የቅርጽ ትችት ከጽሑፍ በስተጀርባ የቃል ወግ ይይዛል እንዲሁም ከቅድመ-ሥነ-ጽሑፍ ቅርፅ ወደ ሥነ-ጽሑፍ ቅርፅ የሚደረግ ሽግግር ላይ ትኩረት ያደርጋል። ምንጭ ትችት በሰፊው ሥነ ጽሑፋዊ አውድ እና በመረጃ ምንጮች ላይ ያላቸውን ጥገኛነት በተናጠል ጽሑፎች መካከል ያለውን ግንኙነት ያጠናል። የጽሑፍ አዘጋጅነት ትችት የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት ግለሰባዊ ደራሲዎች በመጨረሻው ቅርፃቸው ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድረዋል ከሚል ግምት የሚመነጭ ሲሆን የእነዚህን ጽሑፎች ጥንቅር በመጨረሻው አዘጋጅ እይታ ይተነትናል። የጽሑፍ ትችት የጽሑፉን የመጀመሪያ ቅርፅ በተቻለ መጠን በትክክል ወደነበረበት ለመመለስ ያለመ ልዩ እና ቴክኒካዊ ዲሲፕሊን ነው። የደራሲነት ጥያቄዎች፣ የነጠላ መጽሐፍት ታሪክ እና የቀኖና ምሥረታ ሁሉም በላኪው እና በመልእክቱ መካከል ካለው ግንኙነትና ታሪካዊ ገጽታ ጋር የተያያዙ ናቸው።
ገጽ 295 6
~ Bernard C. Lategan. “Hermeneutics.”The Anchor Bible Dictionary. D. N. Freedman, ed. Vol. 3. Doubleday: New York: Doubleday, 1997. pp. 152-153.
Made with FlippingBook flipbook maker