Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide

/ 1 5

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

1 ጴጥ. 1.23-25 - “ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ። ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤ የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል። በወንጌልም የተሰበከላችሁ ቃል ይህ ነው። በዚህ መጠነኛ ዝርዝር ውስጥ ስለ እግዚአብሔር ታማኝነት ተጨማሪ ቅዱሳት መጻሕፍትን ጨምር እና በኢሳይያስ 55 ሃሳብ ላይ ሙሉ ወደሆነ ግንዛቤ ትደርሳለህ። እግዚአብሔር የቃሉን ፍጻሜ እርግጠኝነት በትንቢቱም ሆነ በተስፋው መሠረት ከዘርና ከምድር ጋር ተደባልቆ ብዙ ፍሬ ከሚያፈራው ከሰማይ ዝናብ ተፈጥሯዊ ኃይል ጋር ያነፃፅራል። ዝናብ ከምድር ንጥረ ነገሮች ጋር እንደሚደባለቅ ሁሉ እግዚአብሔር ቃሉም ፍሬያማ፣ እርግጠኛ፣ የተሳካ እና ኃያል እንደሆነ ተናግሯል። ይህን ከእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ቃል ጋር የተያያዘ የፍሬያማነት እና የብልጽግና ተስፋ፣ የውጤት እርግጠኝነት በምን እንቆጥረዋለን? በባሕርይው፣ በማንነቱ፣ በእውነተኛነቱ እንደ ታማኝ አምላክ፣ የማይዋሽ አምላክ (ቲቶ 1.2)፣ ቃሉ የተረጋገጠና የታመነ፣ ለዘላለም በሰማያት የተቀመጠ ነው። ዳዊት በመዝሙር 89 ላይ ስለ እግዚአብሔር ታማኝነት እና ስለ ቃሉ ታማኝነት ዘምሯል፡- “አቤቱ፥ ምሕረትህን ለዘላለም እዘምራለሁ፥ እውነትህንም በአፌ ለልጅ ልጅ እናገራለሁ። እንዲህ ብለሃልና፦ ምሕረት ለዘላለም ይመሠረታል፥ እውነትህም በሰማይ ይጸናል።” (መዝ. 89፡1-2)። በዚህ ጽሑፍ ውስጥ እግዚአብሔር ቃሉ እውነት መሆኑን አረጋግጦልናል። እግዚአብሔር ታማኝ አምላክ ስለሆነ ቃሉ እርሱ የወሰነውን ይፈጽማል፣ እርሱም ያደርገው ዘንድ በሾመው ነገር ላይ ይፈጸማል። ልጠይቅህ፡ እግዚአብሔር የገባልን ቃል ሁሉ በእርግጥም እንደሚፈጸም የመተማመኛ መሰረታችን ምንድን ነው - በምን ምክንያት፣ በምን መሰረት፣ በኢየሱስ ክርስቶስ የተገባልንን ህይወት በእምነት እንደምናጭድ እንዴት እናምናለን? መልሱ እውነተኝነት ለህዝቡ እውነትን የተናገረው የህያው አምላክ እውነተኛ ባህሪ መሆኑ ነው። አምላካችን የእውነት አምላክ ነው፤ ስለዚህም የገባውን ቃል እንደሚፈጽም አውቀን የተስፋ ቃሉን እንጠባበቃለን። ይህ እና ይህ ብቻ መተማመኛ መሠረታችን ነው። የኒቂያን የእምነት መግለጫ (በአባሪው ውስጥ ይገኛል) ካነበብክ እና/ወይም ከዘመርክ በኋላ የሚከተለውን ጸሎት ጸልይ፥ ቅዱሳት መጻሕፍትን ሁሉ ለትምህርታችን እንዲጻፉ ያደረግህ ብሩክ ጌታ፡ አንተ የሰጠኸንን የተባረከውን የዘላለም ሕይወት ተስፋ እንድንሰማ፣ እንድናነብብ፣ እንድንቀበል፣ እንድንማር፣ እና እንድናሰላስላቸው፣ አጥብቀንም እንይዛቸው ዘንድ ከአንተ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በሚኖርና በሚነግሥ አንድ አምላክ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስጠን፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም። አሜን። ~ Episcopal Church. The Book of Common Prayer and Administrations of the Sacraments and Other Rites and Ceremonies of the Church, Together with the Psalter or Psalms of David. New York: The Church Hymnal Corporation, 1979. p. 236

1

የኒቂያ የእምነት መግለጫ እና ጸሎት

Made with FlippingBook flipbook maker