Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide
/ 1 5 9
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማመሳከሪያዎችን መጠቀም
ትምህርት 4
ገጽ 305 1
የትምህርቱ ዓላማዎች
ሃያል በሆነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን ! የዚህን ትምህርት መጽሀፍ ካነበብክ፣ ካጠናህ፣ ውይይት ካካሄድክና ወደ ተግባር ከቀየርከው በኋላ የሚከተሉትን ማድረግ ትችላለህ:- • የአንድን ጽሑፍ ትርጉም ለመረዳት በምናደርገው ሙከራ ውስጥ የጥናት መርጃ መሣሪያዎችን ሚና ታውቃለህ፣ ትረዳለህ። • በመጽሐፍ ቅዱሳዊው አለም እና በእኛ ዘመናዊ አለም መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ የሚረዱን ችሎታዎችን ጨምሮ በመፅሀፍ ቅዱሳዊ አተረጓጎም ውስጥ ማመሳከሪያዎችን የመጠቀም አላማን ትገነዘባለህ፣ ይህም በዘመናችን በብዛት የፈለቁትን አስደናቂ ማመሳከሪያዎችን ለመጠቀም እና ለእግዚአብሔር ቃል የበለጠ ታማኝ እንድንሆን በመርዳት የአንድን ጽሑፍ ትርጉም ከመጀመሪያው አውድ ውስጥ እንደገና እንድንገነባ ያላቸውን ዋጋ ትረዳለህ። • ጥሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም፣ የግሪክ እና የዕብራይስጥ መዝገበ ቃላት፣ መደበኛ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ ኮንኮርዳንስ እና የምንባብ ማመሳከሪያዎችን ጨምሮ ለሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች መሠረታዊ መርጃ መሣሪያዎች ተብለው የሚታሰቡትን ማወቅና ማብራራት ትችላለህ። • የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ አትላስ እና የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፣ ርዕሳዊ መጽሐፍ ቅዱስ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት እና በመጨረሻም በትልቁ ሥነ-መለኮት ላይ የሚያተኩሩ የነገረ መለኮት ትችቶችን ጨምሮ ስለ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች ትርጉም ተጨማሪ ግንዛቤን ሊሰጡ የሚችሉ አጋዥ መሣሪያዎችን ማወቅና ማብራራት ትችላለህ። • መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈባቸውን ሦስት ቋንቋዎች (ዕብራይስጥ፣ አራማይክ እና ግሪክ) ማብራራት እና የቃላት አጠቃቀም ችግሮች፣ የባህል ልዩነቶች፣ የዐውደ-ጽሑፍ ጉዳዮች እና በተርጓሚዎች መካከል ያለውን ልዩነት ጨምሮ ጥሩ ትርጉሞችን ከማዘጋጀት ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶችን ለይተህ ማውጣት ትችላለህ። • የኮንኮርዳንስ፣ ሌክሲከን፣ መዝገበ ቃላት እና ማብራሪያዎች ትርጉም እና ልዩ አጋዥ መሳሪያዎችን ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ አተረጓጎም አንፃር እንዴት መጠቀም እንዳለብን ማብራራት፣ እንዲሁም የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜዎቻችንን ሊያሳድጉ የሚችሉ ጥቆማዎችን መስጠት ትችላለህ።
4
Made with FlippingBook flipbook maker