Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide

1 6 2 /

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

ዋጋ እግዚአብሔርን እያመሰገንን፣እኛም እንደ ቤርያውያን ቅዱሳት መጻሕፍትን የማረጋገጥን ስራ ሌሎች እንዲሰሩልን መፍቀድ የለብንም። በተጨማሪም፣ በተለይም ዓላማው የሚያስተምሯቸው ነገሮች በትክክል ከመጽሐፍ ቅዱስ ቀጥተኛ ትምህርት ጋር የሚጣጣሙ መሆናቸውን ለማየት እስከሆነ ድረስ የየትኛውንም መንፈሳዊ ባለሥልጣን አቋሞችና ትምህርቶችን ማረጋገጥ ፈጽሞ ስህተት አይደለም። በእግዚአብሔር ሐሳብ ውስጥ፣ ይህ የማረጋገጫ ሥራ ክቡር፣ ከሁሉ የላቀ መንፈስ ነው። አሁን ያሉትን ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚሆኑ እጅግ በጣም ጥሩ መሣሪያዎችን ለመረዳት በትጋት እየሠራህ ሳለ፣ ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት የሚቀርቡትን ሃሳቦች ከራሳቸው ቀጥተኛ የቅዱሳት መጻሕፍት ትምህርት ጋር የማጣራት፣ የመፈተሽ እና ደጋግሞ የማጣራት መብትህን አረጋግጥ። ይህ ክቡር እና የተመሰገነ ነው፤ ሁልጊዜም የጌታን ሞገስ እና በረከት ያገኛል። የሐዋርያውን ቃል በየዕለቱ በቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት ማረጋገጥ በጌታ “ክቡር” ተብሎ ተጠርቷል። በጌታ ቃል ነፃ የሚያወጣንን እውነት ለማረጋገጥ በተቻለን መጠን ያንን ክቡር ህይወት እንኑር (ዮሐ. 8፡31-32)። የኒቂያን የእምነት መግለጫ (በአባሪው ውስጥ ይገኛል) ካነበብክ እና/ወይም ከዘመርክ በኋላ የሚከተለውን ጸሎት ጸልይ፥ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንታዘዝ ዘንድ አቤቱ ልንሰማው የሚገባንን በመንፈስህ ንገረን፣ ልናደርገው የሚገባንንም አሳየን ።

የኒቂያ የእምነት መግለጫ እና ጸሎት

~ Presbyterian Church (U.S.A.) and Cumberland Presbyterian Church. The Theology and Worship Ministry Unit. Book of Common Worship. Louisville: Westminister/John Knox Press, 1993. p. 60.

4

ማስታወሻዎችህን አስቀምጠህ ፣ ሀሳቦችህን እና ምልከታዎችን ሰብስበህ ለትምህርት 3 “መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች፡ የመጽሐፍ ቅዱስን ዘውጎች መተርጎም” የተዘጋጀውን አጭር ፈተና ውሰድ

አጭር ፈተና

የቃል ጥናት ጥቅስ ቅኝት

ከሌላ ተማሪ ጋር በመሆን ላለፈው ክፍለ ጊዜ የተመደቡ የቃል ጥናት ጥቅሶች ገምግሙ ፣ ፃፉ እና/ ወይም አንብቡ - 2 ጢሞቴዎስ 3:14-17

የቤት ስራ/መልመጃ ማስረከቢያ

ያለፈውን ሳምንት የንባብ ማጠቃለያህን ማለትም መምህሩ በመደበው ንባብ (የንባብ ማጠናቀቂያ ገጽ) ላይ ለማድረግ የተፈለጉትን ዋና ዋና ነጥቦችን፣ አጭር መግለጫዎን እና ማብራሪያዎን አቅርብ ፡፡

Made with FlippingBook flipbook maker