Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide
1 6 4 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
ዘመናዊ ትርጉሞች ተበክለዋል ተአማኒነት ባላቸው ቅጂዎች ላይ ተመስርተው ብዙ አስተማማኝ ትርጉሞች እንዳሉ በሚታመንበት በዚህ ዘመን፣ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ክርስቲያኖች አሁንም በብዙዎቹ የቅርብ ጊዜ ትርጉሞች ላይ ጥርጣሬ አላቸው። እነዚህ ግለሰቦች እና ቡድኖች በተርጓሚዎች ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩትን ማህበራዊ ጉዳዮችን ሲመለከቱ የእግዚአብሔር ቃል በተጨባጭ በእነዚህ አዳዲስ ትርጉሞች እንደተበላሸ ያምናሉ። የሥርዓተ-ፆታ እኩልነት፣ የባህል እና በርካታ የዘመናዊ የሥነ ምግባር ውዝግቦች አሳሳቢነት ትርጉሞቹን በመበከላቸው ተርጓሚዎቹ የጽሑፉን ትርጉም በጊዜው ካለው ግንዛቤ ጋር በሚስማማ መልኩ እንዲቀይሩ አስገድዷቸዋል የሚል እምነት አላቸው። ምንም እንኳን አብዛኛዎቹ እነዚህ ክሶች የተጋነኑ ቢመስሉም፣ የእነዚህ ወገኖች ሃሳብ ብዙዎች ስለ ትርጉሞቹ የሚጠቁሙትን ሃሳብ በትክክል የሚያንጸባርቁ ይመስላል። በብዙ ዘመናዊ ትርጉሞች ውስጥ ለፖለቲካዊ ትክክለኛነት ጉዳዮች ብዙ ትኩረት እንደተሰጠ ይሰማሃል ወይስ የእግዚአብሔርን ቃል ድህረ ዘመናዊ አንባቢዎች ሊረዱት በሚችሉት መንገድ እያዘጋጁት ነው?
3
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች፡ ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማመሳከሪያዎችን መጠቀም ሴግመንት 1፡ መሰረታዊ መሳሪያዎች
ይዘት
ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ
ቅዱሳት መጻሕፍትን ለሚያከብሩና ለሚወዱ በመቶዎች ለሚቆጠሩ የተሰጡ ምሁራን ሥራ ምስጋና ይግባውና፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ጽሑፍ ትርጉም እንድንረዳ የሚያስችለንን አስደናቂ የሆኑ ምሁራዊ መሣሪያዎችን አግኝተናል። ምሁራዊ ማመሳከሪያዎችን የመጠቀማችን አስፈላጊነት በመጽሐፍ ቅዱሳዊው ዓለም እና በእኛ ዘመናዊ ዓለም መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ እንድንችል ለመርዳት ነው። ይህም ትጉህ የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚው ትርጉሙን ጽሑፉን በዋናው አውድ ውስጥ እንደገና እንዲገነባ በማስቻል ለእግዚአብሔር ቃል የበለጠ ታማኝ እንዲሆን ይረዳዋል። የመጽሃፍ ቅዱስ አተረጓጎም መሰረታዊ መሳሪያዎች ጥሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም፣ የግሪክ እና የዕብራይስጥ መዝገበ ቃላት፣ መደበኛ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ ኮንኮርዳንስ እና የምንባብ ማመሳከሪያዎችን የሚያካትት ሲሆን ይህም በጽሑፉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉሞች ላይ ያተኩራል። እነዚህ መሳሪያዎች በትክክለኛ ቦታቸው እና ጊዜያቸው ጥቅም ላይ ሲውሉ በመጽሐፍ ቅዱሳዊው ዓለም እና እኛ ስለዚያ ዓለም ባለን ግንዛቤ መካከል ያለውን ልዩነት በማጥበብ ረገድ ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ። የዚህ መሰረታዊ መሳሪያዎች የተሰኘ ሴግመንት አላማ የሚከተሉትን እንድትመለከት ለማስቻል ነው፡- • በመቶዎች በሚቆጠሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሑራን እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ምክንያት፣ አሁን ሌሎችን የመረዳት፣ የመተግበር እና የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጉም የማስተማር ችሎታችንን የሚያጎለብቱ እጅግ በጣም ብዙ ጠንካራ ምሁራዊ መሳሪያዎችን ማግኘት ችለናል። • በመጽሐፍ ቅዱሳዊው አለም እና በእኛ ዘመናዊ አለም መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ የሚረዱን ችሎታዎችን ጨምሮ በመፅሀፍ ቅዱሳዊ አተረጓጎም ውስጥ ማመሳከሪያዎችን መጠቀም ሶስት አላማዎች አሉት፤ ይህም በዘመናችን በብዛት የፈለቁትን አስደናቂ
የሴግመንት 1 ማጠቃለያ
4
Made with FlippingBook flipbook maker