Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide

/ 1 8 3

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

በመስቀሉ በኩል ስላደረገው የቤዛነት ስራ በቅዱሳት መጻህፍት የተነገረውን ግልጽ የሆነ አቋም የሚጻረር ምንም አይነት ማመሳከሪያ ተቀባይነት የለውም።

“ከፍተኛ” እና “ዝቅተኛ” የመጽሐፍ ቅዱስ ኅያሴ፡- ልዩነቱ ምንድን ነው?

[ከፍተኛ ኅያሴ] የአንድን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ክፍል የተጻፈበትን ጊዜ፣ ደራሲው፣ ተደራሲያኑ፣ በጽሑፍ ጥቅም ላይ የዋሉ ምንጮች (የቃል፣ የጽሑፍ፣ ወዘተ.) እና አጠቃላይ ሥነ-ጽሑፋዊ ቅርፅን (ከዘመናዊ ካልሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ጽሑፋዊ ባህሪያት እና ስልቶች ጋር ንጽጽርን ጨምሮ) አጠቃላይ ባህሪያትን ለመገምገም የሚሞክር የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጥናት ነው። ገንቢ በሆነና በቅዱሳት መጻሕፍት ታማኝነት ያለ ከተመሰረተ ይህ የጥናት ዘርፍ ጠቃሚ አስተዋጾን ያበረክታል፤ በአንጻሩ ለቅዱሳት መጻሕፍት የሚሰጠው ግምት ዝቅተኛ ከሆነ ተጽእኖው አጥፊ ሊሆን ይችላል። ስለዚህም ይህ ቃል ባለፉት መቶ ዓመታት አንዳንድ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን እንደ አንድ የተቀናጀ መገለጥ ሳይሆን እንደ ሰው ሥራ ብቻ ለመመልከት ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል። [ከዚህ ጋር አወዳድር] ዝቅተኛ ኅያሴ (= ምንባባዊ ኅያሴ)፣ ይህም አብሮ ለመስራት ከሁሉ የተሻለውን የቅዱሳት መጻሕፍት ጽሑፍ ስለማዘጋጀት ያወራል።

~ Paul Karleen. The Handbook to Bible Study. (electronic ed.). New York: Oxford University Press, 1987.

4

I. ማመሳከሪያዎች፣ ርዕሳዊ መጽሐፍ ቅዱሶች፣ የማጣቀሻ መጽሐፍ ቅዱሶች እና ርዕሳዊ ኮንኮርዳንስ

የቪዲዮ ሴግመንት 2 ዝርዝር

ሀ. ማመሳከሪያዎች (አጠቃላይ መርሆዎችን በማግኘት ደረጃ ላይ ጠቃሚ)

1. ፍቺ፡- የማመሳከሪያ መርጃዎች ቅዱሳት መጻሕፍትን ከቅዱሳት መጻሕፍት ጋር በማነጻጸር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተመሳሳዩ ወይም በተያያዙ ጭብጦች መካከል ያለውን ግንኙነት ለመረዳት ይረዱናል።

2. ተመራጭ ማመሳከሪያዎች

Made with FlippingBook flipbook maker