Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide

/ 1 8 7

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

ለ. የመጽሐፍ ቅዱስ አትላስ

1. ፍቺ፡- የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትረካዎችን እና ክስተቶችን አውድ ለመስጠት እና ስለ ቦታዎች እና አካባቢዎች የጀርባ መረጃ ለማግኘት ይጠቅማል።

2. የሚመከሩ የመጽሐፍ ቅዱስ አትላሶች

ሀ. The NIV Atlas of the Bible, Carl G. Rasmussen. (Zondervan, 1989)

ለ. The Macmillan Bible Atlas, Revised 3rd edition Yohanan Aharoni, Michael Avi-Yonah, A. Rainey and Z. Safrai. (Macmillan, 1993)

ሐ. ታሪካዊ እና ማህበራዊ-ባህላዊ የማጣቀሻ ስራዎች

1. ፍቺ፡- የጽሑፉን ትርጉም በራሱ ዐውደ-ጽሑፍ ላይ ብዙ ብርሃን ሊሰጡ የሚችሉ ልዩ ማኅበራዊ፣ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ልማዶችን ወይም ታሪካዊ ክንውኖችን ምንነት ለማወቅ የሚረዱ ማጣቀሻዎች።

4

2. በአሜሪካ ውስጥ የተለመደው አጭር ግብዣ እና እርሱን የመቀበል ዝግጁነት በምስራቁ አለም ክብር የጎደለው እንደሆነ ይቆጠራል። በምስራቁ አለም የተጋበዘው ሰው በመጀመሪያ መቀበል የለበትም ፣ ግብዣውን ውድቅ አድርጎ እንዲለመን ማድረጉ ይጠበቃል። (የመጽሐፍ ቅዱስ አገሮች ባሕሪዎችና ልማዶች)።

3. በሚቀጥሉት ጽሑፎች ውስጥ ይህንን የመረዳት አንድምታ ምን ሊሆን ይችላል?

ሀ. ሉቃስ 14:23፡— “ጌታውም ባሪያውን፦ ቤቴ እንዲሞላ ወደ መንገድና ወደ ቅጥር ውጣና ይገቡ ዘንድ ግድ በላቸው፤” አለው።

Made with FlippingBook flipbook maker