Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide

2 0 0 /

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

³ እነዚህን መሰረታዊ እና ተጨማሪ መሳሪያዎች በሁለቱ ዓለማት: በጽሁፉ አለም እና በዘመናዊው አለም፣ መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ እንዲረዱን በትክክል እንጠቀማቸዋለን። የቅዱሳት መጻሕፍትን ምስክርነት የሚክድ ወይም የሚቃረን የማንኛውም አስተርጓሚ ማብራሪያ ወይም መላ ምት ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም። ስለ ክርስቶስ ማንነት እና በመስቀሉ በኩል ስላደረገው የቤዛነት ስራ በቅዱሳት መጻህፍት የተነገረውን ግልጽ የሆነ አቋም የሚጻረር ምንም አይነት ማመሳከሪያ ተቀባይነት የለውም። ማመሳከሪያዎች በመጽሐፍ ቅዱሳዊ አተረጓጎም ውስጥ ስለሚኖራቸው ጠቀሜታ ጥያቄዎችዎን አብረውህ ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር ለመወያየት ጊዜው አሁን ነው፡፡ ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችንብ በሚረዱን እንደዚህ ባሉ የተትረፈረፉ አጋዥ መሳሪያዎች ስለባረከን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን። ነገር ግን እነዚህን መሳሪያዎች የጽሁፍ ጥናታችንን ፈጽሞ እንዳይተኩብን መጠንቀቅ አለብን። መጽሐፍ ቅዱስን በግልህ በምታጠናበት ጊዜ የእራስህን የማመሳከሪያዎች አጠቃቀም በጥንቃቄ መገምገም አለብህ፤ ለእራስህም እድገት ስትል ትክክለኛውን አጠቃቀም ለማግኘት ጥረት አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስን በምታጠናበት ወቅት እነዚህን መሣሪያዎች እንዴት እየተጠቀምክ እንደሆነ ለመገምገም ከታች ያሉትን ጥያቄዎች ተጠቀም፦ * በአሁኑ ጊዜ በግል የመጽሐፍት ስብስብህ ውስጥ ምን ያህሉ መሰረታዊ ማመሳከሪያዎች አሉህ? ከእነዚህ ውስጥ ቅዱሳት መጻሕፍትን ስታጠና ብዙውን ጊዜ የምትጠቀመው የትኛውን ማመሳከሪያ ነው? * በመጽሐፍ ቅዱሳዊው ዓለም እና በዘመናዊው ዓለም መካከል ስላለው ልዩነት ያለህን ግንዛቤ እንዴት ትመዝነዋለህ? ይህንን ክፍተት ለማጥበብ የማመሳከሪያዎች አጠቃቀምህን እንዴት ትገመግመዋለህ? * የተለያዩ ማመሳከሪያዎች እንዴት ነው ጥቅም ላይ የሚውሉት? በሌላ አነጋገር፣ በእኛ እና በመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎችና ተደራሲያን ባህል መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ለመርዳት እያንዳንዱ ማመሳከሪያ እንዴት እና በምን መልኩ ዕውቀት ያስጨብጣል? * ከመሠረታዊ መሳሪያዎች ውስጥ ከሁሉም ባነሰ መልኩ የምትጠቀመው የትኛውን ነው? ለምን? በሌላ መልኩ ከተጨማሪ ማመሳከሪያዎች፣ ከሁሉም በላቀ እና ከሁሉም ባነሰ መልኩ የምትጠቀመው የትኞቹን ነው? ለምን? * የትኛውን ተከታታይ ማብራሪያ ነው በብዛት የምትጠቀመው? ዋነኛ ትኩረቶቻቸውና ሃሳቦቻቸው ምን እንደሆኑ ታውቃለህ? ይህ አንተ ለእነዚህ ማመሳከሪያዎች በሚኖርህ አጠቃቀምዎ ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራል? * ብዙ ጊዜ የምትጠቀመው የትኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ነው? ምን ያህል የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችስ አሉህ፣ እና ቃሉን ስታጠና እንዴት ትጠቀምባቸዋለህ? የተለያዩ የቅዱሳት መጻሕፍት ምንባቦችን ትርጉም እንድትገነዘብ እንዴት ይረዱሃል? * መጽሐፍ ቅዱስን በትክክል ለማጥናት ብዙ ጊዜ የምታገኘው መቼ ነው - መደበኛ የጥናት ልምዶች አሉህ ወይስ ስትችል ብቻ ነው የምታጠናው? መጽሐፍ ቅዱስን የምታጠናው

የተማሪው ትግበራ እና አንድምታዎች

4

Made with FlippingBook flipbook maker