Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide
5 4 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
ምደባዎች
2 ጴጥሮስ 1: 19-21
የቃል ጥናት ትውስታ
ለክፍል ለመዘጋጀትና የሚቀጥለውን ሳምንት የምንባብ ምደባ ለማግኘት www.tumi.org/books ን ጎብኝ ወይም መምህርህን ጠይቅ።
የንባብ የቤት ስራ
በቀጣዩ ክፍለ ጊዜ ስለዚህኛው ሳምንት የትምህርት ይዘት (የቪዲዮ ትምህርቱን ይዘትና መመሪያውን) አጭር ፈተና ይሰጥሃል፡፡ የትምህርቱን ዋና ዋና ሃሳቦች በጥናትህ መሸፈንህን አረጋግጥ፡፡ የተሰጠህን የንባብ ስራ በሚገባ አጠናቅቀህ አዘጋጅ፡፡ የተመደበውን ንባብ አንብብ እና እያንዳንዱን ንባብ ከአንድ ወይም ከሁለት በማይበልጥ አንቀጽ አጠቃልል። በዚህ ማጠቃለያ በእያንዳንዱ ንባብ ውስጥ ዋና ነጥብ ነው ብለህ የምታስበውን የተሻለ ግንዛቤ አቅርብ። ስለ ዝርዝር ጉዳዮች ብዙ መጨነቅ ሳያስፈልግህ የዚያን የመጽሐፍ ክፍል ዋና ሃሳብ ብቻ አቅርብ፡፡ እባክህ እነዚህን ማጠቃለያዎች በሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ይዘሃቸው ቅረብ፡፡ (እባክህ በዚህ ትምህርት መጨረሻ የሚገኘውን “የንባብ ማጠናቀቂያ ገጽ” ተመልከት፡፡) በዛሬው ትምህርታችን የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጓሜ አስፈላጊነት እና የሕያው እግዚአብሔር ዘላለማዊ ቃል የልባችንን፣ የአዕምሮአችንን እና የፈቃዳችንን ዝግጅት እንደሚፈልግ ተመልክተናል። እንደ መለኮታዊ እና ሰዋዊ መጽሐፍ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ለመረዳት በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ላይ መደገፍ እና ቃሉን ከመተግበራችን በፊት ህይወታችንን እንዲለውጥ ለመፍቀድ ዝግጁ መሆን አለብን። በቀጣዩ ሴግመንት ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስን እስትንፋሰ እግዚአብሔርነት እና ስልጣን መርምረናል፣ እንዲሁም ዘመናዊው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትችት በዛሬው የእግዚአብሔር ቃል ግንዛቤ ውስጥ ስላለው ሚና ተወያይተናል። በሚቀጥለው ትምህርታችን ደግሞ የቅዱሳት መጻሕፍትን እውነት እንድንረዳ እና በጥንታዊ እና በዘመናዊው ዓለማችን መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ወደ ተዘጋጀው ቀላል ግን ውጤታማ መንገድ ወደሆነው ባለ ሶስት ደረጃ ሞዴል የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ በበለጠ ዝርዝር ውስጥ እንገባለን። ይህ ሞዴል የእግዚአብሔርን መልእክት ለመጀመሪያዎቹ ተደራሲያን እንድንረዳ፣ የዛሬውን አጠቃላይ መሠረታዊ መርሆች እንድናውቅ እና በሕይወታችን ተግባራዊ ለማድረግ እንድንችል በጸሎት የሆነና ስርዓትን የተከተለን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማጥኛዎችን መጠቀምን ይጨምራል።
ሌሎች የቤት ስራዎች
1
ገጽ 296 9
ለቀጣዩ ትምህርት መዘጋጀት
ይህ ሥርዓተ-ትምህርት የThe Urban Ministry Institute (TUMI) የሺዎች ሰዓታት የሥራ ውጤት በመሆኑ ያለ ፈቃድ ማባዛት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ TUMI እነዚህን መማሪያዎች ለእግዚአብሔር መንግሥት እድገት ለመጠቀም ለሚፈልጉ ሁሉ ድጋፍ ያደርጋል፤ በተጨማሪም ለማባዛት በተመጣጣኝ ዋጋ ፈቃድ ይሰጣል ፡፡ እባክህ ይህ መጽሐፍ በትክክል ፈቃድ ያገኘ መሆኑን ከመምህርህ ጋር በመሆን አረጋግጥ፡፡ በ TUMI እና በፈቃድ አሰጣጥ ፕሮግራማችን ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት Www.site.org እና Www.tumi.org/license ን ጎብኝ፡፡
Made with FlippingBook flipbook maker