Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide
/ 6 3
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
• በክርስቶስ ጌትነት ስር የጽድቅ ባሪያዎች እንደመሆናችን መጠን ቃሉን በሕይወታችንና በአገልግሎታችን ሁሉ እንድንታዘዝ ተጠርተናል፤ ስለዚህ ሁሉም ሕጋዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜዎች የእግዚአብሔርን ቃል ለህይወት ለውጥ አላማ እንጂ ለአእምሮ መረጃ ለመስጠት አይደሉም።
ሁሉም ሰው መጽሐፍ ቅዱስን የመተርጎም ዘዴ አለው ብታምንም ባታምንም፣ ሁሉም ሰው መጽሐፍ ቅዱስን የሚተረጉምበት ዘዴ አለው። ነገር ግን ሁሉም ዘዴዎች እኩል ውጤታማ አይደሉም። አንዳንዶች የአስማት ጣትን ዘዴ ይጠቀማሉ፥ ይህም አንዳንድ መለኮታዊ መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግን፣ አንድን የተወሰነ ጥቅስ—በተለምዶ ዓይኖቻችንን ጨፍኖ ማግኘት—እና ያንን የቅዱሳት መጻሕፍት ክፍል በእግዚአብሔር የተሰጠ መልስ ወይም እውነት አድርጎ መውሰድን ያካትታል። በዚህ ልንስቅ እንችል ይሆናል፣ ነገር ግን አውዶችን ችላ ስንል ብዙ ጊዜ እኛም ወደዚያው እንቀርባለን። ደግሞም መጽሐፍ ቅዱስን አብዝተው የሚያነቡ ነገር ግን መጽሐፉን በአጠቃላይ ለመረዳት ብዙ ርቀው የሚሄዱ አይመስሉም። ብዙ ሊጠቅሱ ይችላሉ፣ ነገር ግን ምንባቡ ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት ይቸገራሉ። ሌሎች ደግሞ ጽንፈኛ የአምልኮን ሥርዓት ይከተላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ያለማቋረጥ ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸው ለማድረግ የታሰበ ይመስል በአሁኑ ጊዜ “የሚያሟሙቃቸውን” ብቻ ያነባሉ። እነዚህ ሁሉ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን የመተርጎም ሥርዓቶች አሏቸው፣ ስለዚህም ለምን እንደዚህ አይነት ዘዴዎች ወደ መንፈሳዊ ጤናማነት እንደማይመሩ ለመረዳት አስቸጋሪ አይደለም። ከእነዚህ ዘዴዎች የተነሳ—ከፊል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዘዴዎች እና ከፊል የትርጓሜ ዘዴዎች—ብዙዎቹ ደካማ ሲሆኑ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጠንካራ የሆነ ነገር የማግኘት ተስፋቸውም ዝቅተኛ ነው። እንደነዚህ ያሉት ልማዶች መጽሐፍ ቅዱስን በኃይልና ፍሬያማ በሆነ መንገድ የመጠቀም የብስለት ችሎታን በፍጹም አያመጡም። የአተረጓጎም ዘዴዎች ግዴለሽ ወይም ስልታዊ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ስልታዊ አተረጓጎም ቢሆን እንኳን ውጤታማ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል፣ በመሆኑም የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጉም ያበላሻል። የእግዚአብሔር ፈቃድ አማኞች መጽሐፍ ቅዱስን በሚገባ በመረዳት፣ ሚዛናዊ በመሆንና የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን በቀላሉ በማገናዘብ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ የሚችሉበት ደረጃ ላይ መድረስ ነው።
2
~ Paul Karleen. The Handbook to Bible Study. (electronic ed.). New York: Oxford University Press, 1987.
Made with FlippingBook flipbook maker