Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide
/ 6 7
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
II. ደረጃ አንድ፦ ዋናውን ሁኔታ መረዳት (ጽሑፉን በራሱ ውል ማሰር)
ሀ. አንድን ጽሑፍ በመጀመሪያ በቀድሞ ሁኔታው ለመረዳት ለመፈለግ ወሳኝ ምክንያቶች አሉ።
1. ዋናዎቹ የባህል እንቅፋቶች በቀድሞው ባህል እና በጊዜያችን መካከል አሉ።
2. ቋንቋዎቹ (ዕብራይስጥ፣ አራማይክ እና ኮይነ ግሪክ) ከኛ ቋንቋዎች ይለያሉ።
3. እኛ ጎሳ ተኮር ነን (በእራሳችን ባህል ሙሉ በሙሉ የተዘፈቅን ነን፣ የእኛ የየሆነውም የተሻለ ነው ብለን እናምናለን)።
2
4. መጽሐፍ ቅዱስን የምናነበው በዘመን መለኪያ (አናክሮኒስቲክ) መንገድ ነው (ማለትም በዛሬው ጊዜ ያለንበትን ሁኔታ በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን በነበረበት ሁኔታ በማሰብ ነው) ።
5. ጂኦግራፊያዊ፣ ታሪካዊ እና ማህበራዊ ስህተቶችን ለመስራት እንጋለጣለን።
ለ. የመጀመሪያውን ሁኔታ ለመረዳት በጣም አስቸጋሪ የሆነው ለምንድነው?
1. እኛ እዚያ አልነበርንም!፡ የቅዱሳት መጻሕፍት ዘገባዎች በሚሰጡበት ጊዜ ዛሬ በሕይወት ያለ ማንም አልነበረም።
2. የመጽሐፍ ቅዱስን ቋንቋዎች (ግሪክ፣ አራማይክ እና ዕብራይስጥ) አጠቃቀሞች ወይም ልዩነቶች አናውቅም።
Made with FlippingBook flipbook maker