Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide
/ 7 7
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
እባክህ በነዚህና በሌሎችም በዚህ ቪዲዮ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች በቂ ጊዜ ወስደህ ምላሽ ለመስጠት ሞክር፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ የሶስት ደረጃ ሞዴል የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ውጤታማ ዘዴ መሆኑን ተመልክተናል ይህም የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት እንድንረዳ እና በጥንታዊ እና በዘመናዊ ዓለማችን መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ይረዳናል። የቅዱሳት መጻሕፍት ተማሪዎች እንደመሆናችን መጠን የቅዱሳት መጻሕፍትን ተፈጥሮ እንደ ጥንታዊ ሥነ ጽሑፍ እንዲሁም የእግዚአብሔርን አእምሮና ፈቃድ በምንፈልግበት ጊዜ በቤተክርስቲያን ውስጥ አስተማሪያችንና መሪያችን የሆነውን መንፈስ ቅዱስን የሚያከብር ዘዴ ያስፈልገናል (1ቆሮ. 2.9-16)። የሚከተሉትን ጥያቄዎች በመጠቀም የቪዲዮውን ክፍል ለመቃኘት ሞክር፡፡ መልሶችህን በቅዱሳት መጻሕፍት አስደግፍ፡፡ 1. የሶስት ደረጃ ሞዴል የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ትርጓሜ ምንድን ነው? ይህ ዘዴ በተለይ በጥንታዊውና በዘመናዊው ዓለማት መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ የሚረዳን እንዴት ነው? መጽሐፍ ቅዱስን በትክክል ለመተርጎም በእኛና በመጽሐፍ ቅዱስ ዓለም መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? 2. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጉም ለመረዳት ዘዴን መመርመር አስፈላጊ እንደሆነ የሚገልጸው የትኛው ክፍል ነው? (የሐዋርያት ሥራ 17: 11፤ ኢሳይያስ 8: 20፤ ዕዝራ 7: 10፤ ወዘተ) ? 3. በመጽሐፍ ቅዱሳዊ አተረጓጎም ውስጥ ማንኛውንም ዘዴ ከመጠቀም ጋር የተያያዙ ጥቅሞች እና ጥንቃቄዎች ምን ምን ናቸው? በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ያሉትን የእግዚአብሔርን እውነቶች ለማወቅ እና በሕይወታችን ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ በምንፈልግበት ዘዴ እና በራሳችን ማስተዋል ላይ ከመጠን በላይ እንዳንደገፍ የሚጋርደን ምንድነው? 4. ከቅዱሳት መጻህፍት አንድን ክፍል ስናጠና ሁልጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስን ‘አጠቃላይ ገጽታ’ እና ‘አጠቃላይ መልእክት’ ማስታወስ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? የእግዚአብሔርን ቃል ማጥናት በኢየሱስ ክርስቶስ አካል እና ስራ አማካኝነት ከእግዚአብሔር የመጨረሻ መገለጥ ትርጉም እና መልእክት ጋር በቀጥታ መገናኘት እና እርሱንም ማብራራት ያለበት በምን መልኩ ነው? መልስህን በምሳሌ አስረዳ። 5. የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት “ሰዋሰው-ታሪካዊ” ዘዴ ምንድን ነው? የሶስት ደረጃ ሞዴል ከዚህ ጋር እንዴት ይዛመዳል? በተመሳሳይ መልኩ፣ የሶስት ደረጃ ሞዴል የአንድን ጽሑፍ ትክክለኛ ትርጉም እና አጠቃላይ የመጽሐፍ ቅዱስን አንድነት እንድንረዳ የሚረዳን እንዴት ነው? 6. በተለያየ መንገድ (ለምሳሌ በግጥም፣ በመዝሙር፣ በደብዳቤ፣ በታሪክ ወዘተ) ወደእኛ የደረሱትን የቅዱሳት መጻሕፍት ታማኝነት ማክበር አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? የሦስት ደረጃ ሞዴልስ ይህን የሚያደርገው እንዴት ነው? 7. በሶስት ደረጃ ሞዴል ውስጥ በእያንዳንዱ ደረጃ ውስጥ የተካተቱትን ወሳኝ ምክንያቶች በአጭሩ ግለጽ። መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን በነበሩና አሁን ግን በዚህ ዘመን
መሸጋገሪያ 1
የተማሪው ጥያቄዎችና መልሶች
ገጽ 300 3
ምን እንደሆነ ብቻ ሳይሆን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ጳውሎስ ጢሞቴዎስን ‘የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር’ ሰው ለመሆን እንዲጥር ሲነግረው (2 ጢሞ. 15) የእውነትን ቃል በቅንነት የሚይዝ ሰው አለመሆን እንዴት አደገኛ ሊሆን እንደሚችል ከግምት በማስገባት ነው። ይህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት መተርጎም እንዳለብን የሚያመለከቱ ጠቃሚ ጥያቄዎችን ያስነሳል። መጽሐፍ ቅዱስን በጥበብ ለመጠቀም መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሆነ ብቻ ሳይሆን እንዴት ልንጠቀምበት እንደሚገባም ማወቅ ያስፈልጋል። ~ Donald A. Carson. New Bible Commentary : 21st Century Edition. (electronic ed. of the 4th ed.). Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 1997.
2
Made with FlippingBook flipbook maker