Church PLANT Manual, Amharic Edition

ወርልድ ኢምፓክት ከ2016 ዓ.ም. እንደ አውሮጳውያን አቈጣጠር ጀምሮ በርካታ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድኖች በአሜሪካ እና በመላው ዓለም በራሳቸው የአገልግሎት ዐውድ ውስጥ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ስልት እንዲቀይሱ በማስታጠቅና በማሠልጠን ላይ ይገኛል። የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ የኢቫንጄል የከተማ ቤተ ክርትስቲያን ተከላ ትምህርት ቤት መምሪያ ነው። ይህ መርሕን መሠረት ያደረገ መጽሐፍ የተዘጋጀው የቤተ ክርስቲያ ተከላ ቡድኖች በራሳቸው ዐውድና አስፈልጎት ውስጥ ስልታዊ ዕቅድ ማዘጋጀት እንዲችሉ ለማገዝ ነው። ዐዲስ ቤተ ክርስቲያን እየተከሉ ቢሆን ወይም ዳግም ተከላ ለማድረግ (እንደ ገና ለመጀመር፣ ለማነቃቃት፣ ወይም እንደገና ለማስጀመር) እየተዘጋጁም ቢሆን አልያም አኹን ባለ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የመጋቢዎችን አመራር ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ወይም የቤተ ክርስቲያን ተከላ አ

የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

አርትዖት ሬቨረንድ ቴድ ስሚዝ

AMHARIC

የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

አርትዖት፦ ቴድ ስሚዝ (ሬቨረንድ)

World Impact Press 3701 East 13th Street North Suite 100 Wichita, Kansas 67208

የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

©2017 ዓ.ም. World Impact, Inc. መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው። ከአሳታሚው የጽሑፍ ፈቃድ ካልተሰጠ በቀር ይህን መጽሐፍ ሙሉ በሙሉም ኾነ በከፊል ማባዛት፣ መገልበጥ፣ በምስልም ኾነ በድምፅ መቅረጽ አይቻልም።

World Impact 3701 East 13th Street North Suite 100 Wichita, KS 67208

© 2017 ዐማርኛ ትርጕም፦ የአምላክ ቸርነት በዛብኽ

ISBN: 978-1-62932-089-2

አሳታሚ ወርልድ ኢፓክት ፕሬስ የእንግሊዝኛው መጽሐፍ ርእስ፦ Church PLANT Manual

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሱት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የተወሰዱት መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™ ነው። የቅጅ መብት © 2001 በ Biblica, Inc. ፈቃድ የተገኘባቸው ናቸው። መብቱ በመላው ዓለም በሕግ የተጠበቀ።

ይህ መጽሐፍ ለዶ/ር ዶን ዴቪስ የተበረከተ ሲኾን ርሱ ባይኖር ኖሮ ይህ መጽሐፍ ለፍሬ ባልበቃ ነበር። ርሱ ነቢያዊ ድምፅ ነው፣ በርእሰ ጒዳዩ ላይ በርካታ እጅግ ጠቃሚ ጽሑፎችን አበርክቷል፣ የአመራር ጉልብትና ማሠልጠኛ መጽሐፎችን አዘጋጅቷል፣ እንዲሁም በአሜሪካና በመላው ዓለም ጤናማ አብያተ ክርስቲያናት እንዲተከሉ በየስፍራው የሚገኙ ክርስቲያኖች በክርስቶስ ሥራ ላይ እንዲሳተፉ ዘወትር ጥሪ ያቀርብ ነበረ። ዶ/ር ዳቪስ በነገረ መለኮት፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥናቶች፣ እና የከተማ ቤተ ክርስቲያናት ተከላ ላይ የሠራቸው ሥራዎች የዚህ ጽሑፍ ጠንካራ መሠረቶች ናቸው። በእጅጉ የዶ/ር ዳቪስ ውለታ አለብን። ይህን መጽሐፍ በጥንቃቄ የሚያነብቡ ሰዎች በቀላሉ ሊያስተውሉ እንደሚችሉት በርካታ ጽሑፎችን ከርሱ የጠቀስን ሲኾን በርካታ ትምህርቶቹንም በዚህ መጽሐፍ ውስጥ አካትተናል። ይህ መጽሐፍ የርሱን ታላላቅ ሥራዎች የሚያስታውስ እና በድኅነት በተጎዲ ማኅበረ ሰቦች ውስጥ የክርስቶስ ኢየሱስን ዐርማ የሚያውለበልቡ ጤናማ አብያተ ክርስቲያናት እንዲበዙ እና ሰዎችም እግዚአብሔር በክርስቶስ የገለጠውን ፍቅር በማወቅ ወደ ድነት እንዲመጡ እንጸልያለን። ይህን መጽሐፍ በሚያነብቡ ዘንድ ኹሉ የጥሪ ድምፁ ያስተጋባ። ይህም ጥሪ ወደ ኢየሱስን የሚያመላክተን፣ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ጥረትን የሚያነሣሣ፣ እንዲሁም የክርስቶስን መንግሥት ለርሱ ክብር የሚያሰፋ ይኹን።

- ቴድ ስሚዝ (ሬቨረንድ)

ማውጫ

ቀዳሚ ቃል

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

xi

መቅድም .

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

xv

ምስጋና

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

xix

መግቢያ .

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

.

1

የቤተ ክርስቲያን ተከላ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረቶች . . . የጳውሎስ ምሳሌዎች ከሐዋርያት ሥራ፥ ጳውሎሳዊ ዑደት .

3 5 7

የቤተ ክርስቲያን ተከላ አጠቃላይ ዳሰሰ .

.

.

.

.

ክፍል 1፥ ዝግጅት �

� � �

� 13

ትምህርት 1 ትምህርታችሁን መቅረጽ

.

.

.

.

.

.

.

.

15

ትምህርት 2 ቡድን ማዋቀር

.

.

. . . .

.

. .

.

18

ትምህርት 3 ተግዳሮቶችን የመቋቋም ዐቅምን ማጐልበት

.

.

.

.

23

የቡድን መልመጃዎች፡- ዝግጅት

� � �

� 27

መልመጃ 1 ዐውድ መመሥረት

.

.

.

.

.

.

.

.

.

29

መልመጃ 2 ዕሴትንና ርእይን መተለም .

.

.

.

.

.

.

.

31

መልመጃ 3 የቡድን ውጤታማነት .

.

.

.

.

.

.

.

.

34

መልመጃ 4 ተግዳሮቶችን የመቋቋም ዐቅምን ማጐልበት

.

.

.

.

36

ክፍል 2፥ መጀመርና መሰባሰብ ���������������������������������������������������39 ትምህርት 4 የወንጌል አንቀሳቃሽ ኀይል ������������������������������������������������������ 41 ትምህርት 5 ባህልንና ዐውድን ማሰስ ��������������������������������������������������������� 47 ትምህርት 6 ስብከተ ወንጌል እና ክትትል ��������������������������������������������������� 50 የቡድን መልመጃዎች፥ መጀመርና መሰባሰብ �������������������������������� 57 መልመጃ 5 የወንጌል አንቀሳቃሽ ኀይል ������������������������������������������������������ 59 መልመጃ 6 ባህልንና ዐውድን ማሰስ ��������������������������������������������������������� 61 መልመጃ 7 ስብከተ ወንጌል እና ክትትል ��������������������������������������������������� 63 ክፍል 3: ማሳደግና ሽግግር (መብዛት) ���������������������������������������� 65 ትምህርት 7 ውጤታማ ደቀ መዝሙር አድራጊነት ���������������������������������������� 67 ትምህርት 8 መሪዎችን ማሳደግ ����������������������������������������������������������������� 71 ትምህርት 9 የመብዣ መንገዶችን መቀየስ �������������������������������������������������� 77 የቡድን መልመጃዎች፥ ማሳደግና ሽግግር �������������������������������������83 መልመጃ 8 እድገት፥ ቤተ ክርስቲያንን ማሳደግ ������������������������������������������� 85 መልመጃ 9 ሽግግር፥ የመብዛት ስልቶች ���������������������������������������������������� 87

ክፍል 4፥ ሁሉንም ነገር በጋራ ማድረግ (ማቀናጀት) ������������������������89 ትምህርት 10 በአገልግሎት ውስጥ ጥበብን መጠቀም ���������������������������������� 91 ትምህርት 11 የራሳችሁን ስልት ማበጀት ����������������������������������������������������� 101 ትምህርት 12 ለማሸነፍ መላመድ �������������������������������������������������������������� 105 የቡድን መልመጃዎች፥ ሁሉንም በጋራ ማቀናጀት ��������������������������113 መልመጃ 10 የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቀን መቍጠሪያ ማዘጋጀት �������������������� 115 መልመጃ 11 የኢቫንጄል ሰነዳችሁን አጠናቅቁ �������������������������������������������� 118 ተጨማሪ መልመጃዎች የኢቫንጄል መምሪያ ሰነድ ናሙና �������������������������������������������� 120 ድኅረ ቃል �������������������������������������������������������������������������������� 123

ቀዳሚ ቃል

ቤተ ክርስቲያኔን እመሠርታለሁ ሰዎች የሚድኑት ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመሄድ ብቻ አይደለም። እግዚአብሔር ሰዎችን ይፈጥራል። ይህ ሊጠፋን አይገባም። እንደ አለመታደል ሆኖ ብዙዎች ታላቁን የድነት ታሪክ፣ “እግዚአብሔር ዓለምን ፈጠረ፣ እኛ ኀጢአተኞች ነን፣ ስለዚህ እግዚአብሔር እያንዳንዳችንን ከኀጢአታችን ለማዳን ኢየሱስን ላከው” ወደሚል ቀላል ቀመር አውርደውታል። ፍጥረት፣ ኀጢአት፣ ኢየሱስ ያ ነው መጠቅለያው! አንዳንዶች ታዲያ ይሄ ችግሩ ምንድን ነው? ብለው ይገረማሉ። ችግሩ ይሄ ነው፥ የፍጥረት-ኀጢአት-ኢየሱስ ቀመር በጣም ግላዊ ወደ ሆነ ክርስትና ይመራል፥ እምነታች የግል ሕይወታችን ብቻ እንደሆነ አድርጎ ያቀርባል። ኢየሱስ፥ እኔን፣ ራሴንና እኔን ለማገልገል እንደመጣ የቤተ ክርስቲያንን ደውል ነው። የወንጌሉን መልእክት በእጅጉ አኮስሰነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠን ጥልቅ ታሪክ እንጂ ቀላል ቀመር አይደለም። ኢየሱስ ክርስቶስን ስንመሰክር፥ ክርስቶስ ለኀጢአት ሊሞት መጣ፣ ሰይጣንንና ሥራዎቹ አፈራረሰ፣ እንዲሁም የእግዚአብሔርን መንግሥት አገዛዝ በምድር ላይ ዳግመኛ መሠረተ የሚለውን ዓለምን የሚለውጥ ዐሳብ እያወጅን ነው። ኢየሱስ በሕይወቱ፣ በሞቱ፣ በቀብሩ፣ እና በትንሣኤው ያከናወነው ሥራ ይህን ነው። ከሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ጀምሮ ያሉት የዐዲስ ኪዳን መጻሕፍት በአንዲት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ

xi

xii • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋራ የሚኖር ክርስቲያንን ታሳቢ ያደረጉ መልእክታት ናቸው። ድነት የግል ነው የሚኖረው ግን በማኅበር ነው። ቤተ ክርስቲያንን ከሌሎች ማኅበራዊ ተቋማት ልዩ የሚያደርጋት ምንድን ነው? የቅድስና ጕዳይ። ቅድስና የድል መንገድ ነው። ኀጢአትን ድል የሚያደርግ እና ለለውጥ የሚያዘጋጅ ጕልበት ሰጪ ነው። የእግዚአብሔር ሕዝብ ያደረገን ይህ ነው። በክርስቶስ ላይ ያለን እምነት ለዚህ አብቅቶናል። ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው ያው ኀይል የተለወጡ ሕይወቶችና ማኅበረ ሰቦች ምንጭ ነው። የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የመጀመሪያዎቹ 12 ምዕራፎች የቤተ ክርስቲያን ምሥረታን ታሪክ ይናገራሉ። የመጀመሪያው ቍልፍ ገጸ ባሕርይ ጴጥሮስ ነው። ጴጥሮስ፥ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ በመሠከረ ጊዜ ቍልፍ የቤተ ክርስቲያን ተካይ እንደሚሆን ኢየሱስ ነግሮት ነበረ (ማቴዎስ 16፥18)። ከትንሣኤው በኋላ፥ ኢየሱስ ከተከታዮቹ ጋራ 40 ቀናት አሳልፏል። በእነዚህ ጊዜያት የመንፈስ ቅዱስ ኀይል ምንጭ ተገልጦ ነበረ። ኢየሱስ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና ሁሉም አማኞች ሁሉ የመንግሥቱ ዜጎች ሆነው መኖር እንዳለባቸው አስተምሯል። ይህ እንዲሆን ያስቻለው የመንፈስ ቅዱስ ሀልዎት ነበረ። ርሱ ዳግመኛ ተመልሶ እስኪመጣና ክፈን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እስኪደመስስ ድረስ መንግሥቱ እንደማትመጣ ተናግሮ ነበረ። እስከዚያ ድረስ ሁሉም የርሱ ተከታዮች በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በኩል የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማስፋት ይሠራሉ። አልቪን ሳንደርስ የወርልድ ኢምፓክት ፕሬዝዳንት እና ሲ.ኢ.ኦ. መጋቢት 19፥ 2016 ዓ.ም.

የቤተ ክርስቲያን ተከላ ዳይሬክተር መልእክት የአጽናፈ ዓለሙ ገዥ ትርክት የሁለት መንግሥታት ግጭት እውነታ ነው። የእግዚአብሔር መንግሥት በአሸናፊው፥ በናዝሬቱ ኢየሱስ አማካይነት ድል አድርጓል። በትሥጕቱ፣ በስቅለቱና በትንሣኤው አማካይነት ኢየሱስ

ቀዳሚ ቃል • xiii

“የአለቆችንና የባለሥልጣናትንም ማዕረግ በመግፈፍ በመስቀሉ ድል ነሥቶ በአደባባይ እያዞራቸው እንዲታዩ አደረገ” (ቈላስይስ 2፥15)። ምንም እንኳ የጨለማው መንግሥት ቢሸነፍም ሰይጣንና ጭፍሮቹ በቢሊዮን የሚቈጠሩ ነፍሶችን በመንፈሳዊ እስር ጠፍንገው አስረዋቸዋል። አንዳች ነፍስ እንድትጠፋ አይሻም ነገር ግን ሁሉም በወንጌል ኅይል ነጻ ይወጡ ዘንድ ኢየሱስ ለቤተ ክርስቲያኑ ትነሣ፣ ትወጣ፣ ወደ ፊት ትኼድና ትበዛ ዘንድ ተልእኮ ሰጥቷታል። ይህ እጅግ በጣም ወሳኙ የቤተ ክርስቲያን ተግባር ነው - ተልእኮ፥ ይኸውም ሥልጣን ያላቸው ላኪዎች (የታወቁ፣ የታጠቁ፣ የተሾሙ) ሰዎችን ቤተ ክርስቲያን ወዳልተተከለበት አካባባቢ ወንጌልን ለማወጅ፣ ነፍሳትን ለማዳን፣ የተለወጡትን ደቀ መዛሙርት ለማድረግ እንዲሰበስቡ መላክ ሲኾን እንዲሁም በዚያ ማኅበረ ሰብእ ውስጥ የእግዚአብሔርን መንግሥት ፍሬ የሚያፈሩ አብያተ ክርስቲያናትን የሚያበዙ የእግዚአብሔር መንግሥት ማኅበረ ሰቦችን ማብዛት ነው። የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ ቤተ ክርስቲያን ተካይ ቡድኖችን ለማሠልጠን የተዘጋጀ ሲኾን መሠረታዊ መርሑም ጤናማ አብያተ ክርስቲያናትን በዚህም ኾነ በዓለም ዙሪያ በድኽነት ውስጥ በሚገኙ ማኅበረ ሰቦች ውስጥ መትከል የሚል ነው። ጌታ በቅርብ ይመጣል፥ ዋጋውም በርሱ ዘንድ አለ። እስከዚያው ድረስ ግን አብያተ ክርስያቲያናት በየስፍራው ይተከሉ ዘንድ የመኸሩ ሠራተኞችን የመለየት፣ የማስታጠቅና የማገዝ ሥራችንን ቸል አንበል። “… ወደ ኋላ [ከሚያፈገፍጉት] አይደለንም…” (ዕብራውያን 10፥39) ቦብ ኤንጅል (ሬቨረንድ) የቤተ ክርስቲያን ተከላ ዳይሬክተር መጋቢት 19፥ 2016 ዓ.ም.

መቅድም የኢየሱስ ስም ገና ባልታወቀባቸው ወይም በማይመለክባቸው አካባቢዎች አብያተ ክርስቲያናትን መትከል ጥልቅ ጥሪና የክርስቲያናዊ ተልእኮ ዋና አካል ነው። ይህ ተልእኮ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ ተልእኮ ዋና ዐሳብ ጋራ የተሳሰረ ሲሆን ይህም በዓለም ያሉ ሰዎች ሁሉ የእግዚአብሔርን ጥሪ እንዲያውቁት፣ እንዲሁም በልጁ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መንግሥቱ እንድትገዛ ያደርጋል። ግራ በተጋባውና በተሰበረው ዓለም ውስጥ ጥቂት ተጸብራቅ እንኳ ለዚህ ክቡርና አሁንም ጠቃሚ ለሆነው ፍለጋ አሳማኝ ምክንያቶችን ይሰጣል። ቤተ ክርስቲያን ተከላ ታላቁን ተልእኮ ለመፈጸም ሐዋርያዊ ዘዴን ይጠቀማል። ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ የሰጣቸው የመጨረሻው ትእዛዝ ታላቁ ተልእኮ መባል ይታወቃል (ማቴዎስ 28፥18-20)፤ በዚህ ትእዛዙም “ሂዱና ሕዝቦችን ሁሉ ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው” ብሏቸዋል። ይህ ኀላፊነት በቅድሚያ በሚያውቁት ወይም አስቀድሞ በተሰበከበት ዐውድ ውስጥ ይጀምርና ወደ ሁሉም መልክዓ ምድራዊና ባህላዊ ድንበሮች ሁሉ ይዘልቃል። የእግዚአብሔርን የድነትና የትድግና ጥሪ ከዚህ ቀደም ያልሰሙ ወይም ሰምተው ምላሽ ያልሰጡ ሰዎች ሁሉ ሊረዱና ሊቀበሉት በሚችሉት መንገድ ምሥራቹን መስማት አለባቸው። ክርስቶስ በማይታወቅባቸው አካባቢዎች አብያተ ክርስቲያናትን መትከል ይህን ጥሪ ያስተጋባል፤ ይህም እያንዳንዱ ሕዝብ ያለበት ቡድን ወንጌልን የመስማት ዕድል እንዲኖረው ያስችለዋል። ደቀ መዝሙርነትና ጥምቀት የሚከናወኑት በአጥቢያ ቤተ

xv

xvi • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

ክርስቲያን በኩል መደረግ ያለበት ሲሆን ይህም ዐዲስ አማኖች በእምነታቸው እንዲያድጉ የሚያስችል መሠረት የሚሆን ማኅበረ ሰብእ ይጥላል። የቤተ ክርስቲያን ተከላ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር መንግሥት ወኪል መሆኗን ዕውቅና ይሰጣል። ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ይባረካሉ (ዘፍጥረት 12፥1-3) ከሚለው ለአብርሃም ከገባለት የተስፋ ቃል አንሥቶ ዮሐንስ ባየው ራእይ ውስጥ የተገለጹት ሕዝቦች፣ ነገዶች፣ ወገኖችና ቋንቋዎች ሁሉ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት እስከሚሰግዱበት (ራእይ 7፥9-10) ትእይንት ድረስ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርክት የእግዚአብሔር መንግሥት አገዛዝ በምድር ላይ የመስፈንን ጭብጥ ይተርካል። ቤተ ክርስቲያን መትከል ሐዋርያዊ ተግባር ሲሆን ይህም የዚህ መንግሥት መስፋፋት ተጨባጭ መገለጫ ነው። ክርስቶስ የሚታወቅበትና የሚከብርበትን አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መትከል የእግዚአብሔር ንጉሥነትና አገዛዝ የሚገለጥበትን (አካባቢ) እና አገዛዙ በዐዲስ ሕዝቦች መካከል (ወኪል) የሚታይበትና የሚታወጅበትን መንገድ ያሳያል። ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ለዓለም ያለው ጽኑ ፍቅር የዐዲስ ኪዳን ዋነኛ መልእክት ነው። ዮሐንስ 3፥16 በልጁ መሥዋዕትነት ለሰው ልጆች ሁሉ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ፍቅር በመግለጽ ይህን ዋና ጉዳይ በብርቱ ጠቅለል አድርጐ ገልጾታል። አብያተ ክርስቲያናትን መትከል ይህን ፍቅር በየአካባቢው፣ በየሰፈሩና በየመንደሩ ተጨባጭ በሆነ መልኩ መግለጥ ነው። ለወንጌል ሩቅ የሚባል፣ የተለየ ወይም ፈታኝ የሚባል ቦታ የለም፤ በየትኛውም ስፍራ ያሉ ሁሉ እግዚአብሔር ትሩፋኑን ለማዳን ያለው ሉዓላዊ ዕቅድና ዘላለማዊ ዓላማ ሊሰሙ ይገባል። እያንዳንዷ ዐዲስ ቤተ ክርስቲያን የመትከል ጥረት የእግዚአብሔርን የድነት ግብዣ አቃፊነት የሚያሳይ ማስረጃ ነው። ያ ዐዲሱ የአማኞች ስብስብ የእያንዳንዱን ሰው እና እያንዳንዷ ነፍስ በእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዕቅድ ውስጥ ያላትን ዋጋ የሚጐላና የሚያረጋግጥ ነው። ቤተ ክርስቲያን ተከላ ገና ለሚያምኑ ሰዎች እግዚአብሔር ያለውን ፍቅር በተጨባጭ የሚያሳይ ወኪል ነው።

መቅድም • xvii

ቤተ ክርስቲያን ተከላ የማኅበራዊና ባህላዊ ለውጦች መለኮታዊ አቃጣጣይ ነው።

በመጨረሻም፣ የክርስቶስ ወንጌል ምሥራች በአንድ ማኅበረ ሰብእ ውስጥ ሕያው ሲሆን በአካባቢው ያሉ ጕባኤዎች በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በመንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና በባህላዊ መንገድ የለውጥ ብርቱ ወኪል ይሆናሉ። አብያተ ክርስቲያናት የተስፋ ምስክር ማዕከላት ይሆናሉ፤ በፍትሕ፣ በትምህርት፣ በጤና እና በማኅበረ ሰብ እድገት ውስጥ ተግባራዊ መገለጫዎችን ያቀርባሉ። በማኅበረ ሰቡ ውስጥ በክርስቶስ በኩል እውነተኛውን አምላክ ካለማወቅ የሚመጣውን መንፈሳዊ ባዶነት ብቻ ሳይሆን የማኅበረ ሰቡን አካላዊና ማኅበረ ሰባዊ አስፈልጐቶችንም በተመለከተ ይሠራሉ። ከዚህ ቀደም ወንጌልን ሰምተው በማያውቁ አካባቢዎች ቤተ ክርስቲያናትን በመትከል ክርስቲያኖች ሁለንተናዊ ለውጥ እንዲመጣና የእግዚአብሔር መንግሥት በሙሉ ገጽታዋ እንድትታይ የማድረግ እንቅስቃሴን ሊጀምሩ ይችላሉ። በማጠቃለያ፣ ኢየሱስ ገና ባልታወቀባቸው ቦታዎች ውስጥ አብያተ ክርስቲያናትን ለመትከል በሐዋርያዊ ጥሪ ውስጥ ስትሳተፉ የእግዚአብሔርን ተልእኮ ትፈጽማላችሁ። ቤተ ክርስቲያን ተከላ በዋናነት የቤተክርስቲያን ጥሪ የእግዚአብሔርን ልብ በተግባር ማሳየት መሆኑን ያስተጋባል። ታላቁ ተልእኮንም ያካትታል፣ የእግዚአብሔር መንግሥት መገለጥን ያሰፋል፣ እግዚአብሔር ለሰዎች ሁሉ ያለውን ፍቅር ያሳያል እንዲሁም የመንግሥቱ ሕይወት የሁሉን አቀፍ ለውጥ አቀጣጥይ መሆኑን ያመለክታል። ይህ ተልእኮ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ኀላፊነትን የሚወጣና እጅግ በጣም ጥልቅ ከሆኑት የክርስትና እምነት ተግባራዊ መገለጫዎች ጋራ የሚጣጣም በመሆኑ ዛሬ ላይ የቤተ ክርስቲያን አጣዳፊና አስገዳጅ ተግባር ያደርገዋል። የእግዚአብሔርን መንግሥት፣ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያንን በምታገለግሏቸው ማኅበረ ሰቦች ውስጥ በምትገልጡበት ጊዜ ጌታ ኢየሱስ ዐብሯችሁ እንዲሄድ ከልባችን እንጸልያለን። በመንገዳችሁ ሁሉ ርሱ ከእናንተ ጋራ ይሁን። ዶ/ር ዶን ዳቪስ የፕሬዘዳንቱ ከፍተኛ ሥራ አስፈጻሚ አማካሪ መጋቢት 19፣ 2016 ዓ.ም.

ምስጋና ጸሎታቸው፣ የሰጡን ጊዜ፣ አስተያየታቸውና ጥረቶቻቸውን በቃላት መግለጽ ለማይቻለው የወርልድ ኢምፓክት ሠራተኞች ዕውቅና መስጠትና ማመስገን እፈልጋለሁ። ስሞቻቸውን መቼም አታውቁትም ነገር ግን ለክርስቶስ ያላቸው ቍርጠኛነትና ይህን መጽሐፍ ለማዘጋጀት የሠሩት ሥራ በራሱ ይናገራል። በተለይ ሬቨረንድ ቦብ ኤንጅል፣ ሬቨረንድ ሉክ ራውሊ፣ ሬቨረንድ ጆርዳን ኪንግ፣ ፓስተር ሎሬንዞ ኤሊዞንዶ፣ እና ፓስተር ዴቪድ ኤስትራዳ ይህን ጽሑፍ ለማዘጋጀት ላበረከቱት አስተዋጽኦ፣ ቍርጠኛነትና ጸሎት ላመሰግናቸው እወድዳለሁ። ያለ እነዚህ ሰዎች ታማኝ ወዳጅነት፣ የአገልግሎት አጋርነት፣ እና ያልተቋረጠ ማበረታታት ይህ ሥራ ሕልም ከመሆን አያልፍም ነበረ። ይህ ሥራ እንደሚመሰክረው እኛ በቡድን ሥራ እናምናለን። እግዚአብሔር በልባችሁ ውስጥ ያስቀመጠውን ቤተ ክርስቲያን የመትከል ሸክምን ስታከናውኑ የሚያግዛችሁን ይህን ጽሑፍ ለማዘጋጀት ከበርካታ ቡድኖች ጋራ እንድሠራ ጌታ ባርኮኛል። ለእናንተም የሚጠቅም እንዲሆን እንጸልያለን። ሬቨረንድ ቴድ ስሚዝ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ትምህርት ቤቶች ዲን መጋቢት 19፣ 2016 ዓ.ም.

xix

መግቢያ ሬቨረንድ ቴድ ስሚዝ

የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ መጽሐፍ የተሰናዳው የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድናችሁ የቤተ ክርስቲያን ተከላ መርሖችን እንዲገነዘቡ፣ በኢቫንጌል ትምህርት ቤት የሥልጠና ጊዜያት እነዚህን መርሖች ወደ ተግባራዊ ግቦች የመቀየር ጉዞን ለመርዳት እንዲሁም በመጨረሻም ለሚቀጥሉት ዐሥራ ሁለት ወራት የቤተ ክርስቲያናችሁን ስልታዊ ዕቅድ እንድታዘጋጁ ለማገዝ ነው። የመምሪያ መጽሐፉ እና የኢቫንጌል ትምህርት ቤት ራሱ ዐዲስ አብያተ ክርስቲያናት ለሚተክሉ፣ ዳግም ተከላ (ዳግም ጅማሬ፣ ተሓድሶ ወይም ዳግም ማንሰራራት) ለማድረግ እየተዘጋጁ ላሉ፣ ምጋቤያዊ አመራር ተግባር ወደ ቀጣዩ ትውልድ የሚሸጋገርበትን ኺደት ለሚሹ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን ተከላ እንቅስቃሴን ለማነሣሣት ለሚፈልጉ ሰዎች ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ኢቫንጌል፥ በመርሕ ላይ የተመሠረተ ስልት ሲሆን በበርካታ የተከላ፣ ዳግም ተከላ፣ የሽግግር ወቅቶች እና ሌሎች ዐውዶች ውስጥ ሊተገበር የሚችል ነው። ይህ ደግሞ ለብዙ ዓመታት የተለያዩ ቡድኖች ለራሳቸው ዐውድ ስልት እንዲያጐለብቱ ባሠለጥንንበት ጊዜ የተስተዋለ ነው። ስለዚህ፥ “ተከላ” የሚለውን ቃል ከኢቫንጌል መርሖች ጋራ የተያያዘ አካታች ቃል መሆኑን መረዳት ጠቃሚ ነው።

1

2 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

የትኛውም መምሪያ መጽሐፍ ብቻውን የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድኖችን በሥራቸው ለማገዝ ሙሉ በሙሉ በቂ ባለመሆኑ ከዚህ በተጨማሪ ሁሉም የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድኖች በኢቫንጌል ትምህርት ቤት ሥልጠናቸውን ሲያጠናቅቁና የቡድናቸውን ልዩ መንገድ ለይተው ማወቅ ሲችሉ በኢቫንጌል ትምህርት ቤት የሚመራቸው የኢቫንጌል አሠልጣኝ ይመደብላቸዋል። ከኢቫንጌል ትምህርት ቤት ባሻገር ትምህርቱን በወርልድ ኢምፓክት የሚያጠናቅቅ እያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድን እግዚአብሔር ለክብሩ በልባቸው ውስጥያስቀመጠውን ቤተ ክርስቲያን የመትከል ሸክም የኢቫንጌል መስክ አሰልጣኝ ከትምህርቱ በኋላ ለዐሥራ ሁለት ወራት ከቡድኑ ጋራ ዐብሮ የሚሠራና ሸክማቸውን የሚጋራ አሠልጣኝ ይመደብላቸዋል።

መግቢያ • 3

የቤተ ክርስቲያን ተከላ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረቶች ሬቨረንድ ቴድ ስሚዝ

ብዙውን ጊዜ “ዓለም አቀፋዊት” 1 በመባል የምትጠራውን ቤተ ክርስቲያኑን ጌታ እንዲሠራ (ማቴዎስ 16፥18) እንዲሁም ጌታ ራሱ “አካሉ የኾነችው የቤተ ክርስቲያን ራስ” መኾኑን (ቆላስይስ 1፥18) መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ይናገራል። ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን የመትከል ተግባር ሙሉ በሙሉ “ስለዚህ ሂዱና ሕዝቦችን ሁሉ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሯቸው፤ እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ” (ማቴዎስ 28፥19-20) በሚለው የክርስቶስ ሥልጣንና ትእዛዝ ላይ የተሠረተ ነው። ይኹን እንጂ ዛሬ ቤተ ክርስቲያናትን ለመትከል የሚተጉ ሰዎች “ለምን ሌላ ቤተ ክርስቲያን ያስፈልገናል? በመላው አሜሪካ ቤተ ክርስቲያናት ሞልተዋል” ሲሉ ይደመጣሉ። ተጨማሪ ቤተ ክርስቲያናት ለምን ያስፈልጉናል? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ (ከውድቀት ጀምሮ፣ ዘፍጥረት 3፥1-15) “በዓለም ላይ” የዲያብሎስ ተጽዕኖ እንዳለ በግልጽ ይነግረናል። ኢየሱስም፥ “የዚህ ዓለም ገዥ” (ዮሐንስ 12፥31) በማለት ጠርቶታል። ጳውሎስም “በአየር ላይ [ያ]ሉት መንፈሳውያን ኀይላት ገዥ… ለእግዚአብሔር በማይታዘዙት ሰዎች ላይ [የ]ሚሠራው መንፈስ (ኤፌሶን 2፥2)፤ “የዚህ ዓለም አምላክ” (2ቆሮንቶስ 4፥4) ብሎ ጠርቶታል። ዮሐንስም “መላው ዓለምም በክፉው ሥር” እንደ ሆነ ጽፏል። ግልጽ ለማድረግ፥ ዲያብሎስ ከእግዚአብሔር ጋራ እኩል አይደለም። ሁሉን የሚችል ኀያል አይደለም፤ ከኢየሱስ ጋራ ፈጽሞ አይወዳደርም። በሰይጣን ላይ የመጨረሻ ፍርድና ወሳኝ ድል ይኾናል። “ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ ባሕር” ተጥሏል “ለዘላለም ይሠቃያል” (ራእይ 20፥10)። የትኛውም ዐይነት መንግሥት እና/ወይም ሥልጣን ሁሉ ከሰይጣን ይወሰዳሉ። ትክክለኛው ባለቤታቸው ለኾነውና ለሚገባው ለንጉሡ ኢየሱስ ተላልፈው

1 ኤክሌሲያ ዩኒቨርሳሊስ የሚለው የላቲን ቃል በመላው ዓለም ያለችውን ቤተ ክርስቲያን ያመለክታል።

4 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

ይሰጣሉ። እስከዚያው ድረስ ሰዎች ወይ በቤተ ክርስታያን ውስጥ ወይም በዓለም ኾነው ይኖራሉ። ዓለም በሰይጣን ተጽዕኖ (ቍጥጥር) ሥር ነው።በአንጻሩ ደግሞ ቤተ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ተጽዕኖ (ቍጥጥር) ሥር ነች። የቤተ ክርስቲያን ተከላንና አስፈላጊነትን ለመረዳት ይህ ቍልፍ ነው። በኤፌሶን 2፥12-22 እና ኤፌሶን 3፥10-21 ያሉትን ሁለት ክፍላተ ምንባብ ማሰቡ ጠቃሚ ነው። እነዚህ ምንባባት “ለምን ተጨማሪ አብያተ ክርስቲያናት ያስፈልጉናል?” ለሚለው ጥያቄ ሁለት መልሶችን ይሰጡናል። የመጀመሪያው እና በጣም ግለጽ የሆነው እግዚአብሔር የሚሠራው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ (በሕዝቡ መካከል) ነው። በሌላ አነጋገር ይህ ማለት ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ድነት፣ የመንፈስ ቅዱስ የሚያበረታ ሀልዎት፣ እና የመንግሥቱ ሕይወት ትክክለኛ መገለጫና ምስክር “መገኛ” (ቦታ፣ ዐውድ) ናት ማለት ነው። የርሱ ፍላጐት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ዐዲሱን ሰው መፍጠር ነው። ሁለተኛው፥ እነዚህ ምንባባት እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያን በኩል (በሕዝቡ በኩል) አንደሚሠራ ያሳያሉ። ይህን እውነት በሌላ መንገድ ለመግለጽ፣ ቤተ ክርስቲያን የመንግሥቱን ዐላማ በዓለም ላይ ለማስፋት ዝግጁና ፈቃደኛ የኾነች የእግዚአብሔር “ወኪል” ነች ማለት ይቻላል። በቤተ ክርስቲያን በኩል እግዚአብሔር ዓለምን ከራሱ ጋራ ያስታርቃል። 2 መጽሐፍ ቅዱሳዊው እውነት፥ በጠላት ጥቃት፣ ባርነት፣ ክፍፍል፣ እና መቅበዝዝ ሥር ለወደቁ ሁሉ ብቸኛ ተስፋ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ናት። ምንም እንኳ የርሱ አስሚታ በሁሉ ቦታ ቢሆንም ቤተ ክርስቲያን ግን የእግዚአብሔር መገኛ እና ወኪል በመኾን በዚህ ጨለማ ዓለም ውስጥ ሰዎች ነጻነትን የሚጐናጸፉበትን ዕድል ታመቻቻለች። እግዚአብሔር ይመስገን “የዲያብሎስን ሥራ ሊያፈርስ” ኢየሱስ መጣ (1 ዮሐንስ 3፥8)።

2 ቤተ ክርስቲያን “መገኛ ስፍራ” እና “ወኪል” መኾኗን ለመረዳት “Theology of the Church for Team Leaders” in The Timothy Conference Workbook , Wichita: TUMI Press, 2005, pp. 39-46. ይመልከቱ

መግቢያ • 5

የጳውሎስ ምሳሌዎች ከሐዋርያት ሥራ፥ ጳውሎሳዊ ዑደት 3 ወርልድ ኢምፓክት ሚሲዮናዊ ተቋም እንደመኾኑ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ተግባሮቻችን በጳውሎስና በርሱ ሚስዮናዊ ቡድን አማካይነት በሐዋርያት ሥራ ውስጥ ቤተ ክርስቲያናት በተተከሉበት መንገድ ላይ የተመሠረተ ነው። ቀጥሎ የቀረበው ንድፍ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ስልቶችን ለመቃኘት በጣም ጠቃሚ ነው። 1. ሚስዮናውያን ይሾማሉ፡- ሐዋርያት ሥራ 13፥1-4፣ 15፥39-40፤ ገላትያ 1፥15-16። 2. ወደ ሰዎች ይሄዳሉ፡- ሐዋርያት ሥራ 13፥14-16፣ 14፥1፣ 16፥13-15፣ 17፥16-19። 3. ወንጌል ይሰበካል፡- ሐዋርያት ሥራ 13፥17-41፣ 16፥31፤ ሮሜ 10፥9 14፤ 2 ጢሞቴዎስ 2፥8። 4. ሰሚዎች ይለወጣሉ፡- ሐዋርያት ሥራ 13፥48፣ 16፥14-15፣ 20፥21፣ 26፥20፤ 1 ተሰሎንቄ 1፥9-10። 5. አማኞች ይሰባሰባሉ፡- ሐዋርያት ሥራ 13፥43፣ 19፥9፤ ሮሜ 16፥4-5፤ 1 ቆሮንቶስ 14፥26። 6. በእምነት መጽናት፡- ሐዋርያት ሥራ 14፥21-22፣ 15፥41፤ ሮሜ 16፥17፤ ቆላስይስ 1፥28፤ 2 ተሰሎንቄ 2፥15፤ 1 ጢሞቴዎስ 1:3። 7. መሪዎች ይሾማሉ፡- ሐዋርያት ሥራ 14፥23፣ 2 ጢሞቴዎስ 2፥2፣ ቲቶ 1፥5 8. አማኞች ይበረታታሉ፡- ሐዋርያት ሥራ 14፥23፣ 16፥40፣ 21፥32 (2 ጢሞቴዎስ 4፥9 እና ቲቶ 3፥12) 3 “ጳውሎሳዊ ዑደት” የሚለው ቃል መግለጫ ምስሉ የተወሰዱት David J. Hesselgrave, Planting Churches Cross-Culturally , 2nd ed. Grand Rapids: Baker Book House, 2000. “መስበክ፣ ማስታተቅና ማብቃት” እንዲሁም “ተከላ” የሚሉት ቤተ ክርስቲያን ተከላ መርሐ ግብሮች የተወሰዱት ከ Crowns of Beauty: Planting Urban Churches Conference Binder , Los Angeles: World Impact Press, 1999 and Ripe for Harvest: A Guidebook for Planting Healthy Churches in the City , Wichita: TUMI Press, 2016, p. 61 ነው።

6 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

9. ግንኙነቱ ይቀጥላል፡- ሐዋርያት ሥራ 15፥36፣ 18፥23፤ 1 ቆሮንቶስ 16፥5፤ ኤፌሶን 6፥21-22፤ ቆላስይስ 4፥7-8። 10. አብያተ ክርስቲያናት ተሰብስበው ይልካሉ፡- ሐዋርያት ሥራ 14፥26-27፣ 15፥1-4።

1

- እ ያ ን

ተ ል

ዮ ና

ሚ ስ

እ ኮ

ው ነ

ጣ ቸ

4 6 ታ ዎ

ተ ሰ

2

ከ አ

10

5 ,

1

3 9 ,

- 4 ;

1 3 . 1

ድ ማ

ቲ ያ ና ሐ ዋ

ጮ ች

ሥ ራ

ተ ፈ

ክ ር ስ ል -

ጠ ረ

ጋ ር

- 4

አ ዘ

ያ ተ

1 3 .

ጋጅ

1 5 . 1

- ሐ

ግ ን

1 4 1 6 ,

አ ብ

2 7 ;

በ ዋ

ዋ ሥ

ኙ ነ ት

ብ ስ

2 6 ,

ላ ኪ

1 4 . 1

ተ ሰ

1 4 .

ዎ ች

ተ ሰ

9

3

ሥ ራ

1 3 .

መንፈስ ቅዱስ የሚሲዮናያዊ ድርጅት መለኮታዊ አመራር ሐዋ ሥራ 13.2,52

2 3

ነ ቶ ች

በ ከ

ወ ን ጌ

1 8 .

1 7 ff

ሐ ዋ

- ሐ

ግ ን ኙ

3 6 ,

; , 1

ቀ ጠ ሉ -

ዋ ሥ ራ

ል ፍ

1 5 .

6 , 3 1

አ ስ

ተ ላ

ም ር

አ ስ

አ ስ ታ

ጸሎት መንፈሱ ሐዋ ሥራ 13.1-4 የቅዱሳት መጻሕፍት መሠረቶች ሐዋ ሥራ 15.15 ቤተክርስቲያን ወኪሉ ሐዋ ሥራ 15.22

ሐ ዋ

አ ማ

ሥ ራ

ኞ ች

ወ ጡ ሐ ዋ

, 1 5

አ መ

1 4 . 2

ተ ለ

ሥ ራ 1 3 4

6 . 1 4

8

ሰ ገ ኑ ;

3 ; 1

ዎ ች

4

8 ; 1

6 . 4

ሰ ሚ

0

ስ ብ

አ መ

ሥ ራ

ሰ ብ

ራ ር ሥ ራ

ኞ ች ል -

ሐ ዋ

ሐ ዋ

ተ ቀ

አ ማ

ግ ብ

ድ ሷ

4 3

በ ዋ

1 4 2

1 3 .

ብ ስ

ተ ሰ

3

5

7

እ ም

ነ ት

ግ ጧ

ረ ጋ

6

ከዚህ ንድፍ በመነሣት ወርልድ ኢምፓክት ዐዳዲስ ማኅበረ ሰቦችን በወንጌል ለመድረስ፣ ደቀ መዛሙርት ለማድረግ፣ እና በጊዜ ኺደት አገልግሎቶችን ለአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለማስረከብ በምናደርገው ጥረት ሦስት ደርዝ ያለው የወንጌል ሥርጭት፣ የማስታጠቅና የማብቃት ሚስዮናዊ አቀራረብን አዳብሯል። የተከላ ስልት የተወለደውም ከዚህ አቀራረብ በመነሣት ሲኾን የኢቫንጌል የከተማ አብያተ ክርስቲያን ተከላ ትምህርት ቤትና ሥልጠና ሰነዶችም የዚህ ውጤት ናቸው።

መግቢያ • 7

የቤተ ክርስቲያን ተከላ አጠቃላይ ዳሰሰ 4 ቤተ ክርስቲያን እንዴት ይተከላል?

ወንጌል መስበክ መርሕ፥ ሰዎች ማኅበረሰቡን እንዲቀላቀሉ መጋበዝ መጀመር • ተጨማሪ በጐ ፈቃደኞችን መመልመልና ማሠልጠን • የስብከተ ወንጌል ኹነቶችን ማካኼድ ዝግጅት፥ ቤተ ክርስቲያን መኾን መርሕ፥ ቤተ ክርስቲያን የምትወለደው አስቀድሞ ከተተከለ ቤተ ክርስቲያን ነው። • ጸሎት። • የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድን ማደራጀት። • ቤተ ክርስቲያን የሚተከልበትን ቦታ እና ማኅበረ ሰብ መምረጥ። • የሥነ ሕዝብና የባህል ጥናቶች ማካኼድ። መጀመር፥ ቤተ ክርስቲያንን ማስፋፋት መሰባሰብ፥ ቤተ ክርስቲያንን መትከል መርሕ፥ ቤተ ክርስቲያኒቱ በማኅበረ ሰቡ ውስጥ ልትታወቅ ወደምትችልበት ደረጃ ማምጣት • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድኖችን፣ ቤት ኅብረቶችን ማደራጀት • ዐዳዲስ አማኞችን መከታተል • ዕጩ መሪዎችን መለየትና ማሠልጠን • ዐዲሷን ቤተ ክርስቲያን ለአካባቢው ማሳወቅ እድገት፥ ቤተ ክርስቲያንን ማሳደግ መርሕ፥ በእረኛ አመራር ሥር መሪዎችን ማሳደግ ስጦታዎቻቸውን እንዲለማመዱ መርዳት • የቡድንና የግል ደቀ መዝሙርነትን ማሳደግ • የጸጋ ስጦታዎችን በመለየትና በማሳደግ በቤተ ክርስቲያን ቍልፍ ቦታዎች መጠቀም ሸግግር፥ ቤተ ክርስቲያንን ማብዛት መርሕ፥ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ተግባርን የሚረከቡ ወይም ሌላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚተክል ቡድን የሚልኩ መሪዎችን ማሳደግ። • የመብዛት ስልት መቀየስ • ለኅብረት፥ ድጋፍና ተልእኮ ከሌሎች የከተማ አብያተ ክርስቲያናት ጋራ ግንኙነት መፍጠር ማስታጠቅ ማጠናከር

4 ከRev. Dr. Don L. Davis in Ripe for Harvest , pp. 54-60 የተወሰደ

8 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

የቤተ ክርስቲያን ተከላ ዐሥር መርሖች 5 1. ኢየሱስ ጌታ ነው። (ማቴዎስ 9፥37-38) ሁሉም የቤተ ክርስቲያን ተከላ እንቅስቃሴዎች ውጤታማና ፍሬያማ የሚኾኑት የመኸሩ ጌታ በኾነው በጌታ በኢየሱስ ጥበቃና ኀይል ነው። 2. ስብከተ ወንጌል፣ በወንጌል ያልተደረሱ ሰዎች ሌሎች ሰዎችን ይደርሱ ዘንድ ማስታጠቅና ማበረታታት። (1ተሰሎንቄ 1፥6-8) ሌሎችን ለክርስቶስ የመድረስ ግባችን ለጠንካራ ለውጥ ብቻ ሳይኾን በቀጣይ ይበዙም ዘንድ ነው። በወንጌል የተለወጡ ሰዎች ለሌሎችን በወንጌል ለመድረስ መሠልጠን አለባቸው። 3. አካታች መሆን፥ ማንም ሊመጣ ይችላል። (ሮሜ 10፥12) የትኛውም ስልት ማንም ሰው ወይም ቡድን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንዳይገባ መከልከል የለበትም። 4. ከ ባህል ገለልተኛ መሆን፥ የሆናችሁትን ሆናችሁ ኑ። (ቈላስይስ 3፥11) ወደ ኢየሱስ የሚመጡ ሰዎች ባህላቸውን እንዲቀይሩ ወንጌሉ ቅድመ ኹኔታ አያስቀምጥም። እንደሆኑት ሆነው መምጣት ይችላሉ። 5. የምሽግ አስተሳሰብን ማስወገድ። (ሐዋርያት ሥራ 1፥8) የወንጌል ተልእኮ ዐላማ ባልዳኑ ሰዎች መካከል የማይደፈር ግንብ መገንባት አይደለም። ይልቁንም በዓለም ድንበሮች ሁሉ የኢየሱስ ምስክር የሚሆኑ ደጆችን መክፈት ነው። 6. መቀዛቀዝ እንዳይኖር ስብከተ ወንጌልን መቀጠል። (ሮሜ 1፥16 17) የታላቁን ተልእኮ ራእይ በአእምሯችን ይዘን አድማሱን መመልከት። ለክርስቶስ ደፋር ምስክር የሆነ ከባቢን መፍጠር። 7. የዘር፣ የመደብ፣ የጾታ እና የቋንቋ ድንበሮችን መጣስ። (1 ቀሮንቶስ 9፥19-22) ከቤተ ክርስቲያን በእጅጉ ርቀው ላሉ ሰዎች የመንግሥቱን መልእክት ለማስተላለፍ ዐዳዲስና ተቀባይነት ያላቸውን መንገዶች ለመጠቀም በክርስቶስ ያላችሁን ነጻነት መጠቀም።

5 Mere Missions , Wichita: TUMI Press, 2022. pp 234-236.

መግቢያ • 9

8. በማኅበረ ሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን ባህሎች ማክበር። (ሐዋርያት ሥራ 15፥23-29) ኢየሱስን ጌታቸውና መዽኀኒታቸው አድርገው በተቀበሉ ሰዎች ቋንቋዎች፣ ልማዶች፣ ዘይቤዎችና ተመክሮዎች ውስጥ ዐልፎ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ራእይና ባሕርይ እንዲገልጥ መፍቀድ። 9. ጥገኛነትን ማስወገድ። (ኤፌሶን 4፥11-16) በጣም አነስተኛ በኾነውና እያደገ ባለው የክርስቲያን ማኅበረ ሰብ ውስጥ እንኳ መንፈስ ቅዱስ የእግዚብሔርን ሥራ ከግብ ለማድረስ ያለውን ኀይል አቅልላችሁ አትመልከቱ። 10. ዳግም ተከላ ማሰብ። (2ጢሞቴዎስ 2፥2፤ ፊልጵስዩስ 1፥18) በምትጀምሯቸው እንቅስቃሴዎችና ውጥኖች ሁሉ የወንጌል ተልእኮን ክፍት በሆነ አእምሮ ሌሎች እንዲቀጥሉት ማስታጠቅን ዐስቡ።

10 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

የቤተ ክርስቲያን ተከላ ደረጃዎች አጠቃላይ ምልከታ 6 ሬቨረንድ ዶ/ር ዶን ኤል. ዳቪስ

ዝግጅት

ማስጀመር

በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ቤተ ክርስቲያን ለመትከል ራሳቸውን ያዘጋጁ የተጠሩ አባላት ቡድን ማቋቋም

ወደ ተመረጠው ማኅበረ ሰብ ዘልቆ ለመግባት የስብከተ ወንጌል ኹነቶችን ማካኼድ

ብያኔ

ቀጣይነት ያለው የስብከተ ወንጌልና ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማድረግ የሚያስችል በጐ ፈቃደኞችን መመልመልና ማደራጀት።

የታለመውን ማኅበረ ሰብ፣ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድናችሁን ምሥረታችሁን፣ ለማኅበረ ሰቡ የሚማልዱ ማላጆችን እንዲሁም ያሉ መልካም አጋጣሚዎችንና ዕድሎችን

ዐላማ

የሚያጠኑ ሰዎችን በተመለከተ የእግዚአብሔርን ፊት ፈልጉ

የእናት-ልጅ አገላለጽ

ውሳኔና ጽንስ

ቅድመ ወሊድ ክብካቤ

እነዚህን የተመለከቱ ጥያቄዎች • የስብከተ ወንጌል ኹነቶች ብዛትና ባሕርያቸው • ኹነቶቹን ማስተዋወቅና ግንኙነቶች • በጐ ፈቃደኞችን መመልመልና ማደራጀት • የስብከተ ወንጌሉ ማንነትና ስም

እነዚህን የተመለከቱ ጥያቄዎች • ቡድናችሁን ማደራጀት • የታለመውን ማኅበረ ሰብ • የስልታዊ ጸሎት ተነሣሽነቶች • የሥነ ሕዝብ ጥናቶች

በውይይት ወቅት የጥያቄ ትኲረት

ለጌታ ክፍት መኾን

ማኅበረ ሰቡን የማሳተፍ ድፍረት

ዐቢይ ባሕርይ

ወሳኝ ኾኑ ተግዳሮቶች

ቅድመ ዕሳቤ እና “የትንታኔ ሽባ”

ማስፈራራትና ትዕቢት

የማድመጥና የማሰላሰል ጊዜን ማዳበር

ተሳትፏችሁን በድፍረትና በራስ መተማመን መጀመር

መሠረታዊ ጕዳይ

6

Mere Missions , pp. 248-249

መግቢያ • 11

መሰባሰብ

ማሳደግ

ሽግግር

መሪዎች ራሳቸውን ችለው እንዲያስተዳድሩ ማስታጠቅ፤ ሥልጣንን ማስተላለፍ፤ የገንዘብ ነጻነት መዋቅርን በመዘርጋት ከጥገኛነት ማላቀቅ።

አባላትንና ደቀመዝሙር መሪዎችን ማሳደግ፤ አባላት በጸጋ ስጦታዎቻቸው እንዲያገለግሉ ማብቃት፤ በክርስቲያን ጉባኤው ውስጥ ጠንካራ የኾነ አወቃቀር ማደራጀት አባላት ባላቸው ሸክምና ስጦታ በመመሥረት የግልና የቡድን ደቀ መዝሙርትን ማፍራት

ዐዳዲስ አማኞችን በማሰባሰብ የአማኞች አጥቢያ ጉባኤ መመሥረት፤ ዐዲሷን ቤተ ክርስቲያን ለማኅበረ ሰቡ ማስተዋወቅ የቤት ኅብረቶችን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን፣ በመመሥረት የወንጌል ሥርጭቱን በመቀጠል ቤተ ክርስቲያን በማኅበረ ሰቡ ውስጥ በግልጽ እያደገች እንድትመጣ ማድረግ እነዚህን የተመለከቱ ጥያቄዎች • የዐዳዲስ አባላት ክትትል • የአነስተኛ ቡድን ሕይወት መፍጥር • የጋራ አምልኮ መገለጫዎች • የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን መዋቅሮችና ኺደቶች • የመጀመሪያ ሕያው አካልና ዕድገት • ቤተ ክርስቲያን ከባህል ጋራ ያላት ግንኙነት የእግዚአብሔርን ጊዜ ለይቶ የማወቅ ጥበብ ልጅ መውለድ

አባላትና ሽማግሌዎችን ኀላፊነት መስጠት፣ እረኞችን መሾም እና ማሳደግ

ዕድገትና ወላጅነት

ወደ ጉልምስና ማሳደግ

እነዚህን የተመለከቱ ጥያቄዎች • ትብብር • ግንኙነቶችና ኅብረቶች • አመራርን ማስተላለፍ • ሚስዮናዊ ሽግግር • ቀጣይነት ያለው መብዛት

እነዚህ የተመለከቱ ጥያቄዎች • ግለሰቦችንና መሪዎችን ደቀ መዛሙርት ማድረግ • አባላት ስጦታዎቻቸውንና ሸክሞቻቸውን ለይተው እንዲያውቁ መርዳት • የመሪነት መመዘኛዎች • የቤተ ክርስቲያን ሥርዐት፣ አስተዳደር እና ተግሣጽ

በእምነት ነጥቦች ላይ ማተኰር

በመንፈስ ቅዱስ ችሎታ ላይ መደገፍ አባታዊ አስተዳደርና ፈጥኖ መልቀቅ በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ቀጣይነት ላይ በመተማመን ዱላውን ማቀበል

ትዕግሥት ማጣትና ፍርሀት

ቸልተኛነትና ጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ማተኮር በአማኞች ላይ ትኵረት አድርጐ መሥራት

ቤተ ክርስቲያኒቱን ማስተዋወቅን በደስታ ማክበር

ተከላ

ክፍል 1፥ ዝግጅት በዚህ ክፍል ውስጥ የኢቫንጄል መርሖችን ለቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድናችሁ ጥረት፣ ውጤታማ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድንን የመገንባትና ለቤተ ክርስቲያን ተከላ ዐቅምን ማጐልበት አስፈላጊነትን እንወያያለን።

ትምህርት 1 ትምህርታችሁን መቅረጽ ትምህርት 2 ቡድናችሁን ማዋቀር ትምህርት 3 ዐቅም ማጐልበት

13

ክፍል 1፥ ዝግጅት • 15

ትምህርት 1 ትምህርታችሁን መቅረጽ ሬቨረንድ ሬድ ስሚዝ

ቡድናችሁ የኢቫንጄል ትምህርት ቤትን የተከላ መርሖች ቤተ ክርስቲያናችሁ በምታገለግለው ማኅበረ ሰብ ዐውድ መነጽር ማጣራቱ አስፈላጊ ነው።

I. ዐውዳችሁን ለይታችሁ ዕወቁ እያንዳንዱ ጌታ የሚጠራው ቡድን ለቤተ ክርስቲያኑ ልዩ ራእይ ይኖረዋል፤ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድን ጥረትኖ በተለያዩ መንገዶች ይቀርባል። ቤተ ክርስቲያን የምትተክሉት በራሳችሁ ዐውድ ወይም ባህል ዘለል ቢኾን በኢቫንጌል በቀረቡት መርሖች መሠረት የራሳችሁን ልዩ ጉዞ የሚያሳይ ንድፍ ሊኖራችሁ ይገባል። ሴሚናሮች፣ ጥያቄዎችና የቡድን ልምምዶች ቡድናችሁ ከእናንተ ቤተ ክርስቲያን ተከላ ዐውድ ጋራ ተዛማጅነት ያላቸውን ጉዳዮች እንድታጤኑ ይገፏፏችኋል። በእያንዳንዱ ቡድን መልመጃዎች ውስጥ የተካተቱትን ጥያቄዎች በመጠቀም ቤተ ክርስቲያን የምትተክሉበትን ማኅበረ ሰብ በሚመለከቱ ጕዳዮች ላይ ዐሳባችሁን ግለጹ። II. ራእያችሁን ለይታችሁ ወስኑ በጥረታችሁ ውጤታማ ለመሆን ቤተ ክርስቲያን ተካዮች ግልጽ የሆነ ነገረ መለኮታዊ ራእይ መቀበልና ጤናማ የሆነና ባህላዊ ኹኔታዎችን ያገናዘቡ የቤተ ክርስቲያን መገለጫዎችን መምረጥ አለባቸው። ሰዎች ለክርስቶስ ፍቅር ምላሽ እንዲሰጡና በሚኖሩበት በሚሠሩበት ቦታ ሁሉ የክርስቶስን መንግሥት በመወከል ውጤታማ በሆነ መንገድ መስበክ ይችሉ ዘንድ ለማስታጠቅና ለማበረታታት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥበብን መተግበር አለባችሁ። 1

1

Ripe for Harvest , p. 11.

16 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

ትልቅም ይሁን ትንሽ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ውስጥ የቤተ ክርስታየን ተከላ ቡድናችሁ የጋራ የሆነ ራእይን በተመለከተ ግልጽ የሆነ ግንዛቤና የጋራ አስተዋጽዖ ሊኖረው ይገባል። 2 ግልጽ የሆነ ራእይ “ማድረግ እንችላለን” በማለትና “ማድረግ አለብን” በማለት መካከል ያለውን ልዩነት በግልጽ በመረዳት ውሳኔዎቻችሁ በስሜት፣ በወጪዎች፣ ወይም ባሏችሁ ሀብቶች ላይ የተመሠረቱ እንዳይሆኑ ያስችላችኋል። • በግልጽ በራእያችሁ ላይ አተኩሩ • ለራእዩ አስተዋጽዖ ባላቸው ነገሮች ላይ ብቻ ተጠመዱ • ሊሠሩ የሚችሉ ብዙ መልካም ነገሮች ቢኖሩም ለራእያችሁ አስተዋጽዖ የሚያበረክቱት ጥቂት ናቸው። • ደካማ ባላደራነት በራእይ ሳይሆን በመልካም አጋጣሚዎች እንድንመራ ይዳርገናል። • በጣም ቀላሉን መንገድ ብቻ መምረጥ ሳይሆን የእያንዳንዱን ውሳኔ አንድምታ በጥንቃቄ አጢኑ።

• ስሜታችሁ በቀላሉ ሊያታልላችሁ ስለሚችል “ንቁ አእምሮ ይኑራችሁ፤ ራሳችሁንም የምትገዙ ሁኑ” (1ጴጥሮስ 4፥7)። • ራስን መግዛት የሌለበት ጐዳና ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍላል። 3

III.ዋና ዕሴቶቻችሁ ምን እንደሆኑ ወስኑ የሁሉም የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድኖች ታላቅ ተግዳሮት ሥራቸውን የሚመሯቸውን ዕሴቶች መወሰን ነው። ሌሎች ዕሴቶች ጠቃሚ ቢሆኑም እንኳ የትኛዋም ቤተ ክርስቲያን እያንዳንዱ የቡድኑ አባል የሚያመጣውን ዕሴት ሁሉ ምርጥ አድርጋ መሸከም አትችልም። የእናንተ ቡድን ከራእያችሁ ጋራ የሚገጥሙ የጋራ ዕሴቶቻችሁ ምን እንደሆኑ መወሰን አለበት። የትኛዋም ቤተ ክርስቲያን ዐሥር ነገሮችን

2 3

Ripe for Harvest , p. 44 Ripe for Harvest, p. 67.

ክፍል 1፥ ዝግጅት • 17

ጥንቅቅ አድርጋ መሥራት አትችልም። በሁሉም የቤተ ክርስቲያን ተከላ ጥረቶች ውስጥ ግልጽነት ገዥ ነው። ዕሴቶቻችሁን ስትወስኑ ንጽጽሮችን ማስወገድ አለባችሁ። በአንድ ወቅት ቴዎዶር ሩዝቬልት “ማነጻጸር የደስታ ሌባ” ብለው የተናገሩት ነገር በበርካታ የሕይወት ገጽታዎች ውስጥ ሁሉ ተግባራዊ ሆኖ የሚታይ ሲሆን በተለይ ደግሞ በአገልግሎት ውስጥ በተለይም በቤተ ክርስቲያን ተከላ ዐውድ ውስጥ በጉልህ ይታያል። ቡድናችሁ፥ ለእያንዳንዱ የቡድኑ አባላት ጠቃሚ የሆኑ የተለያዩ ዕሴቶችን አሰባስቦ የጋራ የሆኑ ዕሴቶችን በመቅረጽ ኺደት በርካታ የዐሳብ ፍጭቶችን ማድረግ ያስፈልግ ይሆናል። በቡድናችሁ ውስጥ ያሉ አባላት ሁሉ ምልከታቸው የተቃኘበት የየራሳቸው ታሪክ ስላላቸው መጀመሪያ ላይ ይህን ማድረጉ አስቸጋሪ ሊመስል ይችላል። በዚህ ጉዞ ውስጥ ጥሩ ጥያቄዎችን መጠየቁ ጠቃሚ ይሆናል። በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ሁላችንም ወደ ቤተ ክርስቲያን ተከላ የምንመጣው በተመክሮዎቻችን ለመሆኑ አንዱ ማሳያ “ቀድሞ በነበርሁበት ቤተ ክርስቲያን ይህን ወይም ያን አድርገናል” ወይም “ነገሮችን የምናደርገው በዚህ ወይም በዚያ መንገድ ነው” የሚሉና የመሳሰሉት መግለጫዎቻችን ናቸው። የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድናችሁ በሁሉም አቅጣጫ የጋራ ዕሴቶችን በመያዝ ንጽጽሮችን ማስወገድ ያስፈልጋል።

18 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

ትምህርት 2 ቡድን ማዋቀር 1 ሬቨረንድ ሉክ ራፍሊ

ብዙውን ጊዜ ስኬት በቡድን መሥራትንም ያካትታል። “ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” የሚለው አባባል ጠንካራ የሆነ የቡድን ሥራን ጠቃሚነት አጉልቶ የሚያሳይ ነው። በቡድን ስለመሥራት ጠቀሜታና አስፈላጊነት ብዙ ተጽፏል። እያንዳንዳችን በተለያዩ ዐውዶች ውስጥ ያሉ የተለያዩ ቡድኖችን መጠቆም እንችላለን (ለምሳሌ፥ ስፖርት፣ ንግድ፣ ውትድርና፣ ጥናትና ምርምር፣ ትምህርት፣ ወዘተርፈ)። ከእነዚህ ቡድኖች ውስጥ አንዳንዶቹ በብቃት ዪሠሩና ጥሩ ውጤቶችን የሚፈጥሩ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ በትግልና ምንም ማስተካከያ ባለማድረግ አባሎቻቸውን ለተስፋ መቍረጥና ለብስጭት ይዳርጋሉ። ይህ እውነታ ለቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድኖችም ቢሆን ተመሳሳይ ነው። በተመክሮዎች ብቻ ሳይሆን በቡድን እንድንሠራ የታቀድንና ለዚህ የተፈጠርን መሆናችንን የሚጠቁሙ በርካታ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሖች አሉ። እስቲ ለውጤታማ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድኖች መርሖችን የሚሰጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እንመልከት። I. ግልጽነት እንደ ዋሽንትና እንደ በገና ያሉ ሕይወት የሌላቸው ነገሮች እንኳ የድምፃቸው ቃና ልዩነት ከሌለው ዜማቸውን እንዴት ማወቅ ይቻላል? ደግሞም መለከት ትክክል ያልሆነ የጥሪ ድምፅ ካሰማ፣ ለጦርነት ማን ይዘጋጃል? (1ቆሮንቶስ 14፥7-8) የጋራ ግልጽ ጥሪ አስፈላጊ መሆኑን ለመግለጽ ጳውሎስ የሙዚቃ መሣሪያዎችን በምሳሌነት ይጠቀማል። አነስተኛ የሙዚቃ ባንድም ይሁን ትልቁ ኦርኬስትራ ግልጽ የሆኑና የተስማሙባቸውን ሙዚቃዎች ይጫወታሉ። ያ ካልሆነ አስከፊ ውጤት መከተሉ አይቀርም። ቆንጆ ሙዚቃ ወዲያውኑ ማንንም ወደ የማያስደስት ጫጫታ ሊለወጥ ይችላል። ግልጽ ትእዛዝ ከሌለ ጠንካራ ወታደራዊ ኀይል ግራ ሊጋባ፣ ሊያፈገፍግ ብሎም ሊሸነፍ ይችላል። ውጤታማ ቡድኖች ስለሚሠሩት፣

1 በተጨማሪ ስኬታማ ቡድንን ስለመገንባት ለማንበብ Ripe for Harvest, pp. 169-180 ይመልከቱ።

ክፍል 1፥ ዝግጅት • 19

ስለሚማሩት፣ ወይም ስለሚጫወቱት ነገር ግልጽ ራእይ አላቸው። ግልጽ ዐላማና ራእይ ከሌለ ሰዎች የትኛው ጥረታቸው አስቸጋሪና አዳጋች ይሆናል። II. የባለቤትነት ስሜት አካል የተሠራው ከብዙ ብልቶች እንጂ ከአንድ ብልት አይደለም። እግር፣ “እኔ እጅ ስላልሆንሁ የአካል ክፍል አይደለሁም” ቢል ይህን በማለቱ የአካል ክፍል መሆኑ ይቀራልን? ጆሮም፣ “እኔ ዐይን ስላልሆንሁ የአካል ክፍል አይደለሁም” ቢል ይህን በማለቱ የአካል ክፍል መሆኑ ይቀራልን? አካል በሙሉ ዐይን ቢሆን ኖሮ፣ መስማት ከየት ይገኝ ነበር? አካል በሙሉ ጆሮ ቢሆን ኖሮ፣ ማሽተት ከየት ይገኝ ነበር? ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ወደደ እያንዳንዱን በየቦታው መድቧል። ሁሉም አንድ ብልት ቢሆን ኖሮ አካል ከየት ይገኝ ነበር? እንግዲህ ብልቶች ብዙ ናቸው፣ አካል ግን አንድ ነው (1 ቆሮንቶስ 12፥14-17)። ይናገራል። አስቂኝ በሚመስል መልኩ እግርና እጅ የአካሉ ክፍል እንዳልሆኑ ይናገራሉ። በተመሳሳይ መልኩ የቤተ ክርስቲያን አባላት ወይም የቡድናችሁ አባላት፣ “የዚህ ቡድን አባል አይደለሁም” ሊሉ ይችላሉ። ብዙውን ጊዜ አንዳንድ የቡድናችሁ አባላት የሚሰማቸው ልክ እንዲህ ነው። ባለማወቅም ይሁን የቡድናችሁ አባላት በቡድኑ ውስጥ የባለቤትነት ስሜት የማይሰማቸው ከሆነ መለያየት ሊከሠት ይችላል። III.ለተለያዩ ስጦታዎች ዋጋ መስጠት 1ቆሮንቶስ 12፥11-27፤ ኤፌሶን 4፥11-16፤ 1ጴጥሮስ 4፥9-11፤ እና ሮሜ 12፥3-8 እነዚህ ጥቅሶች ሁሉ ስለ ልዩ ልዩ ስጦታዎችና እነዚህ ስጦታዎች አካሉን ለማነጽ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆኑ ይናገራሉ። በተጨማሪም ለእነዚህ ስጦታዎች ዋጋ መስጠትና እያንዳንዱ ሰው ሁሉም የቡድኑ አባላት ሊጠቀሙ በሚችሉበት መንገድ ስጦታቸውን የመጠቀማቸውን አስፈላጊነት ይናገራሉ። እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድንም የተለያዩ ተሰጥዎችና ስጦታዎች ያስፈልጉታል። ከእናንተ ስለ 1 ቆሮንቶስ 12፥11-27 እና ስለ ቡድን እንዲሁም ባሕርያት ብዙ ነገር ማለት ይቻላል። በቍጥር 14-17 ጳውሎስ ስለ ባለቤትነት ስሜት

20 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

የተለዩ የሆኑትን ስጦታዎች ዋጋ መስጠትና ልዩነቶቹን አቀናጅቶ ሁሉም ሰው በጋራ ዐላማ ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽ እንዲሠራ ማድረግ አስፈላጊ ነው። የቡድን መሪዎች የቡድናቸውን ጠባይ ለማወቅ የጸጋ ስጦታዎችን መለየት የሚያስችሉ ዘዴዎችንና እንዲሁም ተፈጥሯዊ ባሕርዮቻቸውን ለመለየት የሚያስችሉ መመዘኛዎች ተግባራዊ ማድረግ ይችላሉ። IV.መተግበርና ማስተካከያዎች ነህምያ የኢየሩሳሌምን ቅጥሮች መልሶ ለመገንባት በጣም ጠንካራ የሆነ ዕቅድ ዐወጣ (ነህምያ 4፥15-23)። ሥራው በጣም ታላቅ ቢሆንም ቡድኑ በከፍተኛ ተነሣሽነትና በትጋት ሥራውን ይሠራ ነበር። ነህምያ፥ ቡድኑና እስራኤላውያን ሥራቸው በሚሠሩ ጊዜ ተቃውሞም ገጥሟቸው ነበረ። የነህምያ ቡድን ለገጠማቸው የጥቃት ስጋት መፍትሒ ለማበጀት አቀራረባቸውን ማስተካከል ነበረባቸው። ነህምያ፥ የግንባታ ቡድኑን ደኅናነታቸው ተጠብቆ እንዲሠሩና አስፈላጊም ከኾነ ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጡ እንደገና አዋቅሮ አስተባበራቸው። ካደረገው ማስተካከያ የተነሣ በርካታ ሥራ መሠራት ቻለ ይሁን እንጂ ተግዳሮቶችም ነበሩ። ውጤታማ ቡድኖች ዕቅድ አላቸው፤ዕቅዱን ከልባቸው ይተገብራሉ፤ እንዲሁም የሚገጥሟቸውን ዐዳዲስ ችግሮች ለመጋፈጥ ዕቅዶቻቸው ላይ ማስተካከያዎች ያደርጋሉ። V. ተግባቦትና ቅንጅት ከላይ በተጠቀሱት በእያንዳንዱ የቅዱሳት መጻሕፍት መካከል ግንኙነትና ተዛማጅነት አለ። ግልጽ ስሜት ሊኖረን ይችላል ነገር ግን ይህ ሊሆን የሚችለው ራእዩ በቀላሉ ሌሎች የሚገባቸው ሲሆን ነው። የባለቤትነት ስሜት ሊኖርም የሚችለው በቃል ወይም በተግባር መቀራረብንና አንድነትን የሚፈጥር ተግባቦት ሲኖር ነው። ልክ እንዲሁ በአካል ክፍሎች ምሳሌ እንደተገለጸው ስጦታዎች የተሰጡት ተቀናጅተው አካሉን ለማነጽ ነው። ይህም የሚሆነው ጥሩ የተግባቦት መሥመር ሲኖር ነው። ነህምያ ተግዳሮቶች በገጠሙት ጊዜ አስተካክሎ ሥራው መቀጠል የቻለው በተደራጀ ቅንጅትና ጠንካራ ተግባቦት ነው።

ክፍል 1፥ ዝግጅት • 21

VI.ባለ ሥልጣንና ሐዋርያዊ በአንጾኪያ ባለችው ቤተ ክርስቲያን ነቢያትና መምህራን ነበሩ፤ እነርሱም፦ በርናባስ፣ ኔጌር የተባለው ስምዖን፣ የቀሬናው ሉክዮስ፣ የአራተኛው ክፍል ገዥ የሄሮድስ ዐብሮ አደግ የነበረው ምናሔና ሳውል ነበሩ። እነዚህም ጌታን እያመለኩና እየጾሙ ሳሉ፣ መንፈስ ቅዱስ፣ “በርናባስንና ሳውልን እኔ ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ” አለ። እነርሱም ከጾሙና ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጭነው አሰናበቷቸው (ሐዋርያት ሥራ 13፥1-3)። እነዚህ ባሕርያት ለቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድኖች ልዩ የኾኑ ባሕርያት ናቸው። የተለያዩ ቡድኖች የተለያዩ ዐላማዎችና ግቦች ላይ የሚያተኩሩ ሲኾን የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድን ግን ትኩረቱ ክርስቶስን ያማከለ ደቀ መዛሙርትን የማፍራት ሥራ ነው። በዚህ ሥራ ውስጥ የሚካፈለው ማንኛውም ሰው ሳይሆን በቤተ ክርስቲያን ሥልጣን የተሰጣቸውና የኢየሱስን ትእዛዛት ሌሎች እንዲታዘዙ ለማስተማር የተላኩ ናቸው። ስኬታማ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድኖች ወደ ሥራቸው የሚሰማሩት በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ነው። VII. ምዘና ጳውሎስ ከጥቂት ጊዜ በኋላ በርናባስን፣ “ተነሣና የጌታን ቃል ወደ ሰበክንባቸው ከተሞች ሁሉ እንሂድ፤ በዚያ ያሉ ወንድሞችም በምን ሁኔታ እንዳሉ ለማወቅ እንጐብኛቸው” አለው (ሐዋርያት ሥራ 15፥36)። ጳውሎስ የምዘናና የግምገማን አስፈላጊነት በግልጽ አሳይቷል። እያንዳንዱ ስኬታማ ቡድን ሊሠሩ ያሰቡትን ነገር ማሳካታቸውን ይገመግማሉ። ይህን ሲያደርጉም በቀጣይ ስኬታቸውን ዘላቂ ለማድረግ ይወስናሉ። ግባቸውጋ ለመድረስ ሊከተሏቸው የሚገቡ ርምጃዎችን ይወስናሉ። ልክ እንዲሁ የእናንተም ቡድን እንደ ቡድን ምን ያህል እየሠራችሁ እንደሆነ መገምገምና በቀጣይ እንዴት ውጤታማ ልትሆኑ እንደምትችሉ መመዘን ያስፈልጋችኋል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር ሰዎችን ያገናኘባቸው ልዩ ልዩ መንገዶች እንዳሉ ምሳሌዎችን መመልከት እንችላለን። ሙሴን ከአሮን፣

22 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

ዳዊትን ከዮናታን፣ ኤልያስን ከኤልሳዕ፣ ጳውሎስን ከበርናባስ፣ ሲላስና ሌሎች ጋራ። ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዐሥራ ሁለት ደቀ መዛሙርትን ጠርቶ ነበር። እነዚህ ሁሉ በራሳቸው ብቻ ከሚያመጡት ተጸዕኖ ይልቅ በጋራ ታላቅ ተጽዕኖ መፍጠር ችለዋል። የጌታ ኢየሱስን ምሥራች ማወጅ እንደሚሻ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድን ምስክርነታችን ለዓለም የሚታወቀው ርስ በርስ ባለን መዋደድና የፍቅር ተግባር ነው። የአማኞች ማኅበረ ሰብ ለመመስረት መጀመሪያ የአማኞች ማኅበረ ሰብ ምን እንደሚመስል ማሳየት አለባችሁ። ይህ ዐዲስ ቡድን የቡድን ጓደኞቻችሁን ጨምሮ ሌሎችም በነጻነት የሚመላለሱበት ቡድን ሊሆን ይችላል። ዋናው ነገር ጌታ ከሰጣችሁ ቡድን ጋራ መሥራትና ጳውሎስ በተለያዩ ጒዞዎቹ እንዳደረገው መጀመር ነው። 2 “የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድን፥ ቡድኑን እግዚአብሔር ሲመሠርተው ምን ሊያደርግ እንዳለ እንደሚያውቅ መረዳት ቀዳሚ መርሑ ነው። በቡድን በጋራ መሆን ጥሩ ሐሳብ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርም ሐሳብ ነው። አስቸጋሪ ጊዜያት ሲመጡ የቡድን መሪዎች ለቡድኑ አንድነት ይጋደላሉ፣ አንድነታቸውን ያረጋግጣሉ እንዲሁም ቡድናቸውን ይወድዳሉ። ይህ የእግዚአብሔር ሐሳብ እንደሆነ በልባቸው ያምናሉና።” 3

2 See “Paul’s Team Members: Companions, Laborers, and Fellow Workers” in The Timothy Conference Workbook , p. 129. 3 The Timothy Conference Workbook , p. 65.

ክፍል 1፥ ዝግጅት • 23

ትምህርት 3 ተግዳሮቶችን የመቋቋም ዐቅምን ማጐልበት ሬቨረንድ ጆርዳን ኪንግ

ችግሮችን የመቋቋም ችሎታ ማጐልበት መሪዎች ወይም እረኞች ይዘውት የሚወለዱት ባሕርይ ወይም ለእነርሱ ብቻ የተሰጠ ስጦታ አይደለም። ይልቍንም ችግሮችን የመቋቋም ዐቅም የሚዳብረው በተመክሮ፣ መጐዳት እንዲሁም መንፈሳዊና ስሜታዊ ፍላጐቶቻችንን እንዲያሟላልን በእግዚአብሔር ላይ በመታመን ውስጥ ነው። እያንዳንዱ መሪ ከአገልግሎቱ ጋራ ተያይዘው የሚመጡ ተግዳሮቶችን የመቋቋም እና ከዚያም የማገገም ችሎታ ማዳበር አለበት። ለአገልግሎታችሁና ለቤተ ሰባችሁ ጤናማ የሆነ ልማድ ለማዳበር “ድካም ሁላችንንም ፈሪዎች ያደርገናል” በማለት የመቋቋም ችሎታን ለማዳበርና የድካም ስሜትን ለመከላከል ቍልፍ ነው። 1 I. ተግዳሮቶችን የመቋቋም ችሎታ ያጐለበቱ መሪዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌዎች ሀ. ሙሴ በሥራ ብዛት ደክሞ ነበረ ስለዚህም ሌሎችን መወከልና በአመራሩ ውስጥ ሌሎችንም ማሳተፍ ነበረበት ለዚህም በሕይወቱ ውስጥ ከሚያምናቸው ሰዎች ድጋፍ ማግኘትና በእነርሱም መደገፍ ነበረበት። ግትርና አስቸጋሪ የነበሩ ሰዎችን የመምራት ፈተናዎች ቢገጥሙትም ርሱ ግን ጉልበትን ከሚሰጠው ከእግዚአብሔር ጋራ የጠበቀ ግንኙነት ነበረው (ዘፀአት 18፥13-23፣ 17፥8-13) ለ. ዳዊት ፍትሓዊ ባልሆነ መንገድ ለዓመታት ንጉሥ ሳኦል ያሳድደው ነበረ ይሁን እንጂ በዚህ ሁሉ ውስጥ ርሱ ግን በእግዚአብሔር ላይ በመታመን ዘልቋል። የገዛ ልጁ እንኳ ሊገድለው በሞከረ ጊዜ በጓደኞቹ ታምኖ ሕይወቱን ለእግዚአብሔር አሳልፎ ሰጠ። በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአትን በሠራ ጊዜ ስለ ተጸጸተ ፈውስን ፍለጋ ወደ እግዚአብሔር ተመለሰ (መዝሙር 18፥1-6፣ 51፥7-12፤ 2ሳሙኤል 15፥18-23)።

1 This quote is attributed to Vince Lombardi.

24 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

ሐ. ኢየሱስ ለማረፍና ለመጸለይ ዘወትር ከሕዝቡ ገለል ብሎ ለብቻው ይሆን ነበረ። ሲጾም፣ ሲጸልይ እንዲሁም ገለል ሲል የሚያሳዩ ምሳሌዎችን እንመለከታለን። የሚሰቀልበት ጊዜ ሲቃረብ ጊዜውን በጸሎት ያሳለፈ ሲሆን ደቀ መዛሙርቱ ሸክሙን እንዲካፈሉት ጠይቋቸው ነበረ። ፍሬ ለማፍራትም ከእግዚአብሔር ጋራ የማያቋርጥ ግንኙነት ሊኖረን እንደሚገባ በምሳሌ አስረድቷል (ማቴዎስ 14፥13፤ ሉቃስ 22፥39-46፤ ማቴዎስ 4፥1፤ ዮሐንስ 15፥1-4)። መ. ጳውሎስ ከሌሎች ተለይቶ ለብቻ አገልግሎቱን አገልግሎ አያውቅም፤ ሁልጊዜም ዐብረውት የሚሠሩ ባልደረቦች አሉት። በደረሱበት በርካታ መከራዎች ውስጥ ያለማቋረጥ በእግዚአብሔር ላይ የታመነ ሲሆን የሌሎችንም ድጋፍ አግኝቷል። የተሰጠውን አገልግሎት ለመፈጸም በመንፈስ ቅዱስ ጸጋና ሥራ በጥልቀት መታመን እንዳለበት ተረድቷል (2ቆሮንቶስ 1፥8-11፤ ሐዋርያት ሥራ 16፥1-5)። II. ተግዳሮቶችን የመቋቋም ችሎታን የሚያጐለብቱ ነገሮችን ማዳበር 1. ለልባችሁና ለማኅበረ ሰባችሁ ለውጥ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ታመኑ። ዘሮችን ዝሩ ነገር ግን የተዘሩትን ዘሮች እንደሚያሳድግ በእግዚአብሔር ታመኑ። በታማኝነት እናገለግላለን ነገር ግን ለሥራችን ፍሬ በእግዚአብሔር እንታመናለን (1ቆሮንቶስ 3፥5-9፤ 1 ቆሮንቶስ 2፥1-5)። 2. ሌሎችን መወከል በድጋሚ ሌሎችን መወከል። እናንተ በማስተማሩና በእረኝነቱ ተግባር ላይ ማተኮር እንድትችሉ እንዲሁም ሌሎች የመሪነቱን ሸክም እንዲጋሯችሁ ማሠልጠንና ኀላፊነት መስጠት አለባችሁ (ሐዋርያት ሥራ 6፥1-4፤ ኤፌሶን 4፥11-13)። 3. በሕይወትና በአገልግሎት ልምድ ከእናንተ ቀደም ያለ ሰው ፈልጉና በምታገለግሉ ጊዜ እናንተን ደቀ መዝሙር እንዳየደርጓችሁና እረኛ እንዲሆኗችሁ ፍቀዱላቸው። እያንዳንዱ መሪ የሚመክረውና መጋቢ የሚሆነው ሰው ያስፈልገዋል (ማቴዎስ 10፤ ቲቶ 2፥1-8፤ 2ጢሞቴዎስ 1፥1-8)። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገጥሟችሁን

ክፍል 1፥ ዝግጅት • 25

የሚረዳችሁና በቤተ ክርስቲያን ተከላ ተግባራችሁ ዐብሯችሁ የሚሆን አማካሪ ወይም እረኛ ለማግኘት ከፈለጋችሁ የኢቫንጀል መስክ አሠልጣኛችሁ ለእናንተ ፍላጐትና ዐውድ ጋራ ተስማሚ የሆነ ሰው በመፈለግ ሊያግዛችሁ ይችላል። 4. ቤተ ሰባችሁ ቅድሚያ ልትሰጡት የሚገባ የመጀመሪያ አገልግሎታችሁ ነውና ጠብቁት። ቤተ ሰቦቻችሁ እንደተተዉና እንደማትንከባከቧቸው እንዲሰማቸው ፈጽሞ አትፍቀዱ፤ እንዲሁም ለአገልግሎታችሁም ዕንቅፋት አድርጋችሁ አትመልከቷቸው። በቤተ ሰቦቻችሁ ለመደሰትና በእነርሱም ሕይወት አሻራችሁን ለማኖር ቅርብ ሁኗቸው (1 ጢሞቴዎስ 3፥2-5፣ 12፤ ምሳሌ 3፥1-8፤ ኤፌሶን 6፥4፤ ቆላስይስ 3፥18-21)። 5. በየወቅቱ ዕረፍት የማድረግ ልማድ ይኑራችሁ። ሆነ ብላችሁ ለዕረፍት፥ ለጸሎት የምትመድቡት የዕረፍ ጊዜ ይኑራችሁ፤ ከዚያም በዐዲስ ጉልበት ወደ አገልግሎታችሁ ትመለሳላችሁ። ለጥቂት ጊዜ ከሥራ በማረፍ በእግዚአብሔር ላይ በመታመን ልባችንና ሐሳባችንን ዳግም መቃኘት እንችላለን (ዘፍጥረት 2፥1-3፤ መክብብ 3፤1-8፤ ዕብራውያን 4፥6-10፤ ማርቆስ 6፥40-47)። 6. ፍሬ ማፍራት ትችሉ ዘንድ ከወይኑ ግንድ ጋራ ተጣበቁ። ለጸሎትና ለቃሉ ጊዜ መስጠትን ችላ ካልን አገልግሎታችን ከባዶ ማሰሮ እንደ መቅዳት ይሆናል። ሌሎችን የምናገለግለው እግዚአብሔር በልባችን ሞልቶ ካትረፈረፈው መሆን አለበት (መዝሙር 1፥1-4፤ ዮሐንስ 15፥1-5)። III.በግንኙነቶች መካከል ከሚገጥሙ ስብራቶችና ጉዳቶች መፈወስ 1. ሐዘናችሁን በደንብ እዘኑ፤ ሕመማችሁን ለማስታመም ከእግዚአብሔርና ከሰዎች ጋራ ጊዜ ውሰዱ። በአገልግሎት ውስጥ ሥራ ወደሚበዛበት ቀጣዩ ምዕራፍ ወዳየውኑ የመሻገር ፈተና አለ። በሚያሳዝኑ አስቸጋሪ ሁኔታዎችንና ተመክሮዎች ውስጥ ስታልፉ ለማዘን ጊዜ ይኑራችሁ (2 ቆሮንቶስ 7፥6-7፤ ኢሳይያስ 38፥14፤ ሮሜ 12፥15)።

26 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

2. ራሳችሁን ከሰዎች አታርቁ ይልቁንም በዙሪያችሁ የምታምኗቸውና ለእናንተ ግድ የሚላቸው ሰዎች ይኑሯችሁ። ጉዳት ወይም የልብ ስብራት ሲገጥመን ራሳችንን ከሰዎች ማግለል የተለመደ ነገር ነው፤ ነገር ግን ይህ ተግባር ጤናማ ወዳልሆነ ልማድና የአገልግሎት መልክ ይመራናል። ራሳችንን ከሰዎች አግልለን መኖር ሥቃያችንን የሚያባብስና ሕመማችንን ማንም እንዳያውቀው የምንንሸፋፍን እንድንሆን ያደርገናል፤ ውሸትንም እንለምዳለን (1ነገሥት 19፥9 18፤ 2ቆሮንቶስ 1፥3-11)። 3. ጥሪያችሁን በመረዳት የምታልፉበት መከራ የተለመደ የመሆኑን እውነታ ተቀበሉ። የጥሪና የዐላማ ሸክም በአገልግሎት ውስጥ የሚገጥሙንን መከራዎች እውነታነት እንድንቀበል ያስችለናል። ጥሪያችን እንደሆነ ማወቃችን ከገጠመን አሁናዊ ኹኔታ አሻግረን እንድንመለከትና በሩጫው መም ላይ ሩጫችንን ሳናቋርጥ እንድንቀጥል ይረዳናል (2ተሰሎንቄ 1፥11፤ ዕብራውያን 12፥1-3)።

ተከላ

የቡድን መልመጃዎች፡- ዝግጅት

የቡድንመልመጃ 1 ዐውድ መመሥረት የቡድን መልመጃ 2 ዕሴትና ርእይን መተለም የቡድን መልመጃ 3 የቡድን ውጤታማነት የቡድን መልመጃ 4 ተግዳሮቶችን የመቋቋም ዐቅም ማጐልበት

27

የቡድን መልመጃዎች፡- ዝግጅት • 29

መልመጃ 1 ዐውድ መመሥረት 1

ቡድናችሁ የራሱን ዐውድ፣ ዒላማ ያደረገውን ማኅበረ ሰብ እና በተመረጠው ዐውድ ውስጥ ሊገጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችን በሚገባ ማወቅ አለበት።

መመሪያዎች ቀጥሎ የቀረቡትን ጥያቄዎች ተወያዩባቸው መልሶቻችሁን አጠናቅራችሁ አስቀምጡ። መልሶቻችሁ እቅጩን ይሁኑ። 1. ዒላማ ያደረጋችኋቸው ማኅበረ ሰቦች ምንድን ናቸው? 2. ስለ እነዚህ ማኅበረ ሰቦች ምን ታውቃላችሁ (የሕዝብ መረጃ)? 3. ስለ እነዚህ ማኅበረ ሰቦች ምን ማወቅና መማር ያስፈልጋችኋል? 4. ዒላማ ያደረጋችሁት ብሔር ወይም ሕዝብ የቱን ነው? ለምን? 5. እናንተን ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት የሚለያችሁ ምንድን ነው? 6. የምትተክሉት ቤተ ክርስቲያን መገለጫ 2 ምን ይመስላል? 7. ቤተ ክርስቲያናችሁ ከየትኛው ቤተ እምነት ወይም ማኅበር ጋራ ነው ግንኙነት እና ትስስር የምትፈጥረው? ተጨማሪ ጥያቄዎች 1. የቤተ ክርስቲያን መተዳደሪያ ደንብና የእምነት መግለጫ አላችሁ? ከሌላችሁ በውስጣችሁ እንዴት ባለ መልኩ መሥራት ትችላላችሁ?

1 Adapted from an Evangel School exercise in Ripe for Harvest , pp. 79−92. 2 የተለያዩ የቤተ ክርስቲያን መገለጫዎችን ለማየት Ripe for Harvest , pp. 87–92 ይመልከቱ Ripe for Harvest , pp. 87–92.

30 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

2. ከመንግሥት ጋራ ተያያዥ የሆኑ ጉዳዮች (ከግብር ነጻ) መሆንን የመሳሰሉትን መቼ ነው የምታመለክቱት? 3 3. የቤተ ክርስቲያኒቱን የወጪና ገቢ ሒሳቦች በተገቢው መንገድ መያዛቸውን የምትቆጣጠሩት እንዴት ነው? 4 4. የ501c3 ደረጃን ትከታተላላችሁ? በውይይታችሁ መሠረት በቀጣዮቹ ከ6-12 ወራት ውስጥ ግቦቻችሁን አዳብሩና ሰነድ አዘጋጁ። ግቦቻችሁ ሊለኩ የሚችሉ መሆናቸውን ርግጠኞች ሁኑ። ግልጽ የመጨረሻ ቀናትን አስቀምጡ፤ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ግን ተጠሪ የሚሆን ሰው በኀላፊነት መድቡ። ግቦቻችሁን እስካስቀመጣችሁና ውሳኔያችሁን የምትወስኑበትን ቀን እስከቆረጣችሁ ድረስ ከኢቫንጄል ትምህርት በኋላ ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍ ትችላላችሁ።

3 See “Church and State” in Planting Churches among the City’s Poor: An Anthology of Urban Church Planting Resources, Vol. 2 , Wichita: TUMI Press, 2015, p. 358. 4 See “Church Financial Process” in Planting Churches among the City’s Poor, Vol. 2 , p. 351.

የቡድን መልመጃዎች፡- ዝግጅት • 31

መልመጃ 2 ዕሴትንና ርእይን መተለም 1

ቡድናችሁ፥ የምትተክሏት ቤተ ክርስቲያንን ዕሴቶችና ርእይ በግልጽ ማስቀመጥ አለበት።

መመሪያዎች የቡድን መልመጃችሁን ሠርታችሁ አጠናቅቁ። ዕሴቶችንና ርእይን መበየን። 1. እያንዳንዱ የቡድን አባል ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ዕሴቶች ውስጥ 7ቱን መምረጥና ደረጃ መስጠት አለበት። 2. ቡድኑ በእያንዳንዱ አባላት ዝርዝሮች ላይ በመወያየት የትኞቹ የቡድኑ ዕሴቶች መሆን እንዳለባቸው ይወስን። a. በሁሉም የቡድን አባላት የተመረጡት ዕሴቶች የትኞቹ ናቸው? b. ከቀረቡት ውጭ ተጨማሪ ዕሴቶች ለቡድናችሁ ያስፈልጋሉን? c. የቤተ ክርስቲያን ተከላችሁን የሚመሩ 5 ዋና ዕሴቶችን ለይታችሁ አስቀምጡ። 3. በዋና ዕሴቶቻችሁ መሠረት የቤተ ክርስቲያናችሁን ርእይ አንቀጽ ግለጹ a. ቤተ ክርስቲያኒቱን በ5 ዓመት ውስጥ ምን ጋ ታዩአታላችሁ? b. “ስኬት” ምን ይመስላል? c. በውስጥ እና በውጭ ቋንቋችሁ መካከል ምን ዐይነት ልዩነቶች ሊኖሩ ይገባል?

1 Adapted from an Evangel School exercise in Ripe for Harvest , pp. 95-102.

32 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

ትልቁን ሥዕል መመልከት፥ ዕሴቶችንና ርእይን በግልጽ ማስቀመጥ ቀጥሎ የቀረቡትን ከ1-7 ደረጃ ስጧቸው (“1” - በጣም አስፈላጊ)። ምንም እንኳ ሁሉም ጠቃሚ ቢሆኑም ከእነዚህ ውስጥ የምትመርጡት ሰባት ብቻ ነው። ርስ በርሳቸው ተያያዥ የሆኑ ዕሴቶችን አስወግዱ። ---- የእግዚአብሔርን ቃል ማስተማር ---- ኅብረት ---- አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ቡድኖች ---- አምልኮ ---- ጸሎት ---- ሥ ልጠና/ አባላት የጸጋ ስጦታዎቻቸውን እንዲጠቀሙ ማስታጠቅ ---- ወጣቶችንና ሕፃናትን ማገልገል ---- የተረጋጋ አመራር ---- መ ልካም ስም በማኅበረ ሰቡ ውስጥ መገንባት ---- መንፈሳዊ ስጦታዎችን መጠቀም ---- የተለያዩ ባህሎችን መወከል ---- የአምልኮ ዘዬ ---- የስብከት ዘዬ/መንገድ ---- የአምልኮ ይዘት ---- የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ---- የፋይናንስ ቅድሚያዎች ---- ውሕደትና ክትትል ---- መ ንፈሳዊ ሥርዓቶች (ጥናት፣ ጸሎት) ---- አካሉን መገንባት ---- የወንጌል ሥርጭት ---- ጐልማሶችን ማገልገል ---- ምክክር/ ምጋቤያዊ ክብካቤ ---- የሙዚቃ አገልግሎት ---- የማኅበራዊ ፍትሕ አገልግሎት ---- ደቀ መዝሙር ---- አስተዳደር ---- ተልእኮ ወደ ዓለም ሁሉ ---- ማኅበረ ሰቡን መድረስ ---- ማቀድና ግብ ማስቀመጥ ---- ዐዳዲስ ተሳታፊዎችን ማዋሐድ ---- ጥብቅ ግንኙነቶች

---- ካሪዝማዊ ዝንባሌ ---- ብሔር/ ባህል ተኮር ---- የቡድን አወቃቀር ---- የስብከተ ወንጌል ስልት ---- የፍትሕ ጕዳዮች ---- የአመራር ዘዬ

---- አስተምህሯዊ ንጽሕና ---- የተለያዩ መርሐ ግብሮች ---- ሌላ (ሌሎች)

የቡድን መልመጃዎች፡- ዝግጅት • 33

በውይይታችሁ መሠረት በቀጣዮቹ ከ6-12 ወራት ውስጥ ግቦቻችሁን አዳብሩና ሰነድ አዘጋጁ። ግቦቻችሁ ሊለኩ የሚችሉ መሆናቸውን ርግጠኞች ሁኑ። ግልጽ የመጨረሻ ቀናትን አስቀምጡ፤ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ግን ተጠሪ የሚሆን ሰው በኀላፊነት መድቡ። ግቦቻችሁን እስካስቀመጣችሁና ውሳኔያችሁን የምትወስኑበትን ቀን እስከቆረጣችሁ ድረስ ከኢቫንጄል ትምህርት በኋላ ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍ ትችላላችሁ።

34 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

መልመጃ 3 የቡድን ውጤታማነት 1

ወደ ቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድናችሁ ማን መጨመር እንዳለበትና የሚጨመሩት ሰዎች የሚጫወቱትን ሚና ለመወሰን ቡድናችሁ ራሱን የሚገመግምበት ተጨባጭ ዘዴ ያስፈልገዋል። 1. የSWOT ትንተና ውስጣዊ ብርቱና ደካማ ጐኖች (ልትቈጣጠሯቸው የምትችሏቸው ነገሮች እንደ ሀብት፣ ጥሪ፣ ስጦታ ወዘተ.) እና ውጫዊ ብርቱና ደካማ ጎኖች (ልትቈጣጠሯቸው የማትችሏቸው ነገሮች እንደ ኢኮኖሚ፣ የአካባቢ ሕጐች፣ የአካባቢው ለወንጌል ክፍት መሆን አለመሆን ወዘተ.) የመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ተወያዩ። • ውስጣዊ ብርቱ ጐኖች (ልትቈጣጠሯቸው የምትችሏቸው ነገሮች) • ውስጣዊ ደካማ ጐኖች (ልትቈጣጠሯቸው የምትችሏቸው ነገሮች) • ውጫዊ መልካም ዕድሎች (ከእናንተ ቍጥጥር ውጭ የሆኑ ነገሮች) • ውጫዊ አደጋዎች (ከእናንተ ቍጥጥር ውጭ የሆኑ ነገሮች) 2. ቡድን መገንባትን የተመለከቱ የውይይት ጥያቄዎች • አሁን ያሉት የቡድን አባላት ያሏቸው የተለያዩ ሚናዎችና ኀላፊነቶች ምንድን ናቸው? • የሚጐድሏችሁ ክሂሎቶች ወይም ሚናዎች ምንድን ናቸው እነዚህን ክፍት ቦታዎች ወይም ሚናዎች እንዴት ነው የምትሞሏቸው?

1 Adapted from an Evangel School exercise in Ripe for Harvest , pp. 188-205.

የቡድን መልመጃዎች፡- ዝግጅት • 35

• የቡድን አባላት ከስጦታቸው ጋራ በሚስማማ መልኩ እየተንቀሳቀሱ ነው ወይ? • ወደ ፊት ስትጓዙ የቡድናችሁን ውጤታማነት መገምገማችሁን እንዴት ነው የምትቀጥሉት? ይህን ለማድረግ ምን ምን መንገዶችን ነው የምትጠቀሙት? • በቤተ ክርስቲያናችሁ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ቦታዎች ላይ እነማን በቡድን ቢጣመሩና በጋራ ቢመደቡ የተሻለ እንደሚሆን ተወያዩ። • የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ሞዴላችሁ ምንድን ነው? • ቡድናችሁ ውሳኔዎችን እንዴት እንደሚወስን ግለጹ? • ቡድናችሁ ለሥልጠናና ለመመካከር መቼ፣ የት፣ እና እንዴት ነው የሚሰባሰበው? • ቡድናችሁ ቡድናችንን ለማጠናከርና ለማበርታት ምን ዐይነት ሥልጠና ወይም የዝግጅት መሣሪያዎች ያስፈልጉታል? • ቡድናችሁ በምን በምን ጉዳዮች ማደግ አለበት? • እንደ ቡድን ስኬታችሁን የምትገመግሙት እንዴት ነው? በውይይታችሁ መሠረት በቀጣዮቹ ከ6-12 ወራት ውስጥ ግቦቻችሁን አዳብሩና ሰነድ አዘጋጁ። ግቦቻችሁ ሊለኩ የሚችሉ መሆናቸውን ርግጠኞች ሁኑ። ግልጽ የመጨረሻ ቀናትን አስቀምጡ፤ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ግን ተጠሪ የሚሆን ሰው በኀላፊነት መድቡ። ግቦቻችሁን እስካስቀመጣችሁና ውሳኔያችሁን የምትወስኑበትን ቀን እስከቆረጣችሁ ድረስ ከኢቫንጄል ትምህርት በኋላ ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍ ትችላላችሁ።

36 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

መልመጃ 4 ተግዳሮቶችን የመቋቋም ዐቅምን ማጐልበት

ቤተ ክርስቲያን ለመትከልና ለመምራት በጋራ ስትሠሩ ቡድናችሁ ጤናማ የሆነ የአገልግሎት ሥርዓተ ጥለቶችን መመሥረት ይኖርበታል። ቤተ ክርስቲያን ተከላ አካላዊ፣ ስሜታዊና መንፈሳዊ መሰጠቶችን የግድ እንደሚልና በጋራ ጤናማ የሆኑ ንድፎችን ማዘጋጀት እንዴት እንደምትችሉ ቡድናችሁ ማወቅና መመካከር አለበት። መመሪያዎች ከዚህ በታች በቀረቡት ጥያቄዎች ዙሪያ ጤናማ የአገልግሎት ንድፎችን እንደ ቡድን በጋራ እንዴት መቅረጽ እንደምትችሉ ጊዜ ወስዳችሁ ተወያዩ። 1. በቡድናችሁ ውስጥ ቅድሚያ ሰጥታችሁ ልታዳብሯቸው የሚገቡ በተለያዩ ጊዜያት ሊደረጉ የሚችሉ መንፈሳዊ ተግባራት (ሰንበት፣ ጸሎት፣ ጾም፣ በቃሉ ውስጥ ለመሆን ጊዜ መውሰድ) ምንድን ናቸው? 2. ቡድናችሁ እንዴት ባለ መልኩ ጤናማ ቤተ ሰባዊ ከባቢን መደገፍና ማበረታታት ይችላል? 3. ቡድናችሁ ጤናማ መንፈሳዊና ቤተ ሰባዊ ከባቢን ለመፍጥር፣ ለመደገፍና ለማበረታት የተመደቡት ሰዎች ምን ዐይነት ሰዎች ናቸው? እንደዚህ ዐይነት ሰዎች ቡድናችሁ ከሌለው ድጋፍ በመስጠት ማደግ የምትችሉት እንዴት ነው? 4. ለቡድናችሁ የሚጠቅሙ ሥልጠናዎች ወይም መሣሪያዎች ይኖሩ ይሆን? 5. ተግዳሮቶችን መቋቋምን ማጐልበት በሚለው ትምህርት መሠረት መለወጥ ያሉብን ነገሮች ይኖሩ ይሆን?

የቡድን መልመጃዎች፡- ዝግጅት • 37

በውይይታችሁ መሠረት በቀጣዮቹ ከ6-12 ወራት ውስጥ ግቦቻችሁን አዳብሩና ሰነድ አዘጋጁ። ግቦቻችሁ ሊለኩ የሚችሉ መሆናቸውን ርግጠኞች ሁኑ። ግልጽ የመጨረሻ ቀናትን አስቀምጡ፤ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ግን ተጠሪ የሚሆን ሰው በኀላፊነት መድቡ። ግቦቻችሁን እስካስቀመጣችሁና ውሳኔያችሁን የምትወስኑበትን ቀን እስከቆረጣችሁ ድረስ ከኢቫንጄል ትምህርት በኋላ ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍ ትችላላችሁ።

ተከላ

ክፍል 2፥ መጀመርና መሰባሰብ በዚህ ክፍል ውስጥ በወንጌል አንቀሳቃሽ ኀይል፣ ባህልንና ዐውድን ማሰስ፣ እንዲሁም የስብከተ ወንጌል ስልቶችን መቀየስና መከታተል በሚሉ ጉዳዮች ላይ እናተኩራለን።

ትምህርት 4 የወንጌል አንቀሳቃሽ ኀይል ትምህርት 5 ባህልንና ዐውድን ማሰስ ትምህርት 6 ስብከተ ወንጌል እና ክትትል

39

ክፍል 2፥ መጀመርና መሰባሰብ • 41

ትምህርት 4 የወንጌል አንቀሳቃሽ ኀይል መጋቢ ሎሬንዞ ኤሊዞንዶ

ወንጌል ሙሉ በሙሉ ስለ ኢየሱስ ነው። ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የሚጠቁሙት ወደ ኢየሱስ ስለሆነ ወንጌል ቅዱሳት መጻሕፍት ማእከላዊ ጭብጥ ነው። ወንጌል፥ ታላቁ አምላካችን የወደቀውን ሰው በርኅራኄ የተመለከተበት፤ እና ልንኖረው ያልቻለውን ሕይወት ይኖረው ዘንድ ልጁን ኢየሱስን የላከበት፤ እንዲሁም እኛ ልንከፍለው ያልቻልነውን ዋጋ ሊከፍል፣ ከሙታን በመነሣት፣ ሰይጣንን፣ ኀጢአትንና ሞትን ድል በመንሣት እንዲሁም በእግዚአብሔርና በሰው መካከል የነበረውን መለያየት ያስወገደበት ምሥራች ነው። ያዳነን ብስራት ይህ ነው። ወንጌል የሚያድነን ብቻ ሳይሆን የክርስቶስን ተልእኮ እንድንፈጽምም ይልከናል። እንደ አለመታዳል ሆኖ ዛሬ ላይ ብዙ ክርስቲያኖች ወንጌልን እንደ ለመለወጥ እንደሚተቅም መሣሪያ ብቻ አድርገው ይመለከቱታል። ነገር ግን ወንጌል ከክርስትና ሀ ሁ የበለጠና የክርስትና እምነት ከ ሀ እስከ ፐ ነው። ሐዋርያ ጳውሎስ በሮሜ 1፥16 እንዲ በማለት ያስታውሰናል “በወንጌል አላፍርም፤ ምክንያቱም ለሚያምን ሁሉ ለድነት የሚሆን የእግዚአብሔር ኀይል ነው፤ ይህም በመጀመሪያ ለአይሁድ፣ ቀጥሎም ለአሕዛብ ነው።” ወንጌል የሚያድነንና የሚልከን ብቻ ሳይሆን እንደ ቤተ ክርስቲያን ቅርጽ የሚሰጠንም ነው። በሌላ አገላለጽ፥ ቤተ ክርስቲያን የቆመችው በወንጌሉና ለወንጌሉ ነው። ቤተ ክርስቲያን እንደ ልብ ናት። ልብ ደም የሚረጨው ወደ ራሱ ብቻ ቢሆን ሰውነት ይሞታል። ልብ ደምን ወደ ሰውነት መርጨት ብቻ ቢሆን ሥራው አሁንም ሰውነት ይሞታል። ሰውነት በሕይወት እንዲኖር ልብ ወደ ውስጥም ወደ ውጭም ደም መርጨት አለበት። በተመሳሳይ መልኩ ቤተ ክርስቲያን ሕያው ለመሆን ያለ ማቋረጥ ወደ ወንጌሉ መምጣት አለባት እንዲሁም ሕያው ሆና ለመዝለቅ ወደ ሌሎች መላክ አለባት። ልክ እንደ ልብ ኢየሱስም በተመሳሳይ ስልተ ምት እንድንኖር ፈጥሮናል። እግዚአብሔርን፣ ባልንደራችንን እንድንወድድ እና ርስ በርሳችን (ቤተ ክርስቲያን) እንድንዋደድ ነግሮናል።

42 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

ከሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ወንጌሉን ለማወጅ፣ ለመጠበቅ እና ለማስፋት ሕይወታቸውን የሰጡ ሰዎች ታሪክ ነው። አብያተ ክርስቲያን እና ቤተ ክርስቲያን ተካዮች በብዙ ነገሮች ተነሳስተው ይመራሉ። አንዳንዶች ለተሻለ ነገ፣ ለተሻሉ ባልጀሮች፣ ወይም ለተሻሉ አብያተ ክርስቲያናት ራእይ በመሰነቅ ይንቀሳቀሳሉ። እነዚህ ሁሉ መልካም ነገሮች ናቸው ነገር ግን በዋናነት የሚመራንና የሚያንቀሳቅሰን ወንጌል ሊሆን ይገባል። ስለዚህ የወንጌሉን መልእክት፣ ተልእኮ እና መንገዶች መረዳት በጣም አስፈላጊ ነው። ምን ማመን እንዳለብን፤ በዙሪያችን ያለውን ዓለም እንዴት ማየት እንዳለብንና ቤተ ክርስቲያንም ምን መሆን እንዳለባት የሚነግረን ወንጌል ነው። I. የወንጌሉ መልእክት • መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ግልጽ ትዕይንትን ይተርካል ይህም የእግዚአብሔር ታሪክ ነው። ከዘፍጥረት እስከ ራእይ የእግዚአብሔር ፈቃድ ሰዎችን ለመቤዠት መሆኑ ግልጽ ነው። • በእግዚአብሔር ታሪክ ውስጥ ዋናው አሸናፊ ኢየሱስ ነው። • ሙሉው የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ስለ ርሱ የሚናገር እንደሆነ ጌታችን ግልጽ አድርጓል. • ዐዲስ ኪዳን ስለተገለጠው ኢየሱስ ክርስቶስ ከሆነ ብሉይ ኪዳን ደግሞ ተሰውሮ ስለነበረው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው የሚል አባባል አለ። 1 መጽሐፍ ቅዱሳችን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻው የሚተርከው ስለ ኢየሱስ ነው። • በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እና በመላው ዓለም በሚገኙ ልቦች ውስጥ ኢየሱስ ማእከላዊው፣ ዋናው፣ አቻ የሌለው የሆነው ለምንድን ነው? ምክንያቱም ከሰማይ ወደ ምድር የወረደ፣ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ የሆነ፣ ፍጹም ሕይወት የኖረ፣ የስርየት ሞትን የሞተ፣ ኀጢአትን፣ ሰይጣንን፣ ጨለማንና ሞትን ድል ለማድረግ የተነሣ ርሱ ብቻ ነው። አዳም መኾን ያቃተውን ሁሉ፣ እስራኤል መሆን የተሳናትን ሁሉ፣ እኛ ሁላችን የወደቅንበትን ሁሉ ማድረግ የቻለው

1 Augustine’s statement from “Questions on the Heptateuch,” 2.73 in The Works of St. Augustine: Writings On The Old Testament .

ክፍል 2፥ መጀመርና መሰባሰብ • 43

ኢየሱስ ነው። እኛ ያልተሳካልንን ነገር ሁሉ ርሱ አሳክቷል። ርሱን እንድናመልከውና በርሱም ደስ እንድንሠኝ የፈጠረን፤ እኛ ግን በዐመፃችን ያሳዘንነው ርሱ ታሪኩን ለማዳን ጣልቃ ገባ። II. የወንጌሉ ተልእኮ • ወንጌል፥ የሚያድነንና የክርስቶስን ተልእኮ እንድንፈጽም የሚልከን ምሥራች ነው። ኢየሱስ ተልእኮውን እንዲህ በሚል ዐጭር ቃል ገልጾታል “የሰው ልጅ የመጣው የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን ነው” (ሉቃስ 19፥10)። • ወንጌል ሲታወጅ ሰዎች ሰምተው እንዲረዱት ወንጌሉ ዐውዳዊ መሆን አለበት። ዐውዳዊ የማድረግ ሂደት ሲነሣ ብዙዎች ሐዋርያ ጳውሎስን ያስባሉ። ጳውሎስ እንዲህ አለ “ደካሞችን እመልስ ዘንድ፣ ከደካሞች ጋራ እንደ ደካማ ሆንሁ። በሚቻለኝ ሁሉ አንዳንዶችን አድን ዘንድ፣ ከሁሉም ጋር ሁሉን ነገር ሆንሁ። ይህን ሁሉ የማደርገው፣ ከወንጌል በረከት እካፈል ዘንድ፣ ስለ ወንጌል ብዬ ነው” (1ቆሮንቶስ 9፥19-23)። እንዲሁም “እኔ የክርስቶስን ምሳሌ እንደምከተል እናንተም የእኔን ተከተሉ” (1 ቆሮንቶስ 11፥1) ያለው ጳውሎስ ነው። በሌላ አገላለጽ ዐውዳዊነትን በተመለከተ የጳውሎስ ፍጹም ምሳሌ ኢየሱስ ነበረ። ዮሐንስም እንዲህ ብሎ ጽፏል “ቃልም ሥጋ ሆነ፤ በመካከላችንም ዐደረ፤ እኛም ጸጋንና እውነትን ተሞልቶ ከአባቱ ዘንድ የመጣውን የአንድያ ልጅን ክብር አየን” (ዮሐንስ 1፥14)። በክርስቶስ ትሥጕት የእግዘአብሔር መንግሥት ወደ ዓለም መግባቷን አየን። በክርስቶስ የዓለም ብርሃን ወደ ጨለማችን ዘልቆ ሲቤዥና ነጻ ሲያወጣ አየን። በእኛ በኀጢአተኞች ሰዎችና በቅዱሱ በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን ግድግዳ አፍርሶ ኢየሱስ ቀረበን። • ኢየሱስም “አብ እኔን እንደ ላከኝ፣ እኔም እናንተን እልካችኋለሁ” አላቸው (ዮሐንስ 20፥21)።

44 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

ወደ ከተሞቻችንና ባልንጀሮቻችን የወንጌሉን መልእክት እንድናደርስ ኢየሱስ እየላከን ነው። ነገር ግን የክርስቶስን ተልእኮ በብቃት እንፈጽም ዘንድ የተለያዩ የባህል ዐውዶችን ጠንቅቀን በመረዳት ብልኆች መሆን አለብን። ዐውዳዊነት የሚጠይቀው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜዎችን 2 ጠንቅቆ መረዳት ብቻ ሳይሆን በወንጌል የምንደርሳቸውንም ሰዎች ባህል ጠንቅቆ መረዳትን ይጠይቃል። ይህ የአተረጓጐም ሂደት ባህላችንን በወንጌል ተልእኮ መነጽር እንድንመለከት ይረዳናል። III.የወንጌሉ መንገድ • ወንጌሉ እኛን በማዳንና ለተልእኮ በማሠማራት ብቻ አላበቃም ነገር ግን ያበጀናልም። ኢየሱስ ወደ ወንጌሉ (ኢየሱስን መውደድ)፣ ወደ ባህሉ (ባልንጀሮቻችንን መውደድ)፣ እና ወደ ቤተ ክርስቲያን (ወንድሞችና እኅቶቻችንን መውደድ) ጠራን። በዳንን ወቅትና ለተልእኮ ከመሰማራታችን በፊት በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ዐውድ ውስጥ በወንጌል ቅርጽ እንይዛለን። ቤተ ክርስቲያን፥ ዓለምን ለመድረስ የእግዚአብሔር ቀዳሚ ዕቅድ ናት። ኢየሱስ እንዲህ አለ፥ “በዚህ ዐለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አያሸንፏትም” (ማቴዎስ 16፥18)። • ወንጌልና ተልእኮ እንዲሁ ከምንም ተነሥተው የሚመጡ ነገሮች አይደሉም። የቤተ ክርስቲያን ትኩረትና ዐላማዎች ናቸው፤ ወደ ክርስቶስና ወደ ቤተ ክርስቲያኑ የተጨመሩትን የእግዚአብሔርን ሕዝብ የሚያያይዙ አቀጣጣዮች ናቸው። ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔርን አገዛዝ ምንነት ስለምትገልጽ የክርስትና ተልእኮ ወሳኝ ክፍል ናት። ተልእኮ፥ ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር፣ለባልንጀሮቻችን ያለንን ፍቅር፣ እንዲሁም ርስ በርሳችን ያልነን ፍቅር ለሌሎች የምናሳይበት መድረክ ነው። 2 ሥነ ፍታቴ፥ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍላተ ምንባብ ትርጓሜ ለመረዳት እና ለመተርጎም እንዲሁም ቍልፍ መርሖችን ለማስቀመጥ የሚረዳ የጥናት መሣሪያ ነው። በሥነ ፍታቴ ሂደቶች ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎች ለማግኘት Rev. Dr. Don L. Davis, Bible Interpretation . The Capstone Curriculum, Module 5. (Wichita: TUMI Press, 2005) ይመልከቱ።

ክፍል 2፥ መጀመርና መሰባሰብ • 45

ስለዚህ፣ ቤተ ክርስቲያን የምንናገረው ነገር ከምንኖረው ሕይወት ጋራ የሚገናኝ መሆኑን በሚገባ ማጤን አለባት። በዚህ አግባብ፥ የማይታየው አምላክ በእግዚአብሔር ሕዝቦች መዋደድ በኩል ይታያል (1ዮሐንስ 4፥12)። • ቤተ ክርስቲያን ከመሰባበሰቢያ ቦታ ያለፈች ናት። ቤተ ክርስቲያን በሰዎች መካከል የእግዚአብሔር መንግሥት መገለጫ ማሳያ ናት። በሌላ አገር የአንድ ሉዓላዊ አገርን ፍላጎት እንደሚወክል ኤምባሲ ቤተ ክርስቲያንም በዚህ ዓለም የእግዚአብሔር ኤምባሲ ናት። ቤተ ክርስቲያን በዚህ ዓለም ውስጥ የወንጌሉን ኅይልና ተጽዕኖ በሕይወታቸው የሚገልጡ እንደራሴዎች ናቸው። “ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር መንግሥት ማኅበረ ሰብ እንጂ በራሷ ንግሥት አይደለችም። መንግሥቱ የእግዚአብሔር የንግሥና የርሱ አገዛዝ በረከቶች የሚዳረስባቸው ቦታዎች ኹሉ ናቸው። በዚህ ረገድ ቤተ ክርስቲያን በእግዚአብሔርን አገዛዝ እና ንግሥና በረከቶች ሥር የተሰባሰቡ ሰዎች ማኅበር ናት። የእግዚአብሔር መንግሥት ቤተ ክርስቲያንን ፈጠረ፤ በቤተ ክርስቲያን በኩል ይሠራል፤ በቤተ ክርስቲያን በኩልም ለዓለም ይታወጃል።” 3 IV. መደምደሚያ የወንጌል መሪ ኀይል በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ተገልጿል፤ ኢየሱስ እንዲህ አለ “እነዚሁ መጻሕፍት ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው” (ዮሐንስ 5፥39)። ከዘፍጥረት እስከ ራእይ ያሉት መጻሕፍት ሁሉ ወደ አዳኛችንና ንጉሣችን ኢየሱስ የሚያመለክቱ ናቸው። ስለዚህ፥ ስትሰብኩ፣ ስታስተምሩ፣ እና ደቀ መዛሙርት ስታደርጉ እንዲህ የሚለው የጳውሎስ ንግግር ዘወትር በልባችሁ ይሁን “በመካከላችሁ ሳለሁ ኢየሱስ ክርስቶስን፣ ያውም የተሰቀለውን፣ እርሱን ብቻ እንጂ ሌላ እንዳላውቅ ወስኜ ነበርና” (1ቆሮንቶስ 2፥2)። የወንጌል መሪ ኀይል የጠፋውን ለማዳን የመጣውን የኢየሱስን ምሳሌ በምንከተልበት በተልእኮ ዐውድ ውስጥ ተገልጿል። ወንጌል ያድነናል

3

Mere Missions , p. 148.

46 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

ለተልእኮም ያሰማራናል። ከኀጢአት ያዳነን ከመኾኑ ባሻገር ሕዝቦችን ደቀ መዛሙርት እንድናደርግ ተልእኮ ሰጥቶናል። የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ መከማቸትና የሰዎች መሰባሰቢያ ስፍራ መሆን ብቻ አይደለም ይልቁንም የማይለወጠውን የወንጌል እውነት በተጠራንበት ዐውድ ውስጥ ሁሉ በመግለጥ የኢየሱስን ተልእኮ መፈጸም ነው። በመጨረሻም፥ የወንጌል መሪ ኀይል ለእግዚአብሔር፣ ለባልንጀሮቻችን እንዲሁም ርስ በርሳችንን ያለንን ፍቅር በምንገልጥበት ዐውድ ውስጥ ተገልጿል።

ክፍል 2፥ መጀመርና መሰባሰብ • 47

ትምህርት 5 ባህልንና ዐውድን ማሰስ 1 መጋቢ ሎሬንዞ ኤሊዞንዶ

የምንኖረው በፈጣን ለውጥ ውስጥ በሚገኝ ዓለም ውስጥ ነው። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ከተሞች የሕዝቦች መልከዓ ምድራወ አቀማመጥ በእጅጉ ተለውጧል። አብዛኛው የዓለማችን ሕዝብ በትላልቅ ዓለም አቀፍ ከተሞች ውስጥ መኖርን ምርጫው እያደረገ ይገኛል፤ ይህም እጅግ የበለጸጉ ከተሞችን ፈጥሯል። ይህ ለውጥና የሕዝብ እድገት በርካታ ማኅበረ ሰቦችን ከማስገኘቱም በላይ የተለያዩ የባህል ልዩነቶችንም ፈጥሯል። “ብዝኅነት” የሚለው ቃል ለዘመናችን ዐውድ እንግዳ ቃል ባይሆንም እንዲሁም የባህልን ልዩነት መረዳት አስፈላጊ እንደሆነ ብዙዎች ቢስማሙም ባህል ምን እንደሆነ ሊያብራሩ የሚችሉ ግን ጥቂቶች ናቸው። ቤተ ክርስቲያን ውጤታማ በሆነ መንገድ ወንጌሉን ለሰዎች እንድታደርስ እግዚአብሔር ስለጠራት ባህሎችን በማሰስና በመረዳት ረገድ የሠለጠንን ልንሆን ይገባል። I. ባህል ምንድን ነው? • ዶ/ር ዴቪስ ባህልን እንዲህ በማለት ይተረጉሙታል፦ “ባህል፥ የተቀናጀ፣ በደንብ የተመሠረተ፣ ማኅበረ ሰባዊ ብያኔ ብያኔ ያላቸውን ባሕርያትና በአስተሳሰብ፣ የራሱ የሆነ የግምገማ ሥርዐት ያለው ንጽረተ ዓለም ነው።” በቀላል አነጋገር ባህል የምንማረው ሥርዓትና የሥነ ምግባር ሲሆኑ እነዚህም ዕሴታቻችንና ንጽረተ ዓለማችንን የሚቀርጹ፣፣ በማኅበረ ሰቡ ውስጥ የሚኖረንን ማኅበራዊ መስተጋብር የሚቀርጽ ሥርዐት ነው። • እነዚህ የምንማራቸው ሥርዐቶችና ባሕርያት ከየት ነው የሚመጡት? እንዴትስ ነው የሚያድጉት? ይህን በተመለከተ ዶ/ር ዴቪስ ሦስት የባህል አቅጣጫዎችን ያብራራሉ።.

1 This seminar is rooted in the concepts of the seminar “The Difference That Difference Makes” in Ripe for Harvest , pp. 139-153.

48 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

1. የዕውቀት ገጽታ፥ ይህ ባህሉ የሚያውቀውና እውነታና እውነት ብሎ የሚረዳቸው ነገሮች ናቸው። የዕውቀት ገጽታ 2. የስሜት ገጽታ፥ ይህ የስሜቶችና የስሜት መገለጫዎችን የሚመለከት ሲሆን ባህሉ የሚወድዳቸውንና የሚጠላቸውን ነገሮች የሚገልጽ ነው። 3. የምዘና ገጽታ፥ ይህ አንድ ባህል ዕሴቶቹን፣ የሰዎችን መስተጋብር ሥነ ምግባራዊና ኢ ሥነ ምግባራዊ (ትክክልና ስሕተት) በማለት የሚበይንበት ሥርዓት ነው። • በዋናነት ባህል ዕሴቶችን የተመለከተ ነው። ባህልን ለመረዳት ሰዎች ትልቅ ቦታ የሚሰጡት ነገር ምን እንደሆነና ለእነዚህ ነገሮች ከፍ ያለ ቦታ የሚሰጡት ለምን እንደሆነ መረዳትን ይጠይቃል። የሚወድዱት፣ የሚኖሩለት፡ የሚሞቱለት፣ ትልቅ ዋጋ የሚሰጡት ነገር ባህሉን የሚገልጽና ባህልን የሚፈጥር ነው። II. የባህል ልዩነቶችን መረዳት ባህልን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማሰስ ማወቅ ያለብን ባህል ምን ማለት እንደሆነ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ባህሎች መካከል ያለውንም ልዩነት መረዳት ይጠበቅብናል። • እግዚአብሔር ልዩ ልዩ አድርጎ ስለ ፈጠረን ልዩነቶች መልካም ናቸው፣ ሐዋርያት ሥራ 17። • በባህሎች (በሰዎች) መካከል ያለው ልዩነት ግልጽና ጉልህ ነው። • ባህላዊ ልዩነቶችን አሳንሶ መመልከት ወይም ችላ ማለት በወንጌል ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።. III.ለየት ያለ ክርስቲያናዊ ባህል መመሥረት ነገር ግን ኢየሱስን ከምንም ነገር በላይ ከፍ አድርገው ለሚመለከቱ ክርስቲያኖች ባህል በሰዎች ስኬቶች የሚበየን አይደለም። ከዚህ ይልቅ “ኢየሱስ ጌታ ነው” በሚሉ ሦስት ቃላት ተገልጿል። ቤተ ክርስቲያን ለህልውናዋ የተለየ ምክንያት ያላት ስትሆን የተመሠረተችው፣ ህላዌዋን

ክፍል 2፥ መጀመርና መሰባሰብ • 49

የሚበይኑ የሚያሳድጉና የሚመሩት ልዩ የሆኑት ክርስትያናዊ ባህሎች በእነዚህ ሦስት ቃላት ላይ የተመሠረቱ ናቸው። • ከሁሉ አስቀድሞ ክርስቲያናዊ ባህል በተፈጥሮው ልዕለ ተፈጥሯዊ ስለሆነ ፈጽሞ ከዓለም የተለየ ነው። • ሁለተኛው፦ ኢየሱስ ጌታ ነው የሚለው እውነት የቤተ ክርስቲያንን ምንነት ብቻ ሳይሆን እድገትም የሚገልጽ ነው። ቤተ ክርስቲያን በራሷ ስላልተፈጠረች እና ለራሷም ስለማትኖር ልዩ የሆነ ክርስቲያናዊ ባህል አላት። • በመጨረሻም፦ ኢየሱስ ጌታ ነው የሚለው እውነታ ቤተ ክርስቲያንን የሚመራትም ነው። ቤተ ክርስቲያን፥ የተዋጁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች የትኛውንም ፖለቲካዊ፣ ብሔራዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ፣ ጾታዊ የባህል ገደቦችን ሁሉ የሚያልፍ ነው። ይህ የሆነው ግን በራሱ የተሻለ ወይም የላቀ ስለሆነ ሳይሆን ለመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣንና በቂነት በልዩነት ስለሚገዛ ነው። IV. መደምደሚያ የባህል አሰሳ ግቡ እያንዳንዱ ዐውድ የራሱ የሆነ ባህል እንዳለውና ውጤታማ ስብከተ ወንጌል ማድረግ የባህል ልዩነቶችን እንዳሉ መረዳት ነው። ይህም ዋነኛው ግባችን የሆነውን ሰዎችን ወደ ተመሳሳይ ባህል ሳይሆን ወደ ክርስቶስ የማምጣት ተልእኮ እንድንፈጽም የሚያስችለን ነው። ዐላማችን ሰዎች ያላቸውን የተለየ ባህል እንዲያጡ ማድረግ ሳይሆን ለኢየሱስ ጌትነት እንዲገዙ መምራት ነው። ልክ ኢየሱስ የባህል ግድግዳዎችን ጥሶ ወደ እኛ እንደመጣ እንዲሁ እኛም በዘመናችን ዐውድ ውስጥ የሚገኙ የባህል ዕንቅፋቶችን በማለፍ ወንጌልን ማወጅና መግለጥ አለብን። የቅዱሳት መጻሕፍትን ሥልጣትና ክርስቶስን መምሰልን ቅድሚያ በመስጠት አማኞች የባህል ልዩነቶችን በማለፍ ወንጌል ውጤታማ በሆነ መልኩ ማወጅና መግለጥ ይችላሉ።

Made with FlippingBook - Share PDF online