Church PLANT Manual, Amharic Edition
መግቢያ ሬቨረንድ ቴድ ስሚዝ
የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ መጽሐፍ የተሰናዳው የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድናችሁ የቤተ ክርስቲያን ተከላ መርሖችን እንዲገነዘቡ፣ በኢቫንጌል ትምህርት ቤት የሥልጠና ጊዜያት እነዚህን መርሖች ወደ ተግባራዊ ግቦች የመቀየር ጉዞን ለመርዳት እንዲሁም በመጨረሻም ለሚቀጥሉት ዐሥራ ሁለት ወራት የቤተ ክርስቲያናችሁን ስልታዊ ዕቅድ እንድታዘጋጁ ለማገዝ ነው። የመምሪያ መጽሐፉ እና የኢቫንጌል ትምህርት ቤት ራሱ ዐዲስ አብያተ ክርስቲያናት ለሚተክሉ፣ ዳግም ተከላ (ዳግም ጅማሬ፣ ተሓድሶ ወይም ዳግም ማንሰራራት) ለማድረግ እየተዘጋጁ ላሉ፣ ምጋቤያዊ አመራር ተግባር ወደ ቀጣዩ ትውልድ የሚሸጋገርበትን ኺደት ለሚሹ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን ተከላ እንቅስቃሴን ለማነሣሣት ለሚፈልጉ ሰዎች ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ኢቫንጌል፥ በመርሕ ላይ የተመሠረተ ስልት ሲሆን በበርካታ የተከላ፣ ዳግም ተከላ፣ የሽግግር ወቅቶች እና ሌሎች ዐውዶች ውስጥ ሊተገበር የሚችል ነው። ይህ ደግሞ ለብዙ ዓመታት የተለያዩ ቡድኖች ለራሳቸው ዐውድ ስልት እንዲያጐለብቱ ባሠለጥንንበት ጊዜ የተስተዋለ ነው። ስለዚህ፥ “ተከላ” የሚለውን ቃል ከኢቫንጌል መርሖች ጋራ የተያያዘ አካታች ቃል መሆኑን መረዳት ጠቃሚ ነው።
1
Made with FlippingBook - Share PDF online