Church PLANT Manual, Amharic Edition
ይህ መጽሐፍ ለዶ/ር ዶን ዴቪስ የተበረከተ ሲኾን ርሱ ባይኖር ኖሮ ይህ መጽሐፍ ለፍሬ ባልበቃ ነበር። ርሱ ነቢያዊ ድምፅ ነው፣ በርእሰ ጒዳዩ ላይ በርካታ እጅግ ጠቃሚ ጽሑፎችን አበርክቷል፣ የአመራር ጉልብትና ማሠልጠኛ መጽሐፎችን አዘጋጅቷል፣ እንዲሁም በአሜሪካና በመላው ዓለም ጤናማ አብያተ ክርስቲያናት እንዲተከሉ በየስፍራው የሚገኙ ክርስቲያኖች በክርስቶስ ሥራ ላይ እንዲሳተፉ ዘወትር ጥሪ ያቀርብ ነበረ። ዶ/ር ዳቪስ በነገረ መለኮት፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥናቶች፣ እና የከተማ ቤተ ክርስቲያናት ተከላ ላይ የሠራቸው ሥራዎች የዚህ ጽሑፍ ጠንካራ መሠረቶች ናቸው። በእጅጉ የዶ/ር ዳቪስ ውለታ አለብን። ይህን መጽሐፍ በጥንቃቄ የሚያነብቡ ሰዎች በቀላሉ ሊያስተውሉ እንደሚችሉት በርካታ ጽሑፎችን ከርሱ የጠቀስን ሲኾን በርካታ ትምህርቶቹንም በዚህ መጽሐፍ ውስጥ አካትተናል። ይህ መጽሐፍ የርሱን ታላላቅ ሥራዎች የሚያስታውስ እና በድኅነት በተጎዲ ማኅበረ ሰቦች ውስጥ የክርስቶስ ኢየሱስን ዐርማ የሚያውለበልቡ ጤናማ አብያተ ክርስቲያናት እንዲበዙ እና ሰዎችም እግዚአብሔር በክርስቶስ የገለጠውን ፍቅር በማወቅ ወደ ድነት እንዲመጡ እንጸልያለን። ይህን መጽሐፍ በሚያነብቡ ዘንድ ኹሉ የጥሪ ድምፁ ያስተጋባ። ይህም ጥሪ ወደ ኢየሱስን የሚያመላክተን፣ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ጥረትን የሚያነሣሣ፣ እንዲሁም የክርስቶስን መንግሥት ለርሱ ክብር የሚያሰፋ ይኹን።
- ቴድ ስሚዝ (ሬቨረንድ)
Made with FlippingBook - Share PDF online