Conversion and Calling, Amharic Student Workbook
/ 1 0 9
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
መ. በክርስቶስ ያለንን ነፃነታችንን እንድንጠቀም የተጠራንባቸው አላማዎች።
1. ለሚጠቅመው ነገር፣ 1ኛ ቆሮ. 6፡12 ሀ - “ሁሉ ተፈቅዶልኛል፣ ሁሉ ግን አይጠቅምም።”
2. ለማንኛውም ጎጂና ሱስ የሚያስይዝ ነገር አይደለም፣ 1ኛ ቆሮ. 6፡12 ለ - “ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ አይሠለጥንብኝም።”
3. የሚያንጽ ብቻ ነው፣ 1ኛ ቆሮ. 10፡23 - “ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ሁሉ ግን የሚጠቅም አይደለም፤ ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ነገር ግን ሁሉ የሚያንጽ አይደለም።”
4. ደካማ አማኝን የሚያሰናክል ማንኛውም ነገር አይደለም፣ 1ኛ ቆሮ. 8፡13 - “ስለዚህም መብል ወንድሜን የሚያሰናክለው ከሆነ፥ ወንድሜን እንዳላሰናክለው ለዘላለም ከቶ ሥጋ አልበላም።”
5. በጌታ ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን ለመውደድ እድል ለሚሰጡ ነገሮች ብቻ፣ ገላ. 5፡13 - “ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኋልና፤ ብቻ አርነታችሁ ለሥጋ ምክንያትን አይስጥ፥ ነገር ግን በፍቅር እርስ በርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ።”
4
6. እግዚአብሔርን ለሚያከብሩ ነገሮች ብቻ፥ 1ኛ ቆሮ. 10፡31 - “እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡብትሆኑ ወይምማንኛውንም ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።
7. አይሁድን፣ አሕዛብን፣ ወይም የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ለሚያስቆጣ ማንኛውም ነገር አይደለም፣ 1ኛ ቆሮ. 10፡32 - “ለአይሁድም ለግሪክም ሰዎች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንም ማሰናከያ አትሁኑ።”
8. ሌሎችን ወደ ክርስቶስ ለማሸነፍ ለሚረዱት ነገሮች ብቻ፣ 1ኛ ቆሮ. 10፡33 - “እኔ ደግሞ ብዙዎቹ ይድኑ ዘንድ ለጥቅማቸው እንጂ የራሴን ጥቅም ሳልፈልግ በሁሉ ነገር ሰውን ሁሉ ደስ እንደማሰኝ፥”
Made with FlippingBook - Online magazine maker