Conversion and Calling, Amharic Student Workbook
/ 1 1 5
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
እግዚአብሔር በሕይወታችን ላይ በቃሉ አማካኝነት ስለሚጠራው ጥሪ የምታቀርቡትን ጥያቄዎች ከተማሪዎችህ ጋር የምትወያይበት ጊዜ አሁን ነው። የደቀመዝሙርነት፣ የማህበረሰብ፣ የነፃነት እና የተልእኮ የተለያዩ ልኬቶች ቀጣይነት ያለው ውይይትና ፍቺ ይፈልጋሉ፣ በተጨማሪም እነዚህ ጽንሰ-ሀሳቦች ከአንተ ህይወትና አገልግሎት ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ መረዳት በጣም አስፈላጊ ነው። ጽሑፉን በፍጥነት መርምረህ አሁን የእግዚአብሔርን ጥሪ ጉዳይ በተመለከተ ምን ጥያቄዎች እንዳሉህ ወስን። ምናልባት ከዚህ በታች ያሉት አንዳንድ ጥያቄዎች የራስህን ልዩ እና ወሳኝ ጥያቄዎችን እንድታነሳ ሊረዱህ ይችላሉ። * አንድ ሰው በግል ሕይወቱ ውስጥ ኢየሱስ ጌታ መሆኑን ክዶ እርሱ ግን በእውነት እንደዳነ መናገር ይችላል? መልስህን አስረዳ። * ጥሪው ለክርስቲያን ማኅበረሰብ ከሆነ፣ እኛ መሆን አለበት ብለን በምናምንበት መልኩ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚመለክበትና የሚከበርበት ቤተ ክርስቲያን ማግኘት ካልቻልን ምን እናድርግ? ካሴቶችን፣ ትምህርቶችን፣ መጻሕፍትንና ሌሎች የማስተማሪያ ቁሳቁሶችን ብንጠቀምስ? - በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለን ስብከት እና ኅብረትን መተካት ይችላሉ? * በክርስቶስ ባለን ነጻነት የመኖር እንቅፋቶች ምንድን ናቸው? በከተማ ውስጥ ባሉ ማህበረሰቦች በተለይም ሰዎች ነፃነትን የፈለጉትን ከማድረግ ጋር በሚያያይዙት ማህበረሰብ ውስጥ በኢየሱስ ስላለ ነፃነት መስበክ አደገኛ አይደለምን? * በዛሬው ጊዜ “ጤናና ብልጽግና” የእግዚአብሔር የረከቱና የመገኘቱ ምልክቶች እንደሆኑ ስለሚያትቱ ትምህርቶችስ ምን ማለት ይቻላል? ሁሉም ስህተት ናቸው? በእግዚአብሔር የደቀመዝሙርነት ጥሪ ላይ ያለ አስተምህሮ ከዚህ ዓይነት ትምህርት ጋር እንዴት ይዛመዳል? * በእግዚአብሔር ጥሪ መሠረት መኖር መከራንና ስደትን እንደሚያመጣ እርግጥ ነው? ኢየሱስ ለእኛ ያሸነፈው ድል ለምንድነው አውቶማቲክ ያልሆነው? ማለትም ኢየሱስ በመስቀል ላይ ያደረገው ነገር ለምን አሁን ለእኛ ተጨማሪ ትግልን አላስቀረልንም? በኢየሱስ ስም ከእርሱ ውጡ አንዲት ውድ እህት በመንፈሳዊ የቴሌቭዥን ፕሮግራሞች ላይ ነጻ የመውጣት አገልግሎትን አስፈላጊነት እና ሂደት በተመለከተ የተለያዩ መምህራንን በትጋት ስትከታተል ቆይታለች። በትምህርቱ ሙሉ በሙሉ አምና፣ በሰንበት ትምህርት ቤቷ ውስጥ ላሉ ሴቶች የሚያጋጥሟቸው አብዛኞቹ (ምናልባትም ሁሉም) ችግሮች ከሕይወታቸው ውስጥ አጋንንትን ለማስወጣት ችላ በማለታቸው እንደሆነ ማስተማር ጀምራለች። እነርሱንም በማስለቀቅ፣ በመለየት፣ በመገሰጽና በእነርሱ ላይ ድልን በማወጅ አንዳንድ ዘዴዎችን በማስተማር በዚህ አገልግሎት ላይ ማተኮር ጀምራለች፤ አንዳንድ እህቶች በዚህ ትምህርት ሐዋርያት በየትም ቦታ ላይ እንዲህ እንድናደርግ አላዘዙንም በማለት በዚህ አይነት ተግባር አይስማሙም። ይህንን ሁኔታ እንዴት ትይዘዋለህ?
የተማሪው ትግበራ እና አንድምታ
4
ጥናቶች
1
Made with FlippingBook - Online magazine maker