Conversion and Calling, Amharic Student Workbook

1 4 /

ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ

ፋይዳ ለሌላቸው ነገሮች ራሳቸውን አሳልፈው መስጠታቸው ነው። የሚኖሩትም በመቶ ዓመታት ውስጥ ለማይኖሩ ወይም ምንም ለማይጠቅሙ ጊዜያዊ ተድላዎች፣ ቁሳዊ ንብረቶች እና ግላዊ ስኬቶች ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ በአግባቡ ለመኖር ትልቅ ፍቅር ብቻ ሳይሆን ፍላጎቶቻችንን እና መሻቶቻችንን ቀጣይነት ወዳላቸውና አስፈላጊ ወደሆኑ ነገሮች መምራት ይኖርብናል። በእግዚአብሔር ቃል መሰረት በእርግጥ አስፈላጊ ነገሮች በጣም ጥቂት ነገሮች ናቸው፤ ስለዚህ ሊፈለጉ የሚገባቸው ጥቂት ነገሮች ብቻ ናቸው። በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ከተነገሩት በጣም ጠቃሚ ሀብቶች አንዱ የእግዚአብሔር ቃል ራሱ ነው። እግዚአብሔር ቅዱስ ቃሉ በሙሉ ሃይላችንና ባልተቋረጠ ጥረት የራሳችን ልናደርገው የሚገባን ውድ ሀብት እንደሆነ ገልጿል። በምድር ላይ እንደ እግዚአብሔር ቃል ጸንቶ የሚኖር ምንም ነገር የለም፤ እርሱ የሚሰጠውን ጥበብ፣ ማስተዋል፣ ተስፋ እና ደስታም የሚሰጠን ምንም ነገር የለም። የእግዚአብሔር ቃል ለዓይን ብርሃንን፣ ለልብ ደስታን፣ ለመንፈስ ጥበብን፣ እና ለሰው ሕይወት ተስፋን የሚሰጥ እጅግ ታላቅ ሀብት ነው። እዚህ ላይ መዝሙረኛው የእግዚአብሔር ሕያው ቃል ስላለው አስደናቂ ተፈላጊነት በግልጽ ተናግሯል። ልጁን፣ እቅዱን እና ተስፋችንን በሚመለከት እንደ እግዚአብሔር ቃል ያለን ወይም ልንይዘው የምንችለው ምንም ነገር የለም። እርሱን በመጠበቅ እንተጋ ዘንድ ያስጠነቅቀናል፥ በቃሉም ላይ በመጣበቅ ታላቅ ብድራት አለን። ገንዘብን፣ ወይም ተድላን፣ ወይም ነፃ ጊዜን፣ ወይም ታላቅ ዕድልን በምትፈልገው ልክ የእግዚአብሔርን ቃል እየፈለግህ ነውን? በዚህ ዓለም ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል ጥልቅ እውቀት ያህል ዋጋ ያለው ወይም ጠቃሚ ነገር የለም። ዛሬ የልብህ መሻት ያለው የት ነው? የኒቂያን የእምነት መግለጫ (በአባሪው ውስጥ ይገኛል) ካነበብክ እና/ወይም ከዘመርክ በኋላ የሚከተለውን ጸሎት ጸልይ፥ እኛና መላው አለም የእርሱን ድንቅ ስራዎች እናስተውል ዘንድ የአዳኛችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጥሪ በፍጥነት እንድንመልስና ለሰዎች ሁሉ የማዳኑን የምስራች እንድናውጅ ጌታ ሆይ ጸጋን ስጠን፤ እርሱም ከአንተና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የሚኖርና የሚነግስ አንድ አምላክ ከዘላለም እስከ ዘላለም። አሜን!

1

የኒቂያ የእምነት መግለጫ እና ጸሎት

~ Martin Luther. Devotions and Prayers of Martin Luther. Trans. Andrew Kosten. Grand Rapids: Baker Book House, 1965. p 77.

Made with FlippingBook - Online magazine maker