Conversion and Calling, Amharic Student Workbook

/ 2 3

ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ

የእግዚአብሔርን ቃል የመፍጠር ኃይልን በሚመለከት ቪዲዮው ያነሳቸውን እነዚህን እና ሌሎች ጥያቄዎችን ለመመለስ ያለህን ያህል ጊዜ ውሰድ። መልሶችህ ግልጽ እና አጭር ይሁኑ፣ አስፈላጊ ሲሆን ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ አስደግፍ! 1. ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር ቃል መሆናቸውን የሚናገሩት በምን መንገድ ነው? ቅዱሳት መጻሕፍት በእግዚአብሔር እስትንፋስ የተጻፉ ናቸው ማለት ምን ማለት ነው? 2. የእግዚአብሔር ቃል “ህያው ሆኖ ለዘላለም ይኖራል” የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ትርጉም ምንድን ነው? 3. እግዚአብሔር በጸሐፊዎቹ ብቻ ሳይወስን ወይም በህልም ሳያሳያቸው እና አእምሮአቸውን ሳይቆጣጠር እንዴት የእግዚአብሔርን ቃል አነሳስቶ ሊሆን ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ ደራሲዎቹ “በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው” ሲል ምን ማለቱ ነው? 4. አንድ አማኝ ቅዱሳት መጻሕፍት ፍጹም እምነት የሚጣልባቸውና እውነተኛ መሆናቸውን ማወቅ የሚችለው እንዴት ነው? 5. የእግዚአብሔር ቃል በቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የተከበረና የተመሰገነ ነው የሚለው አንድምታው ምንድን ነው? 6. በአጽናፈ ዓለም አፈጣጠር እና በእግዚአብሔር ቃል መካከል ያለው ግንኙነት ምንድን ነው? “ኤክስ ኒሂሎ” የሚለው የላቲን ሐረግ ትርጉም ምንድን ነው እና ይህ ጽንሰ-ሐሳብ ከእግዚአብሔር የፍጥረት ሃሳብ ጋር እንዴት ይዛመዳል? 7. ቅዱሳት መጻሕፍት ስለ እግዚአብሔር ፍጥረት አጽናፈ አለሙ እና ሎጎስ ወይም የእግዚአብሔር ቃል (ማለትም ኢየሱስ ክርስቶስ) ግንኙነት ምን ይላሉ? 8. “አጠቃላይ መገለጥ” ማለት ምን ማለት ነው? እግዚአብሔር በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ሁሉ ራሱን የገለጠባቸው ልዩ መንገዶች የትኞቹ ናቸው? 9. “ልዩ መገለጥ?” የሚለው ሐረግ ትርጉም ምንድን ነው? እግዚአብሔር ራሱን ለተወሰኑ ሰዎች በተወሰነ ጊዜና ቦታ የገለጠባቸው ልዩ መንገዶች የትኞቹ ናቸው? 10. በ“ፕሮፖዚሽናል” እና “በግል” የእግዚአብሔር ቃል መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? እንዴት ይዛመዳሉ? አንዱ ከሌላው ይቀድማል (ማለትም የበለጠ አስፈላጊ ነው)? አብራራ።

መሸጋገሪያ 1

የተማሪው ጥያቄዎች እና ምላሾች

1

Made with FlippingBook - Online magazine maker