Conversion and Calling, Amharic Student Workbook
/ 4 1
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
የሚወቅሰው ቃል
ት ም ህ ር ት 2
የትምህርቱ ዓላማዎች
ኃያል በሆነው በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን!
በዚህ ትምህርት ውስጥ ያሉትን ጽሑፎች ካነበብክ፣ ካጠናህ እና ከተወያየህበት እና ከተገበርከው በኋላ፣ እውነቱን ከቅዱሳት መጻሕፍት አንጻር መግለጽ እና መከላከል ትችላለህ፡- • የእግዚአብሔር ቃል ኃጢአትን፣ ጽድቅን እና ፍርድን የሚወቅስ ቃል ነው። • የእግዚአብሔርን አካልና ሥራ ከምንረዳባቸው መንገዶች ሁሉ፣ ኃጢአትን እንድንረዳ የሚያስችለን በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር ቃል ነው - በሥፋቱ እና በባህሪው የሚበላሽ ነው። • የእግዚአብሔር ህግ በኃጢአታችን ይወቅሰናል፣ ይህም በድርጊታችን እና በዓሳባችን እና በእግዚአብሔር ቅዱስ ፍላጎቶች መካከል ያለውን ርቀት ያሳያል። • የእግዚአብሔር ቃል ስለ ጽድቅ ይወቅሳል፣ የእግዚአብሔርን ህግ ለመጠበቅ ብቃት እንደሌለን ያሳያል፤ የእግዚአብሔርን ፅድቅ በእምነት በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ ይገልጣል። • የእግዚአብሔር ቃል ፍርድን በሚመለከት ይወቅሳል፣ በሁሉም ቦታ ያሉ ፍጥረታትን ሁሉ ተጠያቂ ለማድረግ ያለውን ሃሳብ እና በእስራኤል እና በአህዛብ፣ በቤተክርስቲያን፣ በሰይጣን እና በመላእክቱ እና በክፉ ሙታን ሁሉ ላይ ሊመጣ ያለውን ፍርድ ያሳያል። • የእግዚአብሔር ቃል የእውነትን ተፈጥሮ፣ ማለትም፣ ስለ እግዚአብሔር፣ በዓለም ላይ ስላለው ስራ እና የሰው ልጅ እጣ ፈንታ እና አላማን በሚመለከት ትክክለኛ የሆነውን እምነትን ያመጣል። • የእግዚአብሔር ቃል ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት ዋና ርዕሰ ጉዳይ ማለትም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነት እና ሥራ መገለጥ እምነትን ያመጣል። • የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔርን መገለጥ አጠቃላይ ዳራ ማለትም የመንግስቱን እቅድ መገለጥ በተመለከተ እምነትን ያመጣል። • የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔርን አካል እና እቅድ የመወከል እና የመናገር ተግባር በተሰጣቸው በእግዚአብሔር በተመረጡት መልእክተኞች፣ ነቢያት እና ሐዋርያት ታማኝነት እምነትን ያመጣል።
2
Made with FlippingBook - Online magazine maker