Conversion and Calling, Amharic Student Workbook

/ 4 3

ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ

ማስታወሻዎችህን አስቀምጥ ፣ ሀሳብህን ሰብስበህ የትምህርት 1ን ፈተና ውሰድ ፣ የሚለውጠው ቃል

አጭር ፈተና

ከሌላ ሰው ጋር በመሆን ላለፈው ክፍለ ጊዜ የተመደበውን የቃል ጥናት ክፍል ፃፍ ወይም በቃልህ አንብብ: 2 ጴጥ 1: 19 - 21

የቃል ጥናት ክፍል ቅኝት

ባለፈው ሳምንት ለተሰጠው የንባብ የቤት ስራ መምህርህ የሚጠብቅብህን ዋና ዋና ነጥቦችና ማጠቃለያ አቅርብ (ንባብ ማጠናቀቂያ ገጽ)።

የቤት ስራ ማስረከቢያ

እውቂያ

2

እውነተኛው ሃይማኖት ይጸናልን? በአካባቢው በሚገኝ ጁኒየር ኮሌጅ ውስጥ በፍልስፍና ትምህርት ክፍል ውስጥ የሚገኘው ከቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች አንዱ “ባህላዊ አንጻራዊነት” የሚለው ሐሳብ አጋጥሞታል። ይህ ሃሳብ የሚያመለክተው ሁሉም ባህሎች እኩል መሆናቸውን ነው፤ በመሆኑም ሁሉም የተለያዩ የእምነት ስርዓቶቻቸው, ሃይማኖታዊ አስተሳሰቦቻቸው እና የሥነ-ምግባር ደንቦች እኩል ናቸው። ኢየሱስ ክርስቶስ ከሃይማኖታዊ ሥርዓቶችና አስተሳሰቦች ሁሉ በላይ በሆነ መንገድ ልዩ እና ቀዳሚ ነው ብሎ የሚያምነው ይህ የቤተ ክርስቲያን መሪ ይህ ሃሳብ አስጨንቆታል። ስለ “ባህላዊ አንጻራዊነት” ይህን የተለየ አመለካከት እንዴት ሊረዳው ይገባል? የትኞቹ መዝሙሮች ናቸው “የጽዮን መዝሙሮች”? ወጣት ክርስቲያኖች ምን ዓይነት ሙዚቃ ማዳመጥ እንዳለባቸው በሚመለከት በወጣቱ ቡድን አባላት መካከል ከባድ ክርክር እየተፈጠረ ነው። ይህ ሁሉ የጀመረው ከታዳጊዎቹ አንዱ ከሚወዳቸው ራፕ አርቲስቶች አንዱን በሲዲ ማጫወቻ ውስጥ ለማጫወት ሲያስገባና አንዳንድ ልጆች አርቲስቱ የሚጠቅሳቸውን አይነት ነገሮች በመቃወማቸው ነው። ሙዚቃውን ያመጣው ወጣት እግዚአብሔርን በጣም የሚወድ ክርስቲያንና እያደገ ያለ ታዳጊ ሲሆን ለጠፉ ጓደኞቹ ጥሩ ምስክር እንዲሆን በዓለም ላይ ምን እየተካሄደ እንዳለ መረዳት አስፈላጊ እንደሆነ ቢያምንም በተፈጠረው ውዝግብ ተጎድቷል። ሌሎች ደግሞ ይህ ዓይነቱ ሙዚቃ እግዚአብሔራዊ አይደለም ብለው ይከራከራሉ፤ ስለ ሁከት፣ ስቃይ እና ትግል የሚናገር በመሆኑ ብርታትን የሚሰጥ ሳይሆን ተስፋ የሚያስቆጥ ነው ብለው ያምናሉ። ሁለቱም ወገኖች ስለ ጉዳዩ አስፈላጊነት እና ስለ እውነታው ትግበራ እኩል ያመኑ ይመስላል። በሙዚቃ ጉዳይ ላይ በነዚህ ተቀናቃኝ ወገኖች መካከል የተፈጠረውን ይህን አለመግባባት ለመፍታት ከሁሉ የተሻለው መንገድ ምንድነው?

1

2

Made with FlippingBook - Online magazine maker