Conversion and Calling, Amharic Student Workbook
/ 6 3
ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ
ይህ ትምህርት በእግዚአብሔር ቃል እና በእግዚአብሔር መንፈስ መካከል ያለውን ቀጥተኛ ግንኙነት አጽንዖት ሰጥቷል። የእግዚአብሔር ቃል በህይወታችን ሙሉ ስልጣን እንዲኖረው በውስጣችን ሊኖር የሚችለውን ኃጢአት፣ ትዕቢት፣ ስንፍና እና ጠማምነት አስወግደን እግዚአብሔርን በመንፈሱ ቃሉን እንዲያስተምረን ልንጠይቀው ይገባናል። ይህም ብርቱ ቃል የምንጸልይላቸውን እና የምናገለግላቸውን ሰዎች ህይወት እንዲነካ መጸለይ ይኖርብናል። የእግዚአብሔር ቃል የሰውን ልብ ለማቅለጥም ሆነ ከአጥፊ መንገዳቸው ወደ ጌታ ለመመለስ ያለውን ሃይል በፍፁም አቅልለህ አትመልከት። እግዚአብሔር ስለ መነቃቃት፣ መጽናትና ብርቱ ኃይሉ የበለጠ እምነት እንዲሰጥህ ጸልይ። የእግዚአብሔርን ቃል የማሳመን ኃይል ስንለማመድ ብቻ ነው የሌሎችን ልብ የመፈወስ፣ የመለወጥ እና የማብራት ችሎታውን የምንረዳው።
ምክር እና ጸሎት
ምደባዎች
ዮሐ 16፥7-11
የቃል ጥናት ጥቅስ
2
ለክፍል ለመዘጋጀትና የሚቀጥለውን ሳምንት የምንባብ ምደባ ለማግኘት www.tumi.org/books ን ጎብኝ ወይም መምህርህን ጠይቅ።
የንባብ የቤት ስራ
በቀጣዩ ክፍለ ጊዜ ስለዚህኛው ሳምንት የትምህርት ይዘት (የቪዲዮ ትምህርቱን ይዘትና መመሪያውን) አጭር ፈተና ይሰጥሃል፡፡ የትምህርቱን ዋና ዋና ሃሳቦች በጥናትህ መሸፈንህን አረጋግጥ፡፡ እንዲሁም፣ ስለ ሚኒስትሪ ፕሮጀክትህ ባህሪ ማሰብ የምትጀምርበት እና ለትርጓሜ ፕሮጄክትህ የትኛውን የቅዱሳት መጻሕፍት ክፍል እንደምትመርጥ ለመወሰን ጊዜው አሁን ነው። ይህን ለመወሰን አትዘግይ፥ ቶሎ በመረጥክ መጠን ለመዘጋጀት በቂ ጊዜ ይኖርሃል! እባክህ እነዚህን ማጠቃለያዎች በሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ይዘሃቸው ቅረብ፡፡ (እባክህ በዚህ ትምህርት መጨረሻ የሚገኘውን “የንባብ ማጠናቀቂያ ገጽ” ተመልከት፡፡) ቀጣዩ ጥናታችን፣ የመለወጥ እና የጥሪ ሞጁል ትምህርት ሶስት፣ “የሚለውጥ ቃል” በሚል ርእስ ስር ነው። በሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ወደ ሚታኖያ፣ (ከኃጢአት ንስሐ መግባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እግዚአብሔር መመለስ) እና ወደ ፒስቲስ (እግዚአብሔር አማኙን ከኃጢያት ቅጣት፣ ኃይል እና መገኘት ወደሚያድንበት እምነት) የሚመራ ቃል እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን። ይህ የሚለወጠው ቃል በአማኙ ህይወት ውስጥ እግዚአብሔርን እንደ ሰማያዊ አባት ማወቅን፣ አዲስ የጸሎት ልምድን፣ የእግዚአብሔርን ቃል ግልጽነት እና የኢየሱስን ድምጽ ውስጣዊ ምሪት ለመከተል ፈቃደኛነትን ጨምሮ አዲስ የመንፈሳዊ ህይወት ውስጣዊ ምልክቶችን ይፈጥራል። ከእግዚአብሔር ህዝብ ጋር መታወቅን፣ አዲስ የክርስቶስን ባህሪ እና የአኗኗር ዘይቤን ማሳየት፣ ለሌሎች አማኞች ያለን ፍቅር እና የጠፉትን በክርስቶስ አሸንፈው የማየት ፍላጎትን ጨምሮ ውጫዊ ምልክቶች እንዴት እንደሚታዩበትም በተጨማሪ እንመለከታለን።
ሌሎች የቤት ስራዎች
ለቀጣዩ ትምህርት መዘጋጀት
Made with FlippingBook - Online magazine maker