Conversion and Calling, Amharic Student Workbook

/ 6 7

ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ

የሚለውጠው ቃል

ት ም ህ ር ት 3

የትምህርቱ አላማዎች

ኃያል በሆነው በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን!

የዚህን ሞጁል (ትምህርት) መጽሐፍ ጥናትህን ካጠናቀቅህ በኋላ የሚከተሉትን ዕውነታዎች መረዳት፣ ማብራራት እና ለተረዳኸውም እውነት መቆም ትችላለህ:- • የሚለወጠው ቃል በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ከሚገኘው የመዳን የምስራች ጋር ተመሳሳይ ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የሚለውጥ ቃል ነው። • ይህ ብርቱ ቃል ወደ ሜታኖያ ይመራናል፥ ይህም ማለት ከኃጢአት ንስሐ መግባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው። • ይህ ቃል ወደ ንስሐ (ሜታኖያ) ድኅነት የሚያደርስና በአማኙ ላይ እምነትን (ፒስቲስ) ለማምጣት በተመሳሳይ ኃይል የሚሰራ ነው። ይህ እምነት አማኙን ከኃጢአት ቅጣት፣ ኃይል እና ህይወት ያድናል። • የእግዚአብሔር ቃል አንድ ጊዜ በንስሐ እና በእምነት መስራት ከጀመረ የእግዚአብሔርን ይቅርታ እና የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በአማኙ ሕይወት ውስጥ የሚያረጋግጡ ምልክቶችን ይፈጥራል። • አማኙ በውስጣዊ ማንነቱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔርን እንደ ሰማያዊ አባት ማወቅን፣ አዲስ የጸሎት ህይወትን መለማመድን፣ የእግዚአብሔርን ቃል መረዳትን እና የኢየሱስን ድምጽ ምሪት የመከተልን ጨምሮ የአዲሱን ህይወት ምልክቶችን ያሳያል። • በውጫዊውና በሚዛመደው መንገድ ደግሞ የሚለወጠው ቃል ራስን ከእግዚአብሔር ህዝብ ጋር መለየትን፣ አዲስ የክርስቶስን ባህሪ እና የአኗኗር ዘይቤን ማሳየትን፣ ለሌሎች አማኞች ፍቅር እና የጠፉትን ለክርስቶስ የመማረክን መሻት ጨምሮ ውጫዊ ምልክቶችን ያሳያል። ብቻ እንደገና መወለድ አለብህ ዮሐንስ 3፡1-21 አንብብ። ከምንማርባቸውና ከምንደሰትባቸው የኢየሱስ የመንግሥቱ አስደናቂ ትምህርቶች መካከል ምናልባት ከላይ የመወለድንና ዳግመኛ የመወለድን አስፈላጊነት በተመለከተ እንዳስተማረው የሚያስተምረን የለም። የመወለድ ልምምድ ከተፈጥሮ በላይ የሆነ እይታን ይሰጠናል፤ ለትንሽ ህይወት በአለም ውስጥ ለመወለድ፣ ከጓደኞች እና ቤተሰብ ጋር ይህን አዲስ ህይወት ወደ አለም በደስታ ሲቀበሉ እጅግ አስደናቂ እና አስደሳች ነገር ነው። ኢየሱስ በእርሱ በማመን ያለውን የአዲሱን ሕይወት እውነታ ለማስረዳት የአዲሱን ልደት ምሳሌ ተጠቅሟል። የልደት ዘይቤው ስለ አዲስ ዘር ይናገራል፥ ሙሉ በሙሉ አዲስ ስለሆነ የወላጅ ማንነት እና የህይወት ምንጭ ይናገራል። ዳግመኛ መወለድ ማለት ሙሉ ለሙሉ አዳዲስ የህይወት እድሎችን፣ አዲስ የእድገት አቅጣጫዎችን እና አዲስ የለውጥ እድሎችን ማጤን ነው። ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት ዳግመኛ መወለድ፣

3

ጥሞና

Made with FlippingBook - Online magazine maker