Conversion and Calling, Amharic Student Workbook

/ 7 9

ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ

8. ንስሐና እምነትን አማኙ የእግዚአብሔርን ሞገስና ይቅርታ ለማግኘት እንደሚሠራው ነገር ፈጽሞ ማሰብ የሌለበት ለምንድን ነው?

የሚለውጠው ቃል ክፍል 2

ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ

በዚህ ክፍል ውስጥ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል፣ ይህ የእግዚአብሔር ቃል፣ የእግዚአብሔርን ይቅርታ እና መንፈስ ቅዱስ በአማኙ ሕይወት ውስጥ ያለውን ኃይል የሚያረጋግጡ ምልክቶችን እንዴት እንደሚያመጣ ለማሳየት ተስፋ እናደርጋለን። የሚለውጠው ቃል አዲሱን የተለወጠውን በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን ለውጥ ለማሳየት እንደ ማስረጃ የሚያገለግሉ የህይወት ምልክቶችን ይፈጥራል። እነዚህም እግዚአብሔርን እንደ ሰማያዊ አባታቸው ማወቅን፣ አዲስ የጸሎት ልምምድን፣ የእግዚአብሔርን ቃል ግልጽነት እና የኢየሱስን ድምፅ ውስጣዊ ምሪት ለመከተል ፈቃደኛ መሆንን ያካትታሉ። በተመሳሳይ መልኩ ውጫዊ ምልክቶችም በኢየሱስ ወንጌል አማኝ ይገለጣሉ፣ ከእነዚህም መካከል ከእግዚአብሔር ሰዎች ጋር መተዋወቅ፣ አዲስ የክርስቶስን ባህሪ እና የአኗኗር ዘይቤን ማሳየት እና ለሌሎች አማኞች ፍቅር ማሳየት፣ እንዲሁም የጠፉትን የመፈለግ ፍላጎት ማሳየትን ይጨምራል። የዚህ የሚለውጠው ቃል ሁለተኛ ክፍል አላማችን የሚከተሉትን እውነቶች እንድትረዳ፣ እንድታነብ እና እንድትወያይ ለማድረግ ነው። • የሚለውጠው ቃል እምቅ ኃይል ነው፥ የእግዚአብሔርን ሕይወት በክርስቲያን ልብ እና ሕይወት ውስጥ የሚደግፍና በውስጣዊም ሆነ በውጫዊ የመንፈስ አሰራር ምልክቶች (ማስረጃዎች) የሚታይ ነው። • ይህ የሚለውጠው፣ ሕይወትን የሚሰጠው ቃል የመንፈስን ሥራ ውስጣዊ ማረጋገጫ የሚሰጡ ውስጣዊ ምልክቶችን ይፈጥራል። እነዚህ ምልክቶች እግዚአብሔርን እንደ አባት ማወቅን፣ ወደ እግዚአብሔር የመጸለይ አዲስ ልምምድ፣ ግልጽነትና የእግዚአብሔር ቃል ረሃብ፣ እና የኢየሱስን ድምጽ ምሪት እንደ እረኛ ለመከተል ፈቃደኛ መሆንን ያካትታሉ። • በተመሳሳይ መልኩ ውጫዊ ምልክቶችም በኢየሱስ ወንጌል አማኝ ይገለጣሉ፣ ከእነዚህም መካከል ከእግዚአብሔር ሰዎች ጋር መተዋወቅ፣ አዲስ የክርስቶስን ባህሪ እና የአኗኗር ዘይቤን ማሳየት እና ለሌሎች አማኞች ፍቅር ማሳየት፣ እንዲሁም የጠፉትን የመፈለግ ፍላጎት ማሳየትን ይጨምራል።

የክፍል 2 ማጠቃለያ

3

Made with FlippingBook - Online magazine maker