Conversion and Calling, Amharic Student Workbook

/ 9 3

ለ ው ጥ እ ና ጥ ሪ

የሚጠራው ቃል

ት ም ህ ር ት 4

የትምህርቱ ዓላማዎች

ኃያል በሆነው በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን!

የዚህን ሞጁል (ትምህርት) መጽሐፍ ካነበብክ፣ ካጠናህ፣ ውይይት ካደረግህና ወደ ተግባር ከቀየርክ በኋላ የሚከተሉትን ማድረግ ትችላለህ:- • ወደ ድነት እና መለወጥ የሚመራን ያው ቃል የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ሆነን ለፈቃዱ በመታዘዝ እንድንኖር ይጠራናል። • ወደ ደቀመዝሙርነት የሚጠራን ይህ ቃል እርሱን ከሁሉ በላይ ጌታ አድርገን እንድናገለግለውና እንደ ጋብቻ እና ቤተሰብን ጨምሮ ከሌሎች ፍቅሮች ሁሉ በላይ እርሱን እንድንወደውና ራሳችንን ለኢየሱስ እንድናቀርብ ይጠብቅብናል። • ጥሪው በዚህ ዓለም ውስጥ እንደ እንግዶችና መጻተኞች፥ በዓለምም ውስጥ የእግዚአብሔር መንግሥት ዜጎች ሆነው እንደሚሰሩ የኢየሱስ ተወካዮች በክርስቶስ ያለውን አዲሱን ማንነታችንን እንድንቀበል ይጠይቀናል። • የደቀመዝሙርነት አኗኗር የሚገለጠው ለክብሩ የመስዋዕትነትን ኑሮ እንድንኖር ለቀረበልን ጥሪ በጎ ምላሽ ስንሰጥ ነው። የክርስቶስ ባሪያዎች እንደመሆናችን መጠን እርሱ እንደመራን እርሱን የሚያከብረውንና ፈቃዱ የሆነውን ሁሉ ማድረግ ይኖርብናል። • በእግዚአብሔር ህዝብ (ላኦስ) ውስጥ እንደከበረ የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባላት በማህበረሰብ ውስጥ እንድንኖር እና እንድንሰራ ተጠርተናል። • የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የተጠራው በኢየሱስ ክርስቶስ ነፃነት ውስጥ እንዲኖር፣ ነፃነቱን ታላቁን ትእዛዝ ለመፈጸም እንደ እድል ለመጠቀም እና ሌሎችን ለክርስቶስ ለመማረክ ግልጽ ምስክርነት ለመስጠት ነው። • ወደ ደቀመዝሙርነት፣ ማህበረሰብ እና ነፃነት የሚጠራው ቃል ወደ ሚሽንም ይጠራናል። እንደ እግዚአብሔር መንግሥት ወኪሎች፣ ታላቁን ተልዕኮ እንድንፈጽም፣ ከመንፈሳዊ ጠላታችን ዲያብሎስ ጋር እንድንዋጋ እና የመንግሥቱን ሕይወት በፍቅራችን እና በበጎ ሥራዎቻችን እንድናሳይ ተጠርተናል።

4

Made with FlippingBook - Online magazine maker