Foundations for Christian Mission, Amharic Mentor Guide
1 2 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ምዘና
ይህ የትርጓሜ ጥናት (ኤክሴጄቲካል ፕሮጀክት) የ45 ነጥቦች ዋጋ ያለው ሲሆን ከጠቅላላው የዚህ ኮርስ ውጤት 15% ይይዛል፡፡ ስለዚህ በተቻለህ መጠን ስራህን የላቀና አስተማሪ አድርገሀ ለማቅረብ ሞክር፡፡
የሚኒስትሪ ፕሮጀክት የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤” (ዕብራውያን 4፡12)፡፡ ሐዋሪያው ያዕቆብ ሰሚዎች ብቻ ሳይሆን አድራጊዎችም ጭምር እንድንሆን አጽንኦት ሰጥቶ ይናገራል፡፡ ቃሉን በተግባር ላይ እንድናውለውም ይመክረናል፡፡ ይህን ልምምድ መዘንጋት የተፈጥሮ ፊታችንን በመስታውት ውስጥ ተመልክተን ወዲያው ማንነታችንን ከመርሳት ጋር ያመሳስለዋል፡፡ በማንኛውም ሁኔታ የእግዚአብሔርን ቃል የሚያደርግ ሰው በነገር ሁሉ ይባረካል (ያዕቆብ 1፡22-25)፡፡ እኛም መሻታችን የምንቀስመውን ትምህርት በግል ህይወትህ፣ በአገልግሎትህና በቤተክርስቲያንህ ውስት ካሉ ተጨባጭ ሁኔታዎችና ፍላጎቶች ጋር በማዛመድ በተግባር ስታውለው መመልከት ነው፡፡ በመሆኑም የዚህ ትምህርት (ኮርስ) ዋና ዓላማ ከዚህ ኮርስ የተማርካቸውን ነገሮች ከሌሎች ጋር ልትከፋፈልበት የምትችልበት የሚኒስትሪ ፕሮጀክት መቅረጽ እንድትችል ነው፡፡ የዚህን ጥናት መመዘኛዎች ለማሟላት ብዙ አማራጮች አሉህ፡፡ ከሰንበት ትምህርት ቤት የወጣቶች ወይም አዋቂዎች የመጽሀፍ ቅዱስ ጥናት ወይም ማንኛውም አገልግሎት ዘርፍ ላይ ተመስርተህ አጠር ያለ ጥናት ማካሄድ ትችላለህ፡፡ እዚህ ጋር የግድ ማድረግ የሚኖርብህ ነገር ቢኖር ከነበረህ የትምህርት ክፍለ ጊዜ የተማርካቸውን ነጥቦች ከአድማጭህ ጋር መወያየት ነው፡፡ (በእርግጥ የምታካፍላቸውን ነጥቦች ከትርጓሜ ጥናትህም መውሰድ ትችላለህ፡፡) በእያንዳንዱ የፕሮጀክት ስራህ ነጻነትህን ተጠቅመህ ሳቢና ግልፅ ለማድረግ ሞክር፡፡ በዚህ ኮርስ መጀመሪያ ሀሳብህን የምታካፍልበትን ሁኔታ (አውድ) በመወሰን ለመምህርህ ማሳወቅ ይኖርብሃል፡፡ ለዚህም ፕሮጀክትህ ይህን ዝርዝርና ቅደም ተከተል በመጠቀም ሊዘጋጅ ይችላል፡፡
ዓላማ
እቅድ እና ማጠቃለያ
1. ሙሉ ስም 2. የት እና ከማን ጋር የመከፋፈል ጊዜ እንደነበረህ 3. ስለነበራቹ ጊዜ ምን እንደተሰማህና ስለነሱ ምላሽ አጠር ያለ ማብራሪያ 4. ከነበራቹ ጊዜ ስለተማርከው ነገር
ምዘና
ይህ የሚኒስትሪ ፕሮጀክት የ30 ነጥቦች ዋጋ ያለው ሲሆን ከጠቅላላው የዚህ ኮርስ ውጤት 10% ይይዛል፡፡ ስለዚህ ሃሳብህን በልበ ሙሉነት ማካፈልህንና ግልጽ የሆነ ማብራሪያ ማቅረብህን እርግጠኛ መሆን ይኖርብሃል፡፡
Made with FlippingBook flipbook maker