Foundations for Christian Mission, Amharic Mentor Guide
/ 1 4 1
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
CONNECTION
ይህ ትምህርት በከተማና ለሚሽን ባለው ስትራቴጂያዊ ሚና ላይ ያተኮረ ነው፡፡ እግዚአብሔር ከተማን እንደ ተሐድሶና ደህንነት ምልክት መምረጡና ከተማን በዘመናዊ አለም ወስጥ ባለው ጠቀሜታ ምክንያት ከተማ በክርስትና አገልግሎትና በመንግስቱ መስፋፋት ውስጥ ቀዳሚውን ስፍራ ይዞ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ በቀረቡት ጽንሰ ሀሳቦች ውስጥ ያሉትን ማእከላዊ እውነቶች ለመቃኘት ጊዜ ውሰድ:- ³ የከተማ ጽንሰ ሃሳብ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ማዕከላዊ ሃሳብ ሲሆን ስለጥንታዊው የከተማ ባህሪያት ጠቅለል ያለ ዕይታ ይሰጠናል፡፡ በጥንታዊው አለም ያሉ ከተሞች ከመንደሮች የተለዩ በመሆናቸው በግንቦች የተቀጠሩ የቤቶችና የህንጻዎች ስብስብ ቢሆኑም ለዘመናቸው የሚመጥኑና አስገራሚዎቹ ነበሩ፤ አንዳንዶቹ ከተሞች ደግሞ ለጥበቃና ለአቅርቦት በሌሎች ከተሞች ላይ ጥገኞች ነበሩ፡፡ በጥንታዊው አለም የነበሩት ከተሞች በአንጻራዊነት አነስተኛ ንድፍ የሌላቸው፤ በወፍራም ግንቦችና ከፍ ባሉ ማማዎች የተጠናከሩና የመንግስትና የባለስልጣናት መቀማመጫዎች ነበሩ፡፡ ³ በቅዱሳት መጻሕፍት ከተዘረዘሩት የከተማመንፋሳዊ ትርጉም አንጻር ከተሞች ከሰው አመጽና ምንዝር (ሄኖክ፣ የቃየን ከተማ)፣ ከነጻነትና እብሪት (በባቤል ግንብ እንደሆነው)፣ ክፋትና አምላክ አልባነት (እንደ ባቢሎን) ጋር የተዛመዱ ነበሩ፡፡ ከተሞች በኃጢአታቸው ምክንያት በእግዚአብሔር ይፈርድባቸው ነበር (ለምሳሌ ሰዶምና ገሞራ፣ ኢያሪኮና ነነዌ)፤ እንዲሁም በሐሰተኛ የደህንነትና የኃይል ስሜታቸው ይወገዙ ነበር (በተለይም ኢየሩሳሌም)፡፡ ³ እግዚአብሔር ከተማን እንደ መኖሪያውና የበረከት ስፍራው የወሰደበትን ምስል ስንመለከት ኢየሩሳሌምን ለራሱ መምረጡና በምድር ላይ ለምስጋና እንድትሆን መወሰኑን እንረዳለን፡፡ ከዚያም ባሻገር የአመጻን ምስል ወደ መሸጋገሪያ ምስል (ማለትም የመማጸኛ ከተሞች)፤ እና የራሱ ይቅር ባይነት እና በረከት ማወቂያ መለማመጃ ቦታ (ዮሐንስና የነነዌ ተሞክሮ) በማድረግ ውስጥ የእግዚአብሔር አሰራር ታይቷል፡፡ ³ ከእግዚአብሔር ምህረትና ቸርነት የተነሳ በፍርዱ ፊት ለሚመለሱና በቅጣቱ ፊት ምህረቱን ለሚሻ የትኛውም ከተማ እግዚአብሔር ተስፋን ሰጥቷል፡፡ ³ ዛሬ ባለው የሚሽን እንቅስቃሴ ውስጥ ኧርባን ሚሽን ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ የሚሆንባቸው ሶስት ወሳኝ ምክንያቶች አሉ፤ እነዚህም፡- ከተማ በአለም ውስጥ የተጽዕኖ፣ የሃይልና የመንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች መቀመጫ ናት፤ ለተጠቁ፣ ለተጨቆኑና ለድሆች መጠጊያ ናት፤ እንዲሁም ከተማ እንደመንፈሳዊ መዳረሻችና ርስታችን ይታያል፡፡ ³ የኢየሱስ አገልግሎት ራሱ እንዴት በከተማ ስራ ላይ የተመሰረተ መሆኑን እንመለከታለን፤ መንግስቱን የመስበክ ስራው ኢየሩሳሌም ውስጥ ነው፡፡ በተጨማሪም ክርስትና በአንድ ከተማ ውስጥ ተወልዶ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን በሮማ ግዛት ውስጥ በነበሩት ታላቅ ከተሞች (እንደ ደማስቆ፣ አንጾኪያ፣ ፊሊጵስዩስ፣ ተሰሎንቄ አቴንስና ሮም) ተስፋፍቷል፡፡ ሐዋሪያዊ አግልግሎትም (የጳውሎስን ጉዞዎችጨምሮ) በባህሪውከተማተኮር ነው፣ ከተሞች ወደ ታዛቁ የሮማ ግዛት መግቢያ በሮች ነበሩ፡፡ ³ ከተማ ለኢየሱስ እና ለደቀመዛሙርቱም አገልግሎት ያበረከተው ድርሻ ከፍ ያለ ነው፡፡
የዋና ዋና ጽንሰ ሃሳቦች ማጠቃለያ
3
Made with FlippingBook flipbook maker