Foundations for Christian Mission, Amharic Mentor Guide
1 4 6 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
የከተማ ጽንሰ ሃሳብ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ማዕከላዊ ሃሳብ ሲሆን ስለጥንታዊው የከተማ ባህሪያት ጠቅለል ያለ ዕይታ ይሰጠናል፡፡ በጥንታዊው አለም ያሉ ከተሞች ከመንደሮች የተለዩ በመሆናቸው በግንቦች የተቀጠሩ የቤቶችና የህንጻዎች ስብስብ ቢሆኑም ለዘመናቸው የሚመጥኑና አስገራሚዎቹ ነበሩ፤ አንዳንዶቹ ከተሞች ደግሞ ለጥበቃና ለአቅርቦት በሌሎች ከተሞች ላይ ጥገኞች ነበሩ፡፡ በጥንታዊው አለም የነበሩት ከተሞች በአንጻራዊነት አነስተኛ ንድፍ የሌላቸው፤ በወፍራም ግንቦችና ከፍ ባሉ ማማዎች የተጠናከሩና የመንግስትና የባለስልጣናት መቀማመጫዎች ነበሩ፡፡ በቅዱሳት መጻሕፍት ከተዘረዘሩት የከተማ መንፋሳዊ ትርጉም አንጻር ከተሞች ከሰው አመጽና ምንዝር (ሄኖክ፣ የቃየን ከተማ)፣ ከነጻነትና እብሪት (በባቤል ግንብ እንደሆነው)፣ ክፋትና አምላክ አልባነት (እንደ ባቢሎን) ጋር የተዛመዱ ነበሩ፡፡ ከተሞች በኃጢአታቸው ምክንያት በእግዚአብሔር ይፈርድባቸው ነበር (ለምሳሌ ሰዶምና ገሞራ፣ ኢያሪኮና ነነዌ)፤ እንዲሁም በሐሰተኛ የደህንነትና የኃይል ስሜታቸው ይወገዙ ነበር (በተለይም ኢየሩሳሌም)፡፡ እግዚአብሔር ከተማን እንደ መኖሪያውና የበረከት ስፍራው የወሰደበትን ምስል ስንመለከት ኢየሩሳሌምን ለራሱ መምረጡና በምድር ላይ ለምስጋና እንድትሆን መወሰኑን እንረዳለን፡፡ ከዚያም ባሻገር የአመጻን ምስል ወደ መሸጋገሪያ ምስል (ማለትም የመማጸኛ ከተሞች)፤ እና የራሱ ይቅር ባይነት እና በረከት ማወቂያ መለማመጃ ቦታ (ዮሐንስና የነነዌ ተሞክሮ) በማድረግ ውስጥ የእግዚአብሔር አሰራር ታይቷል፡፡ ከእግዚአብሔር ምህረትና ቸርነት የተነሳ በፍርዱ ፊት ለሚመለሱና በቅጣቱ ፊት ምህረቱን ለሚሻ የትኛውም ከተማ እግዚአብሔር ተስፋን ሰጥቷል፡፡ ዛሬ ባለው የሚሽን እንቅስቃሴ ውስጥ ኧርባን ሚሽን ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ የሚሆንባቸው ሶስት ወሳኝ ምክንያቶች አሉ፤ እነዚህም፡- ከተማ በአለም ውስጥ የተጽዕኖ፣ የሃይልና የመንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች መቀመጫ ናት፤ ለተጠቁ፣ ለተጨቆኑና ለድሆች መጠጊያ ናት፤ እንዲሁም ከተማ እንደመንፈሳዊ መዳረሻችና ርስታችን ይታያል፡፡ ከተማ ለኢየሱስ እና ለደቀመዛሙርቱም አገልግሎት ያበረከተው ድርሻ ከፍ ያለ ነው፡፡ የኢየሱስ አገልግሎት ራሱ እንዴት በከተማ ስራ ላይ የተመሰረተ መሆኑን እንመለከታለን፤ መንግስቱን የመስበክ ስራው ኢየሩሳሌም ውስጥ ነው፡፡ በተጨማሪም ክርስትና በአንድ ከተማ ውስጥ ተወልዶ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን በሮማ ግዛት ውስጥ በነበሩት ታላቅ ከተሞች (እንደ ደማስቆ፣ አንጾኪያ፣ ፊሊጵስዩስ፣ ተሰሎንቄ አቴንስና ሮም) ተስፋፍቷል፡፡ ሐዋሪያዊ አግልግሎትም (የጳውሎስን ጉዞዎች ጨምሮ) በባህሪው ከተማ ተኮር ነው፣ ከተሞች ወደ ታዛቁ የሮማ ግዛት መግቢያ በሮች ነበሩ፡፡ በኢየሱስና በሐዋርያት ዘመን በነበሩ ከተሞች ውስጥ የነበሩ ተመሳሳይ ችግሮች እና እድሎች አሁን ባሉት ዘመናዊ ከተሞች ውስጥም የመታየታቸው ዕውነታ ግልፅ ነው፡፡ እነዚህ ዘመናዊ ከተሞች በመጠን፣ በስፋትና በህዝብ ብዛትም ታላላቅ ናቸው፡፡ በመሆኑም እነዚህ ከተሞች የመንግስት፣ የትምህርት፣ የጤና-ክብካቤ፣ የመረጃ፣ የመዝናኛ፣ የንግድ፣ የኢንዱስትሪ፣ የህግ፣ የወታደራዊና የሃይማኖት ተቋማት በመሆን ያገለግላሉ፡፡ አንትሮፖሎጂስቶች ከተሞችን ከሚሰጡት አገልግሎት አንጻር በትኩረታቸውና በአይነታቸው ለይተው ያስቀምጣሉ፡፡ የባህል፣ የፖለቲካና የአስተዳደር፣ የንግድ፣ የኢንዱስትሪ፣ ታሪካዊ ወይም ዋና ከተማ በመባል ተከፍለዋል። እግዚአብሔር ለድሆች ስላለው ልብ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ በመነሳት በአሁን ወቅት ከተሞች ለተጠቁት፣ለተጨቆኑት እና ለድሆች እንዴት እንደ ሚስብ ኃይል እንደሚያገለግሉ ይታያል፡፡ ሌላው ደግሞ እግዚአብሔር ስለ ድሆች ግድ የሚለው ከሆነ አሜሪካ ውስጥ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃና በድህነት ስለሚሰቃዩት ከተሞች ግድ ይለዋል ማለት ነው ስለሚለው ክርክር ግንዛቤ እንጨብጣለን፡፡ ከተማ የመዳረሻችንና የርስታችን ምስል እና ምሳሌ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች ማጠቃለያ ይሰጡናል፡፡ የሚሽን ዋናው ግብ የአለምን ከተሞች የአማኞች ሁሉ እናት የሆነችውን አዲሲቷን ኢየሩሳሌምን እንዲሞሉ መማረክ ነው (የእግዚአብሔር የመጨረሻው
የትምህርቱን ንድፈ ሃሳብ በድጋሚ መጻፍ
3
Made with FlippingBook flipbook maker