Foundations for Christian Mission, Amharic Mentor Guide
/ 1 7 1
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ዘዳ. 15.4-5
V. በቃል ኪዳኑ ማህበረሰብ ውስጥ የእግዚአብሔር መመዘኛዎች: የእግዚአብሔርን ሻሎም በቃል ኪዳኑ ማህብረሰብ መካከል መግለጥ
“አምላክህም እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ ርስት አድርጎ በሰጠህ ምድር ላይ እግዚአብሔር በእውነት ይባርክሃልና አንተ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ፈጽመህ ብትሰማ፥ ታደርጋትም ዘንድ ዛሬ የማዝዝህን ይህችን ትእዛዝ ሁሉ ብትጠብቅ፥ በመካከልህ ድሀ አይኖርም።”
ድሆች በብሉይ ኪዳን ውስጥ: ማጠቃለያ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ጻድቃንን በቅዱሳዊ ሀብት እንደሚያገለግል ይናገራል(ምሳ112፡ 1-3)፡፡ምንም እንኳን የስራና የቁጠባ ጉዳይ ለግለሰቡና ለሀገር ያከው ጥቅም በግልጽ የታየ ቢሆንም እና እግዚአብሄርም ትእዛዛቱን የሚጠብቁትን እንደሚባርክ ቃል የገባ ቢሆንም(ዘዳ28፡1-14)በእስራኤል ታሪክ ውስጥ በየዘመናቱ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ድሆች ነበሩ፡፡ድህነታቸው የተፈጠረው በተፈጥሮ አደጋዎች፣በጠላት ወረራ፣ኃይለኛ በሆኑ ጎረቤቶች ጭቆና ወይም በአራጣ ምክንያት በተከሰተ ዝቅተኛ መኸር አማካኝነት ነው፡፡ሀብታም ሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎች ድሀ ወንድሞቻቸውን የመደገፍ ግዴታ ነበረባቸው(ዘዳ15፡ 1-11)፡፡በድህነት የመሰቃየት እድላቸው ከፍተኛ የሆኑት ወላጅ አልባዎች፣መበለቶችና መሬት አልባ መጻተኞች ነበሩ፡፡ብዙውን ጊዜ የጭቆና ሰለባዎች ቢሆኑም(ኤር 7፡6፣አሞጽ2፡6-7) ያህዌ ግን የእነርሱ ደጋፊ ነበረ(ዘፀ10፡17-19፣መዝ68፡5-6)፡፡ህጉ ለነዚህ ሰዎች ድጋፍ መደረግ እንዳለበት ያዛል(ዘዳ24፡19-22)፤ሌዋውያን መሬት ስለሌላቸው ከድሆች ጋር አብረው ተቆጥረዋል (ዘዳ14፡28-29)፡፡
~R. E. Nixon. “Poverty.” The New Bible Dictionary. D. R. W. Wood, ed. 3rd ed. (electronic ed.). Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 1996. p. 945.
4
ሀ. የእግዚአብሔር ህዝብ በዘፀአቱ ታሪካዊ ክስተት በተነገረው ልምምዳቸው መሰረት እግዚአብሔር ከድሆች ጋር መቆሙን ማንፀባረቅ አለባቸው ፡፡
ለ / ጌታን እና ትእዛዛቱን ስንከተል እግዚአብሔር ሰላሙን (ሻሎምን) ይገልጣል።
ማጠቃለያ
» የድህነትን ፅንሰ-ሀሳብ በሻሎም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መነፅር ወይም በአጠቃላይ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ማህበረሰብ በኩል መረዳት ይቻላል ፡፡ » እስራኤል ምንም እንኳን የእግዚአብሔርን ፍትህና ጽድቅ በማሳየት ታማኝነት የጎደላት ቢሆንም መጽሐፍ ቅዱስ የሚያሳየው እግዚአብሔር በችግራቸው ጊዜ ከድሆች ጎን መቆሙንና ሕዝቦቹም እርስ በርሳቸው በሚያደርጉት ግንኙነት ለአሕዛብ ብርሃን እንዲሆኑ ነው ፡፡
Made with FlippingBook flipbook maker