Foundations for Christian Mission, Amharic Mentor Guide

3 1 4 /

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

ሰዎችን ለነፃነት ፣ ለሙሉነት እና ለፍትህ ማብቃት (ቀጥሏል)

3. ሁ ለንተናዊ ሁን - የመጣውን ሁሉ ፡፡ (ሮሜ. 10.12) ማንም ሰው ወይም ቡድን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእምነት ወደ መንግሥቱ እንዳይገባ በየትኛውም መንገድ ቢሆን ሊከለክል አይገባም ፡፡ 4. ከ ባህል አንጻር ገለልተኛ ሁን -አንተ እራስህን ሁን፡፡ (ቆላ. 3.11) ወንጌል ማንኛውንም ሰው ወደ ኢየሱስ ለመምጣት ቅድመ ሁኔታ ሆኖ ባህላቸውን እንዲለውጡ የሚጠይቅ ነገር የለውም ፡፡ እንደነበሩት ሆነው ሊመጡ ይችላሉ ፡፡ 5. የ ምሽግ አስተሳሰብን ያስወግዱ ፡፡ (ሥራ 1.8) የሚሽን ዓላማ ባልዳነው ማህበረሰብ መካከል የማይደፈር ግንብን መፍጠር ሳይሆን የመንግሥቱን ታላቅ ኃይል እና የኢየሱስን ምስክርነት በዓለም ዙሪያ እስከሚገኙት ድንበሮች ድረስ ማስጀመር ነው ፡፡ 6. መ ቀዛቀዝን ለማስወገድ ወንጌልን መስበክህን ቀጥል፡፡ (ሮሜ. 1.16-17) የታላቁን ተልእኮ ራእይ ከግምት ውስጥ በማስገባት አድማሶችን መመልከትህን ቀጥል; ለክርስቶስ ጠንካራ የሆነ የምስክርነት ሁኔታን ፍጠር ፡፡ 7. የ ዘር ፣ የመደብ ፣ የፆታ እና የቋንቋ መሰናክሎችን አልፈህ ሂድ፡፡ (1 ቆሮ. 9.19-22) ከባህላዊው ቤተ-ክርስቲያን የባህል ክልል በጣም ርቀውወዳሉት ሰዎች የመንግሥቱን መልእክት ለማስተላለፍ አዳዲስ እና ተአማኒ መንገዶችን ለማግኘት በክርስቶስ ያለህን ነፃነትህን ተጠቀም ፡፡ 8. የ ተቀባዩን ባህል የበላይነት አክብር፡፡ (ሐዋ ሥራ 15.23-29) ኢየሱስን እንደ ጌታቸው የተቀበሉ ሰዎችን በቃላት ፣ በቋንቋ ፣ በባህሎች ፣ በስልቶች እና ልምዶች የእግዚአብሔር መንግሥት ራዕይን እና ሥነ ምግባር እንዲለውጣቸው ለመንፈስ ቅዱስ ፍቀድለት ፡፡ 9. ጥ ገኝነትን አስወግድ፡፡ (ኤፌ. 4፣11-16) እያደገ በሚሄደው ጉባኤ ላይ አላግባብ አትደገፍ ወይም ከመጠን በላይ አትሳሳ ፤ በአካባቢያቸው ውስጥ በትንሹ የክርስቲያን ማህበረሰብ መካከል የእግዚአብሔርን ሥራ ለመፈፀም የመንፈስ ቅዱስን ኃይል አቅልለህ አትመልከት ፡፡ 10. ስ ለ መባዛት አስብ ፡፡ (2 ጢሞ. 2.2 ፤ ፊልጵ. 1.18) በምትጀምሯቸው እያንዳንዱ እንቅስቃሴና ፕሮጀክት ውስጥ የወንጌል ተልዕኮህን ዘዴዎች እና ግቦች በተመለከተ አዕምሮህን በመክፍርት ሌሎች ተመሳሳይ ነገር እንዲያደርጉ ለማስታጠቅ አስብ፡፡ ለተጨማሪ ጥናት መርጃዎች Cornett, Terry G. and James D. Parker. “Developing Urban Congregations: A Framework for World Impact Church Planters.” World Impact Ministry Resources. Los Angeles: World Impact Press, 1991.

Made with FlippingBook flipbook maker