Foundations for Christian Mission, Amharic Mentor Guide
3 8 6 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ከጊዜ ወደ ጊዜ በትምህርቱ ውስጥ “ሚስዮሎጂ” (ማለትም መደበኛ የክርስቲያን ሚሽን ጥናት) ላይ ለማተኮር አስፈላጊ በሆኑት ልኬቶች ላይ የሚያተኩሩ ጥቅሶች ያጋጥሙሃል ፣ ግን ለጊዜውም ቢሆን በመመሪያውውስጥ አልተካተቱም ፡፡ እባክህ እነዚህን አስተውለህ ከተማሪዎቹ ጋር ተወያይ፡፡ ረቂቆቹ የሚያተኩሩት በሚስዮሎጂ ጥናት ላይ ሳይሆን በክርስቲያን ሚሽን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረቶች እና መሰናክሎች ላይ ነው ፡፡ ስለሆነም ፣ በውስጣቸው የተካተቱ ቁልፍ ፅንሰ ሀሳቦችን ፣ ጥቅሶችን ወይም ግንዛቤዎችን ከመሸፈን ወደኋላ አትበል፡፡ ድግግሞሽ የዚህ ሞጁል የሥልጠናን ስልት መሠረት ያደረገ ነው ፡፡ ዓላማዎቹ ፣ የግምገማው ጥያቄዎች ፣ የፅንሰ-ሀሳቦቹ ግምገማ እና ጥናቱ-እነዚህ ሁሉ የተማሪ ቁልፍ ሀሳቦችን በተከታታይ እና በመደጋገም እውነትን በደንብ እንዲጨብጡ ለመርዳት የተቀየሱ ናቸው ፡፡ ይህንን እንደ ችግር አትውሰደው፥ ሁሉም ተማሪዎች በደንብ ማወቅ የሚገባቸው ወሳኝ እውነታዎች ፣ ሀሳቦች እና ግንዛቤዎች ምን እንደሆኑ ማወቅ አለባቸው ፡፡ እነዚህን ወሳኝ ሀሳቦች በመደጋገም በብዛት ሸፍናቸው። ሁል ጊዜም አስተውል፥ በእያንዳንዱ ትምህርት መጀመሪያ ላይ የትምህርቱን ዓላማ በግልጽ እና በጥልቀት እንገልፃለን ፡፡ ይህ የሚሆነው እንዲሁ ለውበት ወይም ቦታን ለመሙላት አይደለም ፤ ይልቁንም ለጠቅላላው የመማሪያ ክፍለጊዜ ልምዶች አስፈላጊ ስለሆኑ ነው፣ በመሆኑም አንተ የምትለው ፣ የምታደርገው እና ተማሪዎችህን ተሞክሮ እንዲቀስሙ የሚያደርጋቸውን ሁሉ አፅንዖት መስጠት እና ማጉላት አለብህ፡፡ ለትምህርት ክፍለጊዜ በምትዘጋጅበት ወቅት በእነዚህ ላይ አተኩር፤ ተማሪዎችህን የሚረዱዋቸውን ተጨማሪ ግንዛቤዎችን ፣ ጥቅሶችን እና ቁሳቁሶችን አዘጋጅ፡፡ በሁሉም ክፍለ-ጊዜያት ዓላማዎቹን የበለጠ ማጉላት በሚችሉበት መጠን የእነዚህን ዓላማዎች ከፍተኛነት የሚረዱ እና የሚገነዘቡት ዕድሎች የተሻሉ ናቸው ፡፡ እንደገና ፣ የትምህርት ክፍለ-ጊዜው የአመራር ስልት ጥሩነት መምህሩ የትምህርቱን ዓላማዎች በመረዳትና አለመረዳት ፣ እንዲሁም በመካከላቸው መተግበር መቻልና አለመቻል ላይ የሚወሰን ነው ፡፡ እንደ መምህር ስኬትህ የሚለካው ዓላማህን ከመረዳትህ፣ ከዚያም በክፍል ውስጥ የተወያያችሁባቸውን፣ የተከናወኑ እና የተለማመዳችኋቸውን ነገሮች ሁሉ ከትምህርቱ ዓላማዎች ጋር የሚዛመዱ እና የሚገናኙ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ካለህ ችሎታ ጋር በቀጥታ የተገናኘ ይሆናል፡፡ ይህ የመልካም የትምህርት ሂደት ዋና ደንብ ነው ፣ በተለይም ከተማሪዎችህ ጋር ግልጽ፣ ሳቢ እና ጠቃሚ የመማር ሁኔታን ማመቻቸት ቁልፍ ነው። ስለዚህ በእያንዳንዱ የትምህርት ክፍለ ጊዜ መጀመሪያ ላይ እነዚህን ዓላማዎች በአጭሩ ከመወያየት ወደኋላ አትበል፡፡ የተማሪዎቹን ትኩረት ወደ ዓላማዎቹ ሳብ ምክንያቱም ይህ የትምህርት ክፍል ጊዜው ዋና ነገር ነው ፡፡ የሚደረጉት ውይይቶች እና ተግባራት ሁሉ ወደዚህ ዓላማዎች መጠቆም አለባቸው ፡፡ በእያንዳንዱ ደረጃዎች ላይ እነዚህን አላማዎች ለማጉላት፣ ለማጠናከር እና ሲሄዱ እንደገና ለመደጋገም አማራጭ መንገዶችን ፈልግ፡፡
2 ገጽ 13 የትምህርቱ ዓላማዎች
Made with FlippingBook flipbook maker