Foundations for Christian Mission, Amharic Mentor Guide
3 9 0 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
በዚህ ጥረት ውስጥ እነሱን ስትደግፋቸው ፣ አንተ በሕይወትህ የተለያዩ ገጽታዎች ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩትን እውነቶች እንዴት እንደምትመለከት በመናገር ይህንን ለእነሱ ሞዴል ማድረግ ትፈልግ ይሆናል ፡፡ በተጨማሪም ተማሪዎችህ የፍላጎታቸውን ይናገሩ ዘንድ የራስህን አንዳንድ ጥያቄዎች ዲዛይን ማድረግ ትፈልግ ይሆናል ፡፡ በጣም አስፈላጊው ነገር እኛ ይህንን ጊዜ የምንጠቀመው ዳታዎችን እንደገና ለማደስ ብቻ አይደለም ፣ ነገር ግን በራሳቸው ሕይወት ውስጥ ስለሚያስቧቸው ፣ ስለሚሰማቸው እና ስለሚመርጧቸው ነገሮች ወደ መሬት በማውረድ የትምህርቱ እውነታዎች በእነዚያ ሁኔታዎች ላይ ምን ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ማሳየት ነው ፡፡ ከዚህ በታች የተጻፉትን ሁሉንም ጥያቄዎች የማዳረስ ወይም በግድ እና በመሰላቸት የመመለስ ምንም ዓይነት ግዴታ አይሰማህ፡፡ እኛ የምንፈልገው ከተማሪዎቻችሁ ጋር ስለ ህይወታቸው እና ስለልቦቻቸው ግልጽ ውይይት ማድረግ እና በቀጥታ ከልምዳቸው በሚመነጩ ጉዳዮች ፣ ስጋቶች ፣ ጥያቄዎች እና ሀሳቦች ላይ ለመግባባት እና በህይወታቸው እና በአገልግሎታቸው ዙሪያ ለመነጋገር ነው ፡፡ የሚበዛውን ጊዜ ከቪዲዮው ለተነሳው ጥያቄ ወይም በተለይም በአገልግሎት ሁኔታቸው ውስጥ አሁን ስላሉበት ተጨባጭ ሁኔታ አግባብ ባለው መልኩ ጊዜ ለማሳለፍ አታመንታ ፡፡ የዚህ ክፍል ዓላማ በሕይወታቸው እና በአገልግሎት አውዶቻቸው ላይ በጥልቀት እና ከሥነ-መለኮት አንጻር እንዲያስቡ ለማስቻል ነው ፡፡ እንደገና ፣ ከዚህ በታች የቀረቡት ጥያቄዎች እንደ መመሪያ እና መነሻ ተደርገው የቀረቡ ናቸው ፣ በፍፁም በአስገዳጅ መልኩ እንደ አስፈላጊ ነገሮች መታየት የለባቸውም ፡፡ ከእነሱ መካከል ምረጥ ወይም የራስህን አማራጭ ውሰድ። እዚህ ጋር ቁልፉ ለእነርሱ ሁኔታ እና ለጥያቄዎቻቸው የሚሰጠው ጠቀሜታ ነው ፡፡ እንደ መምህር ከአንተ ተግባራት መካከል ተማሪዎቹ በትምህርት ሂደቱ የት እንዳሉ እንዲያውቁ ማድረግ ፣ ምን ዓይነት ፅንሰ-ሀሳቦች እየተጠኑ እንደሆኑ እና የትኞቹም በሚቀጥለው እንደሚሸፈኑ ፣ እና የትኞቹ የቤት ስራዎች (ካለ) በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንደሚገኙ ማሳወቅ ነው ፡፡ መጪው የፈተና ጥያቄም ሆነ የንባብ ማጠቃለያ ለሁለቱም ለሚቀጥለው ትምህርት ክፍለ-ጊዜ የተሰጠውን ምደባ እንደተገነዘቡ እርግጠኛ መሆን ይኖርብሃል ፡፡ በነገራችን ላይ የንባብ ምደባ አስፈላጊ ነው ግን ከባድ እንዲሆን አልተፈለገም ፡፡ ግቡ ጽሑፉን በተቻላቸው መጠን እንዲያነቡ እና ትርጉማቸ በሚሰጧቸው ነገሮች ላይ ጥቂት አረፍተ ነገሮችን እንዲጽፉ ነው ፡፡ ይህ ለተማሪዎችህ መማር ወሳኝ ችሎታ ነው ፣ ስለሆነም በዚህ ሂደት ውስጥ እነሱን ማበረታታትህን አረጋግጥ ፡፡ በእርግጥ እነዚህ አስቸጋሪ ለሚሆኑባቸው ተማሪዎች ፣ ከዚህ ሚሽን በስተጀርባ ያለውን ዓላማ አረጋግጥላቸው ፣ እንዲሁም የጽሑፍ ችሎታቸው ሳይሆን ቁሱ ትምህርቱን መረዳታቸው ቁልፉ ነገር መሆኑን አፅንዖት መስጠት ይኖርብሃል፡፡ ደግሞም ችሎታቸውን ማሻሻል እንፈልጋለን ነገር ግን መታነጻቸውንና መነሳሳታቸውን በመሰዋት አይደለም። ስለዚህ በተግዳሮት እና በመነሳሳት መካከለኛ ቦታ ለማግኘት ሞክር፡፡
7 ገጽ 52 ምዘናዎች
Made with FlippingBook flipbook maker