Foundations for Christian Mission, Amharic Mentor Guide

/ 4 5

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡት ጥያቄዎች በዚህ በሁለተኛው ሴግመንት የቀረቡትን ሃሳቦች መለስ ብለህ ለመቃኘት እንዲረዱህ ነው፡፡ በዚህ ክፍል እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለዳዊት የሰጠውን የተስፋ ቃል ፍጻሜ ማእቀፍ ውስጥ ተመልክተነዋል፡፡ እግዚአብሔር ለአብርሃም ዘሩንና በእርሱም አህዛብን ለመባረክ የሰጠው የዘር ተስፋ በይስሀቅ፤ በይሁዳ ነገድ በኩል ተረጋግጧል፡፡ ይህ አህዛብን የመባረክ የዘር ተስፋ ከዳዊት ቤት በዙፋኑ ላይ ወራሽ እንዳይታጣ እግዚአብሄር ለዳዊት ካደረገለት ምህረት ጋር ይገናኛል፡፡ አሁን በናዝሬቱ በኢየሱስ ሰውነት አማካኝነት ለአብርሃምና ለዳዊት የተገባው የእግዚአብሔር ኪዳናዊ ተስፋ ተፈጽሟል፡፡ እንግዲህ ሚሽን በእግዚአብሔር የተስፋ ቃል ታማኝነት የተገኘውን አዲስ ህይወት ማወጅ ነው፡፡ ትምህርትና ስብከት በምታዘጋጅበት ወቅት ይህን ሂደትና መመሪያ መከተል በጣም ወሳኝ በመሆኑ ዋና ዋናዎቹን ነጥቦች በሚከተሉት ጥያቄዎች ውስጥ መቃኘት ያስፈልሃል፡- 1. ሚሽንን እንደ መለኮታዊ የተስፋ ፍጻሜ አንፃር ተርጉም፡፡ ይህ ሃሳብ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊው የቃል ኪዳን ግንዛቤ ጋር እንዴት ይዛመዳል? ቃልኪዳንስ ምንድነው? 2. በቅዱሳት መጽሐፍት ውስጥ ቃልኪዳኖች ምን ያህል በብዛት ይገኛሉ? መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቃልኪዳኖች የሚካሄዱባቸው ሁኔታዎች፤ ጠቀሜታዎች እና እንዴት እንደሚፈጸሙና እንደሚጸኑ አስረዳ፡፡ 3. በጣም የተለመደው የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ኪዳን ምን ዓይነት ነው? በእስራኤል መላው ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ ከሚይዙት የእግዚአብሔር ቃልኪዳኖች ሁለቱን ጥቀስ፡፡ 4. የአብርሃማዊውን ኪዳን ዝርዝሮች አስቀምጥ፤ የቃል ኪዳኑ ሁኔታዎችና የሚያስገኙት ጥቅሞች ምንደናቸው? የተስፋው ቃል የይሁዳ ነገድ ተለይቶ የተሰጠው እንዴት ነበር? ይህስ ግንዛቤ የተሰጠው መቼ ነው? 5. በ2ኛ ሳሙኤል የተጠቀሰው እግዚአብሔር ለዳዊት የሰጠው የተስፋ ቃል በይሁዳ ነገር ግልጽ ከሆነው የአብርሃም ኪዳን ጋር እንዴት ይዛመዳል? የንግስናውን ዘር በተመለከተ እግዚአብሔር የሰጠው የተስፋ ቃል ምን ነበር? ዳዊት ምን ማድረግ ይጠበቅበት ነበር? እግዚአብሔር ምን ያደርግለት ነበር? 6. እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለዳዊት የሰጠው የተስፋው ቃል በናዝሬቱ በኢየሱስ ሰውነት ፍጻሜውን የሚያገኘው እንዴት ነው? እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለዳዊት የሰጠው ተስፋ አሁን መፈጸሙን ህይወቱ ፣ ሞቱ ፣ ትንሳኤው እና እርገቱ እንዴት ግልፅ ማስረጃ ይሰጣል? 7. ሚሽን ለአብርሃምና ለዳዊት የገባው ቃል የአሁኑ ፍፃሜ ሆኖ በኢየሱስ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታማኝነት ያረጋግጣል እና ያውጃል ማለት የምንችለው በምን አግባብ ነው? ታላቁን ተልእኮ በመታዘዝ አህዛብን ሁሉ ደቀ መዛሙርት ማድረግ እንዴት ለአሕዛብ የተፈጸመውን የተስፋ ቃል መግለጫ ይወክላል (ገላ. 3፣ ሮሜ 16.25-27 ፣ ቆላ 1.25-29 እና ​ኤፌ. 3 1-10)? 8. ይህ የተስፋ ቃል እና የፍፃሜው ጭብጥ በሚስዮናዊው ስራ ውስጥ ዋነኛውን ስፍራ የሚይዘው ለምንድን ነው? ኢየሱስ ለአብርሃምና ለዳዊት የተሰጠው የተስፋ ቃል ፍጻሜ ሳይጠቀስ በሚሽን ወንጌልን በግልፅ ማወጅ ይቻል ይሆን? ለምን?

መሸጋገሪያ 2

የተማሪው ጥያቄዎችና ምላሽ

1

Made with FlippingBook flipbook maker