Foundations for Christian Mission, Amharic Mentor Guide
5 2 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ሌሎች የቤት ስራዎች
የዚህ ሞጁል (ትምህርት) ጥናትህ የተሳካ መሆኑን ለማረጋገጥ የሳምንቱን የትምህርት ዝግጅትና የንባብ ስራህን ጨምሮ የሚሰጡ የቤት ስራዎችን በወቅቱ ለማከናወን ይረዳህ ዘንድ ጊዜ መስጠት ያስፈልግሃል፡፡ በቀጣዩ ክፍለ ጊዜ ስለዚህኛው ሳምንት የትምህርት ይዘት (የቪዲዮ ትምህርቱን ይዘትና መመሪያውን) አጭር ፈተና ይሰጥሃል፡፡ የትምህርቱን ዋና ዋና ሃሳቦች በጥናትህ መሸፈንህን አረጋግጥ፡፡ የተሰጠህን የንባብ ስራ በሚገባ አጠናቅቀህ አዘጋጅ፡፡ ይህን ማጠቃለያ ለተማርከውና ዋና ሃሳብ ነው ብለህ ላቀረብከው ሃሳብ ያለህ የአንተ ምላሽ ተገርጎ ይወሰዳል፡፡ ስለ ዝርዝር ጉዳዮች ብዙ መጨነቅ ሳያስፈልግህ የዚያን የመጽሐፍ ክፍል ዋና ሃሳብ ብቻ አቅርብ፡፡ እባክህ እነዚህን ማጠቃለያዎች በሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ይዘሃቸው ቅረብ፡፡ (እባክህ በዚህ ትምህርት መጨረሻ የሚገኘውን “የንባብ ማጠናቀቂያ ገጽ” ተመልከት፡፡) በዚህ ትምህርት ለሚሽን “ፕሮሌጎሜና” ምን እንደሆነ ተመልክተናል፡፡ ሚሽን እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነትና ስራ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለሰው ልጆች ሁሉ ያደረገውን ማዳንና ቤዛነት ማወጅ እንደሆነ ተርጉመናል፡፡ እግዚአብሔር በዚህ ምድር ላይ እንዴት በአንድ ታሪክ እየሰራ እንደሆነ “ሚሽን እንደ ዘመናት ትዕይንት” እና “ሚሽን እንደ መለኮታዊ የተስፋ ቃል ፍጻሜ” በሚሉ ማዕቀፎች ውስጥ ተመልክተናል፡፡ ልዑል እግዚአበሔር፣ የቃልኪዳኑ ታማኝነት ለፍጥረት ቤዛነት ያዘጋጀው እቅድና አላማው በናዝሬቱ ኢየሱስ በኩል ተፈጽሟል፡፡ እንግዲህ ሚሽን ይህንን ሉዓላዊ አላማ ለእርሱ ክብርና ለአህዛብ ሁሉ መዳን መፈጸም ነው፡፡ በቀጣዩ ትምህርታችን የእግዚአብሔርን የማዳን ስራ “የእግዚአብሔር ፍቅር” እና “የሽፍታዎች ጦርነት” በሚሉ ማዕቀፎች ውስጥ የሚሽንን ምስሎች መቃኘታችንን እንቀጥላለን፡፡ የእግዚአብሔርን ፍቅር አስመልክቶ እግዚአብሔር ለእርሱ የሚሆን ህዝብ ከዓለም እንደሚወጣ ወስኖ ነበር፤ እነሆ አሁን በኢየሱስ ክርስቶስ እና በቤተክርስቲያኑ በኩል የእግዚአብሔር ፍቅር ወደ ሙሉ ፍጽምና ደርሷል፡፡ የጦርነትን ማዕቀፍ አስመልክቶ ደግሞ እግዚአብሔር የመንግስቱን አገዛዝ በናዝሬቱ በኢየሱስ በኩል ድጋሚ ስለመመስረት ወስኗል፡፡ ከውድቀት አንስቶ እግዚአብሔር ፍጥረቱን ሁሉ በራሱ አገዛዝ ስር መልሶ ለማድረግ የተዋጊን ቦታ ይዞ እናየዋለን፡፡በናዝሬቱ በኢየሱስ ሰውነት አማካኝነት እግዚአብሔር ፍጥረታትን ሁሉ የመግዛት መብቱን መልሶ እያረጋገጠ ነው፤ ስለዚህ ሚሽን አሁን በክርስቶስ በኩል የመጣውን ይህን የመንግስቱን ስልጣን ማሳየትና ማወጅ ነው፡፡
ገጽ 390
7
1
ለቀጣዩ ትምህርት መዘጋጀት
Made with FlippingBook flipbook maker