Foundations for Christian Mission, Amharic Mentor Guide

/ 5 7

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

ድልና የደረሰበትን እርግማን ለማወጅና ለማሳየት የተሾመች የዛሬይቱ የእግዚአብሔር መንግሥት ምልክት እና ቅምሻ ናት፡፡ • ሚሽን እንደ ሽፍቶች ጦርነት የሚለው ማእቀፍ የሚኖረውን አንድምታ እግዚአብሔር በክርሰቶስ ኢየሱስ በኩል ዛሬ በፍጥረታት ላይ ያለውን አገዛዝ ጨምሮ፤ እግዚአብሔር በተቀባው በልጁ በኩል የክፉን ኃይልና የእርግማንን ተጽዕኖ ያሸነፈ ተዋጊ እንደሆነና ሚሽን በዚህ መነጽር ሲታይ እንዴት የእግዚአብሔር መንግስት እዚህና አሁን የመሆኑ ማሳያና አዋጅ መሆኑን ትገነዘባለህ፡፡ አህዛብን ሁሉ ደቀ መዝሙር ማድረግ ማለት በናዝሬቱ በኢየሱስ ሊመጣ ያለውን የእግዚአብሔር አገዛዝ ማስፋት ማለት ነው፡፡ መለኮታዊው ፍቅር አፌ 5፡25-32 “ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤ እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ። እንዲሁም ባሎች ደግሞ እንደ ገዛ ሥጋቸው አድርገው የገዛ ሚስቶቻቸውን ሊወዱአቸው ይገባቸዋል። የገዛ ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል፤ ማንም የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ከቶ የለምና፥ ነገር ግን የአካሉ ብልቶች ስለሆንን፥ ክርስቶስ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን እንዳደረገላት፥ ይመግበዋል ይከባከበውማል። ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ።” የቅዱሳት መፅሀፍት አንዱ አስደናቂ ነገር በታላላቅ ገጸባህርያቱ ህይወትና ልምምዶችውስጥ የተሰወሩት ጥልቅና መሰረታዊ ምስጢራቱ ናቸው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ይህ የቅዱሳት መጻሕፍት ልዩ ባህሪ ከመገለጥ (inspiration) ጋር ይያያዛል፡፡ ከዋና ዋናዎቹ ገጸባህሪያቱ በመነሳት ስለ እግዚአብሔር ተፈጥሮና ከህዝቡ ጋር ስላለው ግንኙነት ትምህርት መቅሰም ይቻላል፡፡ የአዳምና የሄዋን ምሳሌና እንደ ባልና ሚስት ያላቸው ጥምረት በክርሰቶስና በህዝቡ መካከል ያለው ታላቅ ጥምረት ምሳሌ ነው፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ እንደተፈጸመ ለሰው ልጆች የእግዚአብሔርን ልብ የሚያሳይ - ዛሬ ለእኛ ይህ እንዴት ያለ ድንቅ ትምህርት ነው! እግዚአብሔር ከዘመናት በፊት በናዝሬቱ ኢየሱስ ለርስቱ የተለየን ወገን ከአህዛብ መካከል እንደሚጠራ አስቀድሞ ወስኖ ነበር፡፡ እዚህ ላይ ይህ ጽሁፍ ጥቅል ምስጢርን ያሳያል፡፡ በፍጥረት አለም እምብርት ላይ ማራኪ ስነጥበባዊ ትእይንት፣ መለኮታዊ ፍቅር፣ መሳጭ እና አስደናቂ ታሪክ፣ ሁሉን በሚችለው አምላክና በህዝቡ መካል የማይሞት የፍቅር ግንኙነት አለ፡፡ እንግዲህ እኛም የዚህ ህያው ምስክሮች ነን፤ የናዝሬቱ ኢየሱስን ወንጌል አምነው እንደተቀበሉ ሰዎች ይህን መለኮታዊ የፍቅር ድራማ እንዲኖሩት የተመረጡና የተጠሩት ህዝቦች አካል ሆነናል፡፡ የዚህ መለኮታዊ ፍቅር ተፈጥሮ ምን ይመስላል? በብሉይ ኪዳን ይህን በእግዚአብሔር እና በህዝቡ በእስራኤል መካከል ትመለከታለህ፡፡ ኢሳ 62፡5 “ጕልማሳም ድንግሊቱን እንደሚያገባ፥ እንዲሁ ልጆችሽ ያገቡሻል፤ ሙሽራም በሙሽራይቱ ደስ እንደሚለው፥ እንዲሁ አምላክሽ በአንቺ ደስ ይለዋል።”

ጥሞና

ገጽ 393

2

2

Made with FlippingBook flipbook maker