God the Father, Amharic Mentor Guide

1 0 /

እግዚአብሔር አብ

የኤክሴጄሲስ ፕሮጀክት ይህ ትግበራ በትምህርተ እግዚአብሔር አብ የጥናት ሞጁል ውስጥ የተሳትፎህ ቁልፍ አካል ነው። ይህንን መስፈርት ለማሟላት የቅዱሳት መጻሕፍትን ምንባብ መርጠህ በጽሑፉ ላይ ኢንዳክቲቭ ጥናት (የትርጓሜ ጥናት) ማድረግ አለብህ። ከሚከተሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ውስጥ አንዱን መምረጥ ትችላለህ፡-  የሐዋርያት ሥራ 17:24-31  ኢሳይያስ 40:22-26  ሮሜ 9:13-18  ዳንኤል 4:34-37  መዝሙረ ዳዊት 103:9-18  ማቴዎስ 6:25-33  መዝሙረ ዳዊት 104:24-30 የዚህ ፕሮጀክት አላማ በእግዚአብሔር መግቦት፣ በፍጥረት ሁሉ ላይ ስላለው ጥበቃ እና አስተዳደር፣ እና ይህ ዛሬ ለህይወታችን ምን ማለት እንደሆነ በሚመለከት አንድ ዋና ክፍል በዝርዝር እንድታጠና እድል ለመስጠት ነው። ምናልባት ለክርስቲያን መሪ የቅዱሳት መጻሕፍትን ትርጉም ግልጽ ከማድረግ እና በዛሬው ጊዜ ካሉት ሰዎች እውነተኛ የሕይወት ጭንቀቶች ጋር ከማዛመድ ችሎታቸው የበለጠ አስፈላጊ ነገር የለም። አላማው የአንቀጹን ትርጉም ግልጽ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የክፍሉን ትርጉም በቀጥታ ከራስህ የግል የደቀመዝሙርነት ጉዞ ጋር በማያያዝ እና በቤተክርስቲያንህ ወይም በአገልግሎትህ እንድታገለግል እግዚአብሔር የጠራቸውን ሰዎች እንድታስተምር ነው። ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮጀክት እንደመሆኑ የትርጓሜ ጥናት (ኤክሴጄሲስ) ለመስራት የጥናት ክፍሉን በአውዱ ውስጥ መረዳት ያስፈልጋል። በመቀጠልም ዋናውን ትርጉም ከተረዳህ በኋላ ለሁላችንም ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል መርህ ማውጣትና ይህንም በተጨባጭ ከህይወት ጋር ማዛመድ ይኖርብሃል። ይህን የግል የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጥናት በምታደርግበት ወቅት እነዚህ ሶስት ደረጃዎች ሊያግዙህ ይችላሉ:- 1. በተሰጠው ምንባብ ውስጥ ለተጠቀሱት ዋና አድማጮች እግዚአብሔር መናገር የፈለገው ምንድነው? 2. ከዚህ ምንባብ ልንማረው የምንችለውና ለሁሉም ዘመንና በየትኛውም ቦታ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ ልንወስደው የምንችለው መርህ ምንድነው? 3. ዛሬም መንፈስ ቅዱስ እኔን ከተማርኩት መርህ በመነሳት ምን እንዳደርግ ነው የሚፈልግብኝ? እንግዲህ እነዚህን ጥያቄዎች በተገቢው መንገድ ከመለስክ በቀጣይ ለወረቀት ስራህ የግልህን መረዳት ለማቅረብ ዝግጁ ነህ ማለት ነው። ለወረቀት ስራህ ይህን ቅደም ተከተል ተከትሎ መስራት ይረዳሃል፥ 1. የመረጥከው የንባብ ክፍል ዋና ጭብጥ ወይም ሃሳብ ምን እንደሆነ ለይተህ አስቀምጥ። 2. የምንባቡን ዋና ትርጉም በአጭሩ ግለጽ (ይህን በሁለት ወይም በሶስት አንቀጽ ልታስቀምጠው ትችላለህ ወይም ደግሞ በእያንዳንዱ ቁጥር አጫጭር ማጣቀሻ ወይም ማመሳከሪያ እየተጠቀምክ መሄድ ትችላለህ።)

ዓላማ

ዝርዝር መግለጫ እና አወቃቀር

Made with FlippingBook - Online magazine maker