God the Father, Amharic Mentor Guide
/ 1 9
እግዚአብሔር አብ
3. ሥነ-መለኮት ስለ መገለጥ ነጸብራቅ ነው፣ የሰው ልጅ ስለ እግዚአብሔር ማንነት እና መገለጥ የሚያስበው ሃሳብ ማለት ነው።
ሀ. ባህላችን ስለ እግዚአብሔር ባለን አስተሳሰብ ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር መንቃት አለብን።
ለ. ያለ መንፈስ ቅዱስ እርዳታ ስለ እግዚአብሔር በራሳችን አተያይ ብቻ ማመን የለብንም።
1
ሐ. ብዙ የሥነ-መለኮት አይነቶች ቢኖሩም የትኛውም ሥነ-መለኮት እግዚአብሔርን ሙሉ በሙሉ አያብራራም።
መ. ትህትና ለሥነ-መለኮት ጥናት መሰረታዊ ነገር ነው።
4. ከቅዱሳት መጻሕፍት እና ከቤተክርስቲያን የሚመጡ ተአማኒ የሆኑ የስነ-መለኮት ጉዳዮች፡ ነገረ መለኮት ማለት በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ዋና በሆነው የእግዚአብሔር መገለጥ ላይ የምታንፀባርቅ ቤተክርስቲያን ማለት ነው።
5. ሥነ መለኮት ሌሎች የትምህርት ዘርፎችን ሊያማክል ይችላል፥ ይሁን እንጂ እነዚያን ትምህርቶች በፍጹም መከተል የለበትም፣ እግዚአብሔር ብቻ በመንፈሱ በቅዱሳት መጻሕፍት ሊገለጥልን ይችላል።
II. ሉዓላዊው አምላክ ራሱን ይገልጥልናል፡ አጠቃላይ እና ልዩ መገለጥ አጠቃላይ መገለጥ፡- “እግዚአብሔር ሁል ጊዜ በሁሉም ቦታ ለሁሉም ሰው የሚናገረው።” ልዩ መገለጥ፡- “ለተወሰኑ ሰዎች በተወሰኑ ጊዜያት የእግዚአብሔር ልዩ ንግግሮች እና መገለጫዎች፣ አሁን የሚገኙት የተወሰኑ ቅዱሳት መጻሕፍትን [ማለትም፣ መጽሐፍ ቅዱስን] በመመልከት ብቻ እግዚአብሔር ራሱን የሚገልጥባቸው ግንኙነቶች እና መገለጫዎች ናቸው።
~ Millard Erickson, Introducing Christian Doctrine, 2nd Ed. Grand Rapids: Baker Book House, 2001. p. 42
Made with FlippingBook - Online magazine maker