God the Father, Amharic Mentor Guide

3 0 /

እግዚአብሔር አብ

4. እግዚአብሔርን ለሌሎች ለማስተዋወቅ መዝ. 71፡17-19

ዛሬ ቤተክርስቲያን ላይ ያለው በጣም ከባዱ ግዴታ ስለ እግዚአብሔር ያላትን ፅንሰ-ሀሳብ ለእርሱም ሆነ ለራሷ በሚገባ መልኩ እስኪሆን ድረስ ማጥራት እና ከፍ ማድረግ ነው። በጸሎቷ እና በድካሟ ሁሉ ይህ የመጀመሪያ ቦታ ሊኖረው ይገባል። እኛ ካለፉት የዕብራውያን እና የክርስትና አባቶቻችን የተቀበልነውን ያንን የተከበረውን ስለ እግዚአብሔር የሆነ መረዳት ሳይደበዝዝ እና ሳይቀንስ በማስተላለፍ ለሚመጣው የክርስቲያን ትውልድ ትልቁን አገልግሎት እናበረክታለን። ይህ ማንኛውም ጥበብ ወይም ሳይንስ ሊፈጥሩላቸው ከሚችሉት ከማንኛውም ነገር የበለጠ ዋጋ እንደሚያስገኝላቸው ያረጋግጣል። ~ A.W. Tozer. The Knowledge of the Holy . New York: Harper San Francisco, 1961. p. 4.

III. የአምላክ ጥናት ውቅር፡ የእግዚአብሔር ባህሪያት ተፈጥሮ እና ምደባ

ሀ. የእግዚአብሔር ባህሪያት ተፈጥሮ

1. ባህሪያቱ የአምላከ ስላሴን ሁለንተናዊ መለኮታዊ ባህሪያት ያንፀባርቃሉ።

1

ሀ. ከተለያዩ የስላሴ አካላት ጋር ከሚዛመዱት ተግባራዊ ባህሪያት ጋር አንድ አይነት አይደሉም።

ለ. ከስላሴ አካላቱ ተግባራት ወይም ድርጊቶች ጋር ተመሳሳይ አይደሉም፣ ከእያንዳንዱ የስላሴ አካል ባህሪያት ጋር ይለያያሉ።

2. የእግዚአብሔር ባህርያት ውስጣዊ የሆኑ ቋሚ ባሕርያቱ ናቸው።

3. ባህርያቱ ስለ እግዚአብሔር ማንነትና ምንነት ይናገራሉ።

ለ. የእግዚአብሔር ባህሪያት ምደባ

1. የእግዚአብሔር ታላቅነት (እነዚህ ከእግዚአብሔር ግርማ ጋር የተያያዙ ባህሪያቱ፣ እግዚአብሔር በአምላክነቱ፣ በሥነ መለኮት ጥናት ውስጥ “ተፈጥሯዊ ባሕርያት” ይባላሉ)

ሀ. መንፈሳዊነት

ለ. ህይወት

Made with FlippingBook - Online magazine maker