God the Father, Amharic Mentor Guide
3 2 /
እግዚአብሔር አብ
የሚከተሉት ጥያቄዎች በሁለተኛው የቪዲዮ ሴግመንት ውስጥ ያለውን ሐሳብ እንድትገመግም ለመርዳት ታስበው የተዘጋጁ ናቸው። የኒቂያው የእምነት መግለጫ እንደሚያመለክተው አንድ አምላክ ብቻ አለ፣ እርሱም ሁሉን ቻይ የሆነው፣ ሰማይንና ምድርን፣ የሚታየውንና የማይታየውንም ሁሉ የፈጠረ እግዚአብሔር አብ ነው። በፍጥረቱ መካከል እንደሚገኝና እንደሚሰራ እንዲሁም ከፍጥረቱ ሁሉ የመጠቀ ልዕለ-አምላክ እንደመሆኑ መጠን ባህሪያቱን ከታላቅነቱ እና ከመልካምነቱ አንፃር ልንረዳው ይገባል። ቀጥሎ በቀረቡት ጥያቄዎች ላይ ስታሰላስል፣ መልሶችህን ቀላል እና ቀጥተኛ ለማድረግ ሞክር፣ አስፈላጊ ሲሆን ደግሞ መልሶችህን በቅዱሳት መጻሕፍት አስደግፍ! 1. የኒቂያው የእምነት መግለጫ ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚአብሔር አብ ሰማይንና ምድርን፣ እንዲሁም የሚታየውንና የማይታየውን ሁሉ የፈጠረ መሆኑን ይጠቁማል። ስለ እግዚአብሔር ለሚደረጉ ውይይቶች እና ጥናቶች ሁሉ ይህ የመጀመሪያው እና መሰረታዊው እውነት የሆነው ለምን ይመስልሃል? መልስህን አስረዳ። 2. የእግዚአብሔር ህልውና ተፈጥሮ ምንድ ነው? እግዚአብሔር በፍጥረቱና በሰው ልጆች ጉዳዮች ውስጥ በንቃት ተሳትፎ እንደሚያደርግ የሚያሳየን በምን መንገዶች ነው? 3. ለእኛ እንደ ነገረ መለኮት ተማሪነታችን ስለ እግዚአብሔር ሕልውና ማወቅ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ይህ ትምህርት ለሚሽን፣ ስለ እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት የሌላቸውን ሰዎች ለመድረስ የሚኖረው አንዳንድ አንድምታዎች ምን ሊሆኑ ይችላሉ? 4. የእግዚአብሔር ልዕልና ተፈጥሮ ምንድን ነው? እግዚአብሔር ያለ መንፈስ ቅዱስ እርዳታ ሊታወቅ እንደማይችል መረዳት ያለብን ለምንድነው? 5. እግዚአብሔር ልዕለ-ኃያል መሆኑን የመረዳት አንድምታው ምንድን ነው? ይህ ትምህርት እግዚአብሔርን ለማምለክና ለማገልገል የሚረዳን እንዴት ነው? 6. የእግዚአብሔር ባህሪያት ማለት ምን ማለት ነው? የእግዚአብሔርን የግል ባህሪያቱን ስናጠና ሁልጊዜ የእግዚአብሔርን አንድነት ማስታወስ አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድን ነው? አንዱን ከሌላው ለይተን የእግዚአብሔርን ባሕርያት አንድ በአንድ ለመረዳት በምንፈልግበት ጊዜ ልናስወግዳቸው የሚገቡን ስህተቶች የትኞቹ ናቸው? 7. የነገረ መለኮት ሊቃውንት የእግዚአብሔርን ባሕርያት እንዴት ይመድባሉ? ከእግዚአብሔር ታላቅነት ጋር የተያያዙት ባህሪያት የትኞቹ ናቸው? ከመልካምነቱ ጋር የተያያዙትስ የትኞቹ ናቸው?
መሸጋገሪያ 2
የተማሪው ጥያቄዎች እና ምላሾች
1
Made with FlippingBook - Online magazine maker