God the Father, Amharic Mentor Guide

/ 3 7

እግዚአብሔር አብ

የዚህ ትምህርት ማዕከላዊ ሃሳብ እግዚአብሔር ያለና የሚሰራ እንዲሁም ምጡቅ እና ሉዓላዊ መሆኑ ነው። እርሱ በክቡር ፍጥረቱ አማካኝነት ለሰው ሁሉ ይገለጣል፣ ነገር ግን ንስሐ ለሚገቡ እና በመሲሑ ኢየሱስ ለሚያምኑ ሁሉ የገዛ ልቡንና ማንነቱን በግል ይገልጣል። ስለ እግዚአብሔር በምታውቀውና በምታምነው ነገር ለመኖር ብርታቱን እና ጥበቡን ጌታ እንዲሰጥህ እሻ፣ የእግዚአብሔርን የከበሩ ባህሪያት እና ስብዕናን በሚመለከት እውነቱን በበለጠ ግልጽነት እና ድፍረት እንድትናገር እንዲረዳህ ጌታን ለምን። እግዚአብሔር በሚናገረህ በማንኛውም ጉዳይ ላይ ከመሪዎችህ እና ከመምህሮች ድጋፍ ጠይቅ፤ ከተማርከው ነገር የተነሳ እግዚአብሔር በዚህ ሳምንት በልብህና በአእምሮህ እንድታደርገው የሚፈልገውን ሁሉ ሳትዘገይ እንድትታዘዝ የእግዚአብሔርን መንፈስ ሙላት ጠይቅ።

ምክር እና ጸሎት

ምደባዎች

1

መዝሙረ ዳዊት 19፡1-3

የቃል ጥናት ጥቅስ

ለክፍል ለመዘጋጀትና የሚቀጥለውን ሳምንት የምንባብ ምደባ ለማግኘት www.tumi.org/booksን ጎብኝ ወይም መምህርህን ጠይቅ።

የንባብ የቤት ስራ

ውድ ተማሪ ሆይ፣ በቀጣዩ ክፍለ ጊዜ ስለዚህኛው ሳምንት የትምህርት ይዘት (የቪዲዮ ትምህርቱን ይዘትና መመሪያውን) አጭር ፈተና ይሰጥሃል፡፡ የትምህርቱን ዋና ዋና ሃሳቦች በጥናትህ መሸፈንህን አረጋግጥ፡፡ የተሰጠህን የንባብ ስራ በሚገባ አጠናቅቀህ አዘጋጅ፡፡ የተመደበውን ንባብ አንብበህ እያንዳንዱን ንባብ ከአንድ ወይም ከሁለት በማይበልጥ አንቀጽ አጠቃልል። በዚህ ማጠቃለያ በእያንዳንዱ ንባብ ውስጥ ዋና ነጥብ ነው ብለህ የምታስበውን የተሻለ ግንዛቤ አቅርብ። ስለ ዝርዝር ጉዳዮች ብዙ መጨነቅ ሳያስፈልግህ የዚህን የመጽሐፍ ክፍል ዋና ሃሳብ ብቻ አቅርብ፡፡ እባክህ እነዚህን ማጠቃለያዎች በሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ይዘሃቸው ቅረብ፡፡ (እባክህ በዚህ ትምህርት መጨረሻ የሚገኘውን “የንባብ ማጠናቀቂያ ገጽ” ተመልከት፡፡) በሚቀጥለው ትምህርታችን ትኩረታችንን በፍጥረት እና በታሪክ ሁሉ ላይ የእግዚአብሔርን የበላይ ስልጣን እና መግቦትን በመረዳት ላይ እናደርጋለን። እግዚአብሔር አብ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ሉዓላዊ፣ የሁሉም ነገር ምንጭ እና የሁሉ አኗሪ እንደሆነ እንመለከታለን። በክርስቶስ ዳግመኛ ምጽአት ፍጥረትን ሁሉ ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ በገባው ቃል ኪዳን እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር የሚጠብቅበትን እና በፍጥረት ሁሉ ላይ ያለውን አገዛዝ እንመረምራለን።

ሌሎች የቤት ስራዎች

ገጽ 258  13

ለቀጣዩ ትምህርት መዘጋጀት

ይህ ሥርዓተ-ትምህርት የThe Urban Ministry Institute (TUMI) የሺዎች ሰዓታት የሥራ ውጤት በመሆኑ ያለ ፈቃድ ማባዛት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ TUMI እነዚህን መማሪያዎች ለእግዚአብሔር መንግሥት እድገት ለመጠቀም ለሚፈልጉ ሁሉ ድጋፍ ያደርጋል፤ በተጨማሪም ለማባዛት በተመጣጣኝ ዋጋ ፈቃድ ይሰጣል ፡፡ እባክህ ይህ መጽሐፍ በትክክል ፈቃድ ያገኘ መሆኑን ከመምህርህ ጋር በመሆን አረጋግጥ፡፡ በ TUMI እና በፈቃድ አሰጣጥ ፕሮግራማችን ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት Www.site.org እና Www.tumi.org/license ን ጎብኝ፡፡

Made with FlippingBook - Online magazine maker