God the Father, Amharic Mentor Guide
/ 5
እግዚአብሔር አብ
የትምህርቱ/የሞጁሉ መግቢያ
ኃያል በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም ላንተ ይሁን!
የአምላካችንን የእግዚአብሔር አብ ማንነት ማጥናት በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ካሉ ጥናቶች ሁሉ እጅግ አስፈላጊ እና እጅግ ጥልቅ ከሆኑት አንዱ ነው። የደቀመዝሙርነታችንን፣ የአምልኮታችንን እና የአገልግሎታችንን ክፍል ሁሉ ይነካል። በእውነት ጌታችን ኢየሱስ “እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት” እንዳለው ነው (ዮሐ. 17፡3)። ፕሮሌጎሜና፡ ትምህርተ እግዚአብሔር እና የመንግሥቱ መስፋት፣ በተሰኘው በመጀመሪያው ትምህርታችን፣ እግዚአብሔር ራሱን ለእኛ የመግለጡን አስፈላጊነት በመመልከት፣ የነገረ መለኮትን ጥናት የሚያስተናግደውን ፕሮሌጎሜና በአጭሩ እንመረምራለን። የጠቅላላ እና የልዩ መገለጥ ጽንሰ ሀሳቦችን እናጠናለን፣ እንዲሁም ትምህርተ እግዚአብሔርን የማጥናት አስፈላጊነትን ከእግዚአብሔር ህልውና አንጻር፣ ማለትም እግዚአብሔር በፍጥረት ውስጥ ስላለው መገኘትና ተሳትፎ፣ እንዲሁም የእርሱን ምጡቅነት/ልዕልና፣ የእግዚአብሔርን የማይወሰን ተፈጥሮና ታውቆ የማይጨረስ ማንነት በጥንቃቄ እንመረምራለን። እግዚአብሔር እንደ ፈጣሪ፡ የእግዚአብሔር መግቦት በተሰኘው በሁለተኛው ትምህርታችን በፍጥረት እና በታሪክ ሁሉ ላይ ያለውን የእግዚአብሔርን የበላይ ሥልጣን እና መግቦትን እንመረምራለን። እግዚአብሔር ሁሉን እንደ ፈቃዱ ይሰራል። ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚአብሔር አብ የሁሉም ሉዓላዊ ገዥ፣ የሕይወት ሁሉ ምንጭ፣ እና በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሁሉ አኗሪ ነው። በተጨማሪም የእግዚአብሔር መግቦት ሁሉንም ነገር በመጠበቅ እና በማስተዳደር እንዴት እንደሚገለጽ እንመረምራለን፤ የእግዚአብሔርን መግቦትን በተመለከተ ጠንካራ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ግንዛቤ በፍልስፍና እና በሥነ-መለኮት ውስጥ ዋና ዋና ዘመናዊ ስህተቶችን ማለትም ፓንቴይዝም፣ ዴይዝም፣ ፋታሊዝም እና እድል እንዴት እንደሚፈታ እንመለከታለን። አምላከ ስላሴ: የእግዚአብሔር ታላቅነት በተሰኘው በሦስተኛው ትምህርታችን ጥቂት ለየት ያለ አቅጣጫ እንይዛለን። ስለ ሥላሴ፣ ማለትም ስለ እግዚአብሔር ሥላሴአዊ ማንነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎችን እንመለከታለን። ቅዱሳት መጻሕፍት አንድ አምላክ ብቻ እንዳለ ያስተምራሉ፣ ነገር ግን ይህ አምላክ ራሱን እንደ እግዚአብሔር አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ገልጿል። የሥላሴ አካላት አንድ፣ ልዩ ልዩና እኩል ናቸው፤ አንድ እውነተኛ አምላክ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ናቸው። ስለ ሥላሴ ካጠናን በኋላ፣ የእግዚአብሔርን የታላቅነቱን ባህሪያት፡ መንፈሳዊነቱን፣ ህያውነቱን፣ ስብዕናውን፣ የማጨረስና የማይለወጥ ማንነቱን በአጭሩ እንመረምራለን። በመጨረሻም፣ በትምህርት አራት እግዚአብሔር እንደ አባት፡ የእግዚአብሔር ቸርነት ወደተሰኘው ክፍል ትኩረታችንን እናዞራለን። እዚህ ላይ የእግዚአብሔርን ድንቅ ቸርነት በሥነ ምግባራዊ ባሕርያቱ ውስጥ ፍጹም የሞራል ንጽህና፣ ፍጹም ጽኑ አቋም እና ገደብ የለሽ ፍቅሩ ውስጥ እንመለከታለን። የእግዚአብሔርን ቸርነት እና ቆራጥነት በመመልከት፣ በእግዚአብሔር ቸርነት እና ጭከና፣ በፍቅሩ እና በፍትህ መካከል ያለውን ግንኙነት በመመርመር ሞጁላችንን እንዘጋለን ።
Made with FlippingBook - Online magazine maker