God the Father, Amharic Mentor Guide
/ 6 3
እግዚአብሔር አብ
ዝግመተ ለውጥ፣ ፍጥረት ወይስ ምን? ከወጣቶች ቡድን ስብሰባ በኋላ ከተማሪዎችህ አንዷ ሺርሊ እየሠራችበት ስላለው የትምህርት ቤት ፕሮጀክት ካንተ ጋር መነጋገር ትችል እንደሆነ ጠየቀችህ። እንደ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የኬሚስትሪ የጥናቷ አካል፣ በዝግመተ ለውጥ ክርክር ላይ ወረቀት ለመጻፍ መርጣለች። እርሷ ራሷ ክርስቲያን መሆኗን በጋዜጣው ላይ መግለጽ ይኑርባት ወይም አይኑርባት ወይም ዝምብላ በዚህ ውይይት ዙሪያ እየተሽከረከሩ ያሉትን የተለያዩ ክርክሮችን ብቻ መዘርዘር እንዳለባት እርግጠኛ አይደለችም። ጉዳዩን ስታጠና ምናልባት የዝግመተ ለውጥ አንዳንድ ክፍሎች ከእውነት የራቁ ላይሆኑ እንደሚችሉ ብትገነዘብም፤ ነገር ግን ኅሊናዋ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ብቻ የሰማይና የምድር ፈጣሪ እንደሆነ ከማመን አልቦዘነም። መምህሯ ፍጥረት ሳይንስ ሳይሆን ምናባዊ ፈጠራ ነው ስትል ስትሰማ ብትጎዳና ግራ ብትጋባም የኢየሱስ ተከታይ እንደመሆኗ እምነቷን የምታካፍልበትን የግንኙነት ድልድይ ግን ማፍረስ አትፈልግም። ለወረቀቷ የተሻለው ስልት ምን መሆን እንዳለበት ግራ ገብታለች። ሸርሊን ፕሮጀክቷን እንዴት እንድትሰራ ትመክራታለህ-ምን ዓይነት አቀራረብ መውሰድ አለባት? ስራዋንስ በምን መልኩ መያዝ አለባት? እልቂት ቅጣት በአካባቢው በሚገኝ የመጻሕፍት መደብር ውስጥ መደርደሪያውን ስትቃኝ፣ ሆሎኮስት (ከ1939-1945 በሦስተኛው ራይክ ስድስት ሚሊዮን አይሁዶች ላይ የተፈፀመው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ) መሲሑን በመሰቀላቸው ምክንያት በእነሱ ላይ የመጣ እውነተኛ ቅጣት ነው የሚለውን ክርክር የሚያቀርብ መጽሐፍ አጋጥሞሃል። የታሪክ ምሁር ነኝ ባዩ የጸሃፊው ትንታኔ በአብዛኛው ስነ-መለኮታዊ ነው (እንዲሁም ክርስቲያን ነኝ ይላል)። ከዚህ መጽሐፍ ምን እንወስዳለን? በታሪክ ውስጥ የተፈጸሙትን ክንውኖች በመመልከት እና እግዚአብሔር የተከናወኑት ክንውኖች መለኮታዊ ዓላማን ለመፈጸም እንዳሰበ የሚጠቁመውን እንዲህ ዓይነት ትንታኔ እንዴት እንውሰድ። (ለምሳሌ ብዙዎች በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የነበረውን ባርነት ለአፍሪካ አሜሪካውያን አስቀድሞ የተወሰነ ነው ብለው ያምኑ ነበር፣ ምክንያቱም ኖህ ከጥፋት ውሃ በኋላ ካም ላይ ያደረገው እርግማን ውጤት ነው ብለው ይከራከራሉ (ዘፍ. 9.24-25))። የነጮች አምላክ ብዙ ሰዎች ዛሬ የክርስትና እምነት በነጮች ለነጮች የተፈጠረ በአውሮፓ ባህል የተቀረጸ እና የሚወሰን ሃይማኖታዊ ባህል ነው ብለው ያምናሉ። እንዲህ ያለውን አስተሳሰብ እንዴት ሊያገኙ እንደሚችሉ ለማየት አስቸጋሪ አይደለም፡ የክርስትና ወግ ከአውሮፓውያን ባሕሎች ጋር የተቆራኘ ነው፣ አብዛኞቹ የአምልኮ ሥርዓቶች፣ የጥበብ አገላለጾች እና የጽሑፍ ምንጮች ከአውሮፓ ሥር የወጡ ናቸው፣ እንዲሁም እግዚአብሔር ሁልጊዜ ከ”ደቡብ” እና “ምስራቅ” አገሮች ይልቅ ከምዕራቡ ዓለም አገሮች ጋር ተያያዞ ይነሳል። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ ብዙዎች ክርስትናን በመቃወም ይነሳሉ ምክንያቱም በሁሉን ቻዩ እግዚአብሔር አብ ላይ ያለን እምነት እና የአውሮፓ-አሜሪካን ባህልና የአኗኗር ዘይቤን መደገፍን ያምታታሉ።
ጥናቶች
1
ገጽ 262 7
2
2
3
Made with FlippingBook - Online magazine maker