God the Father, Amharic Mentor Guide

/ 6 5

እግዚአብሔር አብ

የእግዚአብሔርን መግቦት ሁሉንም ውስብስብ ነገሮች መረዳት እንደማንችል ብናውቅም፣ ስለ እግዚአብሔር ሉዓላዊነት በሕይወታችን ላይ ስናሰላስል ልባችን እንደሚሞላ እና እንደሚበረታታ እናውቃለን። ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የሚናገሩት ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚአብሔር አብ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ መሆኑን ነው ስለዚህም አጽናፈ ዓለሙ ሁሉ የእርሱ እንደሆነ እና እንደ አሳቡም ለተጠሩት ሁሉም አንድ ላይ ተያይዞ የሚሠራ መሆኑን ነው (ሮሜ. 8.28)። ያለ ጥርጥር፣ በእግዚአብሔር መግቦት እና አገዛዝ፣ በጥበቃው እና ምሪቱ በጌታ ፊት መቅረብ ያለባቸው ጉዳዮች እና ነገሮች አሉህ። ለራስህ ህይወት፣ ለምትወዳቸው ሰዎች እና በአገልግሎት የምታገለግላቸውን ሰዎች በመወከል የልብህን ፍላጎት ወደ ጌታ ለማንሳት ትንሽ ጊዜ ውሰድ። በእነዚህ እና ሌሎች ከህይወትህ እና ከአገልግሎትህ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ አስተማሪህ ከአንተ ጋር ሊጸልይ እንደሚችል አስታውስ።

ምክር እና ጸሎት

ገጽ 263  9

ምደባዎች

2

1ኛ ዜና 29፡11-12

የቃል ጥናት ጥቅስ

ለክፍል ለመዘጋጀትና የሚቀጥለውን ሳምንት የምንባብ ምደባ ለማግኘት www.tumi.org/books ን ጎብኝ ወይም መምህርህን ጠይቅ።

የንባብ የቤት ስራ

ለሳምቱ የተሰጠውን የትምህርት ማጠቃለያ የሰራህበትን የንባብ መልመጃ ይዘህ መቅረብ ይጠበቅብሃል (እባክህ በዚህ ትምህርት መጨረሻ ላይ ያለውን “የንባብ ማጠናቀቂያ ገጽ” ተመልከት)። በተጨማሪም ለምትሰራው ኤክሴጄቲካል ፕሮጀክት ምንባብ መርጠህ፥ ለሚኒስትሪ ፕሮጀክትህ ደግሞ ፕሮፖዛል አዘጋጅተህ አቅርብ። በተጨማሪም ሞጁሉ ከማብቃቱ በፊት ስለሚካሄደው የአገልግሎት ፕሮጀክት እንዲሁም የትርጓሜ ፕሮጄክቱን ለመሥራት የትኛውን የቅዱሳት መጻሕፍት ክፍል እንደምትመርጥ ለማሰብ ጊዜው አሁን ነው። አገልግሎትህን ወይም የትርጓሜ ፕሮጄክትህን ለመወሰን እንዳትዘገይ እርግጠኛ ሁን። የአገልግሎት ፕሮጀክትህን የበለጠ ባወቅህ መጠን እና የጥናት ምንባብህን ቶሎ በመረጥክ መጠን ለመዘጋጀት ብዙ ጊዜ ይኖርሃል፣ ስራህም የተሻለ ይሆናል! በሚቀጥለው ትምህርታችን የእግዚአብሔርን ትምህርት፣ የሥላሴ ትምህርት ወይም የእግዚአብሔር የሦስትነት ባሕርይ ከሚባሉት ታላላቅ ምሥጢራት አንዱን አብረን እናጠናለን። መጽሐፍ ቅዱስ አንድ እግዚአብሔር እንዳለ ያስተምረናል፣ ያም እግዚአብሔር ራሱን እንደ እግዚአብሔር አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ይገልጣል። ቅዱሳት መጻሕፍት አንድ እውነተኛ አምላክ የሦስትነት ባሕርይ እንዳለውና የሥላሴ አካላት አንድ፣ ልዩ ልዩና እኩል መሆናቸውን፣ አንድ እውነተኛ አምላክ አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ መሆናቸውን ያስረዳሉ። እንዲሁም የአምላካችንን የከበረ ታላቅነት በመንፈሳዊነቱ፣ በህይወቱ፣ በማንነቱ፣ በማያልቀው ባህሪው እና በማይለወጠው ማንነቱ እንመረምራለን።

ሌሎች የቤት ስራዎች

ለቀጣዩ ትምህርት መዘጋጀት

Made with FlippingBook - Online magazine maker