God the Father, Amharic Mentor Guide
/ 7 1
እግዚአብሔር አብ
አብ ተስፋዬ; ልጄ ሆይ መጠጊያዬ; መንፈስ ቅዱስ ሆይ ጥበቃዬ። ቅድስት ሥላሴ ሆይ ክብር ላንተ ይሁን።
~ Compline, Eastern Orthodox, St. Joannikios Appleton, George, ed. The Oxford Book of Prayer. Oxford/New York: Oxford University Press, 1988. p. 183
ማስታወሻዎችህን አስቀምጠህ ፣ ሃሳቦችህን እና ምልከታዎችህን ሰብስበህ ለትምህርት 2 “እግዚአብሔር ፈጣሪ: የእግዚአብሔር አቅርቦት” የተዘጋጀውን አጭር ፈተና ውሰድ።
የሙከራ ፈተና
ከሌላ ተማሪ ጋር በመሆን ላለፈው ክፍለ ጊዜ የተመደቡ የቃል ጥናት ጥቅሶችን ገምግሙ ፣ ፃፉ እና/ ወይም አንብቡ - 1ኛ ዜና 29፡11-12።
የቃል ጥናት ጥቅስ ቅኝት
ያለፈውን ሳምንት ለንባብ የጠሰጠ ሥራ በማጠቃለል አጭር ክለሳ በማዘጋጀት በተመደበው ንባብ (ንባብ ማጠናቀቂያ ገጽ) ላይ ለማንሳት ዋና ዋና ነጥቦችን አብራራ፡፡
የቤት ስራ/መልመጃ ማስረከቢያ
3
እውቂያ
ትርጉም አልባው እምነት? ከቤተክርስቲያንህ አባላት አንዷ ወይዘሮ ጃክሰን በአንዱ ቀን ከይሖዋ ምሥክር ጋር ተገናኝታ ያደረገችው ውይይት ከዚያን ጊዜ አንስቶ ሃሳቧን ይዞታል። ወይዘሮ ጃክሰን ቤቷን የጎበኙትን የይሖዋ ምሥክሮች ንጹሕ፣ ቀላል እና ማራኪ አመክንዮ ከአንድ ሰዓት በላይ በጥሞና አዳምጣለች። እነዚህ ጎብኚዎች የተደራጀችው ቤተክርስቲያን ታምንበታለች የሚሉትን የስህተት ዝርዝራቸውን ሲያቀርቡላት ሙሉ በሙሉ ጭንቀት ተሰማት። ብዙ አስተምህሮዎችን እንደ ቀላል ውሸት እና ታሪካዊ ስሕተቶች በመቁጠርና ውድቅ በማድረግ ምስክሮቹ የመንፈስ ቅዱስን ማንነት፣ የሥላሴ ትምህርት፣ የክርስቶስ አምላክነት፣ የገሃነም መኖር፣ በጸጋ መዳን እና ወዘተ ላይ አጥብቀው ይከራከራሉ። በሁኔታው የተበሳጨው አንድ የቤተክርስቲያን አባል፣ “እናንተ ሁሉንም ነገር የተረዳችሁ ይመስላችኋል፤ ነገር ግን የምታምኑት ነገር ከምክንያታችሁ ጋር የሚጣጣም አይመስልም” በማለት ምሥክሮቹን ጠየቃቸው። የምሥክሮቹ ቡድን ዋና ሰው “ልክ ነው፣ ለአንተ ትርጉም የሌለው እምነት ስለምን ፈለግህ?” በማለት መለሰ። ይህ ሐረግ ከተነገረበት ጊዜ ጀምሮ አባልህ ጋር ቀርቷል። የይሆዋ ምሥክሩን ጥያቄ እንዴት ትመልሳለህ? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉት ሁሉም ነገሮች ምስክርነታቸውን ከማመናችን በፊት ለእኛ “ትርጉም” ሊሰጡን ይገባል? ከእውቀትና ከአመክንዮ በላይ ቢያልፍም መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ማንኛውንም ነገር ማመን አለብን ወይስ የለብንም?
1
ገጽ 268 3
Made with FlippingBook - Online magazine maker