Theology of the Church, Amharic Mentor Guide
/ 1 1
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
4. ከመርሆዎቹ ውስጥ አንዱ፣ የተወሰኑት ወይም በጠቅላላው ከሚከተሉት ነጥቦች ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ አሳይ፥ ሀ. ከአንተ የግል መንፈሳዊ ህይወት እና ከጌታ ጋር ካለህ ጉዞ ጋር
ለ. በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ካለህ አገልግሎት ጋር
ሐ. ባለህበት ማህበረሰብም ሆነ በጠቅላላው ህብረተሰብ ውስጥ ከሚንጸባረቁ ሁኔታዎችና ችግሮች ጋር የዚህን ትምህርት (ሞጁል) መጽሐፍ እና ማጣቀሻዎችን እንደ መመሪያና እንደ መርጃ ለመጠቀም ነጻነት ይኑርህ፤ ይህን በምታደርግበት ወቅት ግን የሌላን ሰው ምልከታ ከተዋስክ ወይም በዛ ምልከታ ላይ የራስህን ከመሰረትክ ለባለሃሳቡ ዕውቅና መስጠትን መዘንጋት የለብህም። ለዚህም የጽሁፍ ውስጥ ማጣቀሻዎችን፣ የግርጌ ማስታወሻዎችን፣ ወይም የመጨረሻ ማስታወሻዎችን ተጠቀም። የተጠቀምከው የማስታወሻ ዘዴ ተቀባይነት የሚኖረው 1) በጠቅላላው የጽሁፍ ስራህ ውስጥ ወጥነት ያለው ሲሆንና 2) የተጠቀምከውን የሌላን ሰው ሃሳብ በትክክል የሚያመለክት ሲሆንና ተገቢውን እውቅና ሲሰጥ ብቻ ነው ፡፡(ለተጨማሪ መረጃ ከአባሪዎች ገጽ ላይ Documenting Your Work : A guide to Help You Give Credit Where Credit is Due ተመልከት ፡፡) የትርጓሜ ጥናቱ (ኤክሴጄቲካል ፕሮጀክቱ) የሚከተሉትን መመዘኛዎች የሚያሟላ መሆኑን አረጋግጥ:- • በአግባቡ መጻፉን(ታይፕ መደረጉን) • ከላይ ከተሰጡት ምንባቦች የአንዱ ጥናት መሆኑን • ሳይዘገይ በቀኑና በሰኣቱ ገቢ መደረጉን • ርዘመቱ 5 ገጽ መሆኑን • ከላይ የተሰጠውን መመሪያ ተከትሎ መሰራቱንና አንባቢው በቀላሉ ተከትሎ ሊረዳው የሚችል መሆኑን • ምንባቡ ከህይወትና ከአገልግሎት ጋር ያላቸውን ዝምድና የሚያሳይ መሆኑን እነዚህን መመሪያዎች አይተህ አትደናገጥ፤ ይህ የመጽሀፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮጀክት ነው፤ ማድረግ የሚያስፈልግህ ምንባቡን በደንብ ማጥናት፤ ከምንባቡ ውስጥ ትርጉም መፈለግ፤ ከዚያም ቁልፍ የሆኑ መርሆዎችን ከምነባቡ ማውጣት እና መርሆዎቹንም ከህይወትና ከአገልግሎት ጋር ማዛመድ ናቸው፡፡ ይህ የትርጓሜ ጥናት (ኤክሴጄቲካል ፕሮጀክት) የ45 ነጥቦች ዋጋ ያለው ሲሆን ከጠቅላላው የዚህ ኮርስ ውጤት 15% ይይዛል፡፡ ስለዚህ በተቻለህ መጠን ስራህን የላቀና አስተማሪ አድርገሀ ለማቅረብ ሞክር፡፡
ምዘና
Made with FlippingBook Ebook Creator