Theology of the Church, Amharic Mentor Guide

/ 1 2 5

የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት

ሐ. በመጨረሻም እንደ መንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ የእግዚአብሔር ስም የሚታወቅበት እና የሚከበርበት እንደ ቅዱስ ስፍራ የቅድስና እና የመታዘዝ ስራዎችን ልንከታተል ይገባናል።

1. እንደ አማኞች በምናደርገው እንቅስቃሴ ሁሉ የእግዚአብሔርን ንፅህና እና የእኛን ታዛዥነት የሚገልጡ ስራዎችን መስራት እና ህይወት መኖር አለብን። ዕብ. 12.14.

2. የእግዚአብሔር የራሱ ማደሪያ እንደመሆናቸው የቤተክርስቲያ አባላት በግለሰብ ደረጃ የእግዚአብሔርን ንፅህና የሚያሳዩ የአኗኗር ዘይቤዎችን መከተል አለባቸው፣ ምክንያቱም ይህ እንደ እግዚአብሔር ሰዎች ተቀዳሚ ስራችን ነውና። 2ቆሮ. 6.16-7.1. (clarity on 7.1.)

በአዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉት እነዚህ የቤተ ክርስትያን ምስሎች የእግዚአብሔር ቤተሰብ፣ የክርስቶስ አካል እና የመንፈስ ቤተመቅደስ የእግዚአብሔርን መልካምነት ለማሳየት ስራችንን እንድንረዳ ያስችሉናል። ከምንም ነገር በፊት በተልእኮ አንድነታችንን የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመፈጸም የጋራ ትብብራችን እና በድርጊታችን እንዲሁም በእንቅስቃሴያችን ቅድስናን ማሳየት አለብን።

II. ቤተክርስቲያን የክርስቶስ አምባሳደሮ በመሆን በእኛ የነጻነት፣ የሙሉነት እና የፍትህ ስራችን የመንግስቱን ጻድቅ አገዛዝ ታሳያለች። 2 ቆሮ. 5፡18-21 - የክርስቶስን መንግሥት በመወከል እና ሁሉም ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር እንዲታረቁ በመጠየቅ እንደ ክርስቶስ አምባሳደሮች ሆነን መኖር እና መሥራት አለብን። እኛ በዚህ ዓለም ውስጥ ነን ነገር ግን የዚህ ዓለም አይደልንም።.

4

ፊል. 3፡20-21 - እኛ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሰማይ ዜጎች ነን።

1 ጴጥ. 2፡16 - እኛ ወደ እውነተኛ ቤታችን፣ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም የምንሄድ በጊዜያዊነት በምድር ላይ ያለን መጻተኞችና እንግዶች ነን።

እንደ አምባሳደር፣ የመንግሥቱን ነፃነት፣ ምሉዕነት እና ፍትህ በሚገልጹ ሥራዎች እንሳተፋለን።

ሀ. በመጀመሪያ፣ እንደ ክርስቶስ አምባሳደሮች፣ የመንግሥቱን ነፃነት ለማሳየት እንሰራለን።

1. የኢየሱስ አገልግሎት እና ኢሳ 61፤ የኢዮቤልዩ ዓመት፣ አገልግሎቱን ለድሆች የማወጅ፣ ለታሰሩት ነጻ መውጣት እና የዕውሮች ዳግም ማየትን ነው።

Made with FlippingBook Ebook Creator