Theology of the Church, Amharic Mentor Guide
/ 1 3
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
በእግዚአብሔር እቅድ ጥላ ውስጥ ያለች ቤተክርስቲያን
ት ም ህ ር ት 1
ገጽ 199 1
የትምህርቱ ዓላማዎች
ሃያል በሆነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን ! የዚህን ትምህርት መጽሐፍ ካነበብክ፥ ካጠናህ፥ ውይይት ካካሄድክና ወደ ተግባር ከቀየርከው በኋላ የሚከተሉትን ማድረግ ትችላለህ:- • ቤተክርስቲያን እንዴት በእግዚአብሔር ከፍ ባለ አላማ እንደምትታይ ማብራራት ትችላለህ: ማለትም እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር በገባው ቃል ኪዳን አማካኝነት በአዲሱ ሰው በኩል ክብርን ለማምጣት መወሰኑን ትረዳለህ። • ለጸጋው የድነት እቅዱ መገለጥ፣ አህዛብ በክርስቶስ ኢየሱስ የተካተቱበትን ታላቅ ምስጢር ለመግለፅ ከቤተክርስቲያን ጋር የተገናኙ ተዛማጅ መፅሃፍቶችን እና ፅንሰ-ሀሳቦችን ትገነዘባለህ። • ቤተክርስቲያን በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በተገለጠው የእግዚአብሔር እቅድ ጥላ ውስጥ እንዴት እንደምትገለጽ በዝርዝር መናገር ትችላለህ፣ ከመጀመሪያ ጀምሮ የእግዚአብሔር ሃሳብ ለራሱ የተለየ እና ምርጥ የሆነ የእግዚአብሔርን ህዝብ መፍጠር ነበር፣ ይህም የእግዚአብሔር ላኦስ ነው። • መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነን የመዳን ትርጓሜ መስጠት እና ይህም በቤተክርስቲያን ውስጥ ከሚኖር ተሳትፎ ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ትረዳለህ። • ቤተክርስቲያን ከብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ህዝቦች ጋር ስላላት ግንኙነት የሚገልጽ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ማሰላሰል ትችላለህ። ቅዱስ ህዝብ 1ኛ ጴጥሮስ 2፡9-10 አንብብ። “ቤተክርስቲያን” የሚለው ቃል ብዙ ምስሎችን ወደ አእምሯችን ያመጣል። ለብዙ ሰዎች “ቤተ ክርስቲያን” የሚለውን ቃል ሲሰሙ በመጀመሪያ የሚያስቡት ነገር ከላይ መስቀል ያለበት ሕንፃ ነው። ነገር ግን ሐዋርያው ጴጥሮስ ስለ ቤተክርስቲያን የሚያስበው እንደዛ አይደለም። ለጴጥሮስ ቤተክርስትያን እግዚአብሔር እርሱን እንዲያገለግሉት እና ስሙን በምድር ላይ እንዲወክሉ የመረጣቸው ሰዎች ልዩ የሆነ ስብስብ ነው። በእነዚህ ጥቅሶች ላይ ጴጥሮስ በዘፀአት 19.5-6 ላይ እግዚአብሔር ለእስራኤል የተናገረበትን ቋንቋ ተጠቅሟል፡- “አሁንም ቃሌን በእውነት ብትሰሙ ኪዳኔንም ብትጠብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ፤ እናንተም የካህናት መንግሥት የተቀደሰም ሕዝብ ትሆኑልኛላችሁ። ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ቃል ይህ ነው።” ጴጥሮስም ደግሞ አሕዛብን አካትታ ለያዘች ቤተ ክርስቲያን እየተናገረ መሆኑን እያወቀ፣ “እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን
ገጽ 199 2
1
ጥሞና
ገጽ 199 3
Made with FlippingBook Ebook Creator