Theology of the Church, Amharic Mentor Guide

/ 1 7

የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት

2. የተስፋው ቃል በአብርሃም የዘር ሐረግ የእግዚአብሔር መለኮታዊ ሥራ ይሆናል።

ሐ. ይህ ቃል ኪዳን አሕዛብን ጨምሮ፣ ሁሉም በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ የተዋጁትን ሕዝብን ለራሱ ለማውጣት የእግዚአብሔርን የላቀ ዓላማ ገልጧል፣ ገላ. 3.6-9. ይህ ጽሑፍ በአብርሃም ቃል ኪዳን በኩል ለቤተክርስቲያን ጥላነት በርካታ ጠቃሚ እንድምታዎች አሉት።

1. የአብርሃም እምነት እንደ ጽድቅ ተቆጠረ።

1

2. አማኞች እግዚአብሔር ለአብርሃም ከገባው የተስፋ ቃል ጋር ተዛመዱ።

3. እግዚአብሔር በአብርሃም ቃል ኪዳን በማመን አሕዛብን እንደሚያጸድቅ ቅዱሳት መጻሕፍት አስቀድመው አመላክተዋል።

II. ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር የማይታጠፍ እቅድ ተጠልላለች፡ በኢየሱስ ክርስቶስ፣ እግዚአብሔር ለዓለም ሁሉ የራሱን ክብር በአይሁድ እና በአህዛብ መካከል ለመመስረት ያለውን ምሥጢሩን ገልጧል። በአብርሃም የተስፋ ቃል አሕዛብን ለመቤዠት የእግዚአብሔር ምሥጢር መገለጡን ሦስት ግልጽ ጽሑፎች ያመለክታሉ።

ሀ. ጽሑፍ አንድ፡- ከጥንት ጀምሮ የተሰወረው ምሥጢር አሁን በነቢያትና በሐዋርያት ተገልጧል፣ ሮሜ. 16፡25-27።

ይህ ጽሑፍ በርካታ ወሳኝ ነጥቦችን ይጠቁማል፡-

1. ይህ ምስጢር፡ የኢየሱስ ክርስቶስ የወንጌል ስብከት

2. ይህ የኢየሱስ ክርስቶስ ስብከት ለብዙ ዘመናት ተሰውሮ የነበረው ምሥጢር ሲገለጥ ነው።

Made with FlippingBook Ebook Creator