Theology of the Church, Amharic Mentor Guide

/ 3 1

የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት

እግዚአብሔር ግለሰቦችን እያዳነና ለመንግስተ ሰማያት እያዘጋጃቸው ብቻ አይደለም። ይልቁንም እግዚአብሔር የሚያድርባቸው እና በሕይወታቸው አብረው የእግዚአብሔርን ሕይወትና ባሕርይ የሚገልጡትን ሕዝብ ለስሙ እየፈጠረ ነው። ይህ የመዳን አመለካከት በጳውሎስ ዘንድ ጥልቅ አመለካከት ነው። ~ Gordon D. Fee. God’s Empowering Presence. Peabody: Hendrickson, 1994. p. 872.

መ. ድነት ማለት ከእግዚአብሔር ሰዎች ጋር መዋሃድ መሆኑን እንድንረዳ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳት መጻሕፍት መሠረት ጥለውልናል።

ገጽ 205  14

1

1. ከግብፅ መዳን (ዘፀአት)፡-

ምናልባት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሁሉ የተሻለው የድነት ምስል የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ባርነት ነፃ የወጡበት የዘፀአት ታሪክ ነው። በቤተክርስቲያን ታሪክ ከጥንት ጀምሮ የዘፀአት ታሪክ ክርስቲያናዊ የመዳንን ግንዛቤ የሚያብራራ ታሪክ እንደሆነ ይወሰዳል። የዘጸአት ታሪክ ድነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዴት አድርጎ እንደሚስል አስተውል።

ሀ. ያለ ተስፋ በመከራ ውስጥ የሚኖር ባሪያ ሕዝብ (በግብፅ ያሉ እስራኤላውያን)

ለ. እርሱ በላከው (ሙሴ) አማካኝነት በእግዚአብሔር ምርጫ ተጠርተዋል

ሐ. በደሙ (በፋሲካው በግ በኢየሱስ) አማካኝነት ከእግዚአብሔር ቁጣ ይድናሉ

መ. በእግዚአብሔር ታላቅ ኃይል (በፈርዖን እና በሠራዊቱ ሽንፈት) ከክፉ አገዛዝ ነፃ ወጡ

ሠ. በውሃ (ቀይ ባህር) ውስጥ በማለፍ ነጻ ይወጣሉ

ረ. የእግዚአብሔርን ፈቃድ (ሕግ) የሚታዘዙ የተቀደሰ ሕዝብ (እስራኤል) ሆነው ተመስርተዋል

ሰ. ለአሕዛብ ምስክር የመሆን ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል (ዘጸ. 19.5-6)

Made with FlippingBook Ebook Creator