Theology of the Church, Amharic Mentor Guide
/ 4 3
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
በአምልኮ ላይ ያለች ቤተ ክርስቲያን
ት ም ህ ር ት 2
ገጽ 209 1
የትምህርቱ ዓላማዎች
ሃያል በሆነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን ! የዚህን ትምህርት መጽሐፍ ካነበብክ፥ ካጠናህ፥ ውይይት ካካሄድክና ወደ ተግባር ከቀየርከው በኋላ የሚከተሉትን ማድረግ ትችላለህ:- • መዳን የሚገኘው በእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ ነው የሚለውን ሀሳብ እና የሰው ልጅ በምንም መንገድ ሊያገኘው ወይም ሊገባው አይችልም ለሚለው ሃሳብ ትሟገታለህ። • አምልኮ ለእግዚአብሔር ፀጋ ትክክለኛ ምላሽ መሆኑን ትገነዘባለህ። • “ምስጢረ ቁርባን” እና “ሥርዓት” በሚሉት ቃላት መካከል ያለውን ልዩነት ማብራራት እና ከእያንዳንዱ ቃል በስተጀርባ ያለውን ሥነ-መለኮታዊ አመለካከት መግለጽ ትችላለህ። • የጥምቀትን እና የጌታን እራትን ትርጉም ትረዳለህ፣ ደግሞም ክርስቲያኖች ስለነዚህ ትርጉም በሚያስቡበት መንገድ ላይ ያሉትን ቁልፍ ልዩነቶች ማብራራት ትችላለህ። • እግዚአብሔርን መሳይ ከማይገኝለት ቅድስናው፣ ወሰን ከሌለው ውበቱ፣ ወደር ከሌለው ክብሩ እና አቻ ከማይገኝለት ስራው የተነሳ እግዚአብሔርን ማክበር የቤተክርስቲያን የአምልኮ ዋነኛ አላማ እንደሆነ ታሰላስላለህ። • ቤተክርስቲያን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል አምላከ ሥላሴን እንደምታመልክ መግለጽ ትችላለህ። በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አማካኝነት በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ያህዌ አምላክን ብቻ እናመልካለን። • ቤተክርስቲያን በምስጋና እና በውዳሴ እና ቃሉንና ምስጢራትን በሚያጎላ በስርዓተ ቅዳሴ፣ እንዲሁም እንደ ቃል ኪዳን ማህበረሰብ በመታዘዝ እና በአኗኗር ዘይቤዋ እንዴት እንደምታመልክ መረዳት እና መተግበር ትችላለህ። የምስጋና መስዋዕትን እናመጣለን። ሮሜ 12፡1-2፣ ዕብራውያን 13፡15 እና ዕንባቆም 3፡17-19 አንብብ። ከብሉይ ኪዳን የአምልኮ ሥርዓት ጋር ከተያያዙት በጣም የተለመዱ ሃሳቦች አንዱ የመስዋዕት ሃሳብ ነው። በቤተ መቅደሱ ውስጥ ካለው አገልግሎት ጋር በተገናኘ በጋራ በሚከወን ሕዝባዊ አምልኮ ወቅት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡ ሁሉ፣ በመደበኛው የአምልኮ ጊዜም ሆነ ወይም እንደ ቤተ መቅደሱ ምርቃት ባሉ አስፈላጊ ዝግጅቶች ወቅት በማንኛውም ሁኔታ መስዋዕቶችን ያቀርቡ ነበር። በእንዲህ አይነት ጊዜ፣ አምላኪዎቹ በቤቱ ምሥረታ ላይ እግዚአብሔር ስላደረገው ታላቅ ቸርነት ምስጋናቸውን ለማቅረብ የእንስሳትን ደም ያፈስሳሉ (2ዜና. 7.5)። በጣም የሚያስደንቀው ነገር፣ ማንም ሰው ስለ እርሱ ሲባል የሚሠዋውን
2
ጥሞና
ገጽ 210 2
Made with FlippingBook Ebook Creator